2010-11-16 14:14:55

ብፁዕ ካርዲናል ኤርዶ፣ የእምነትን በሙላት ለማክፈል


የባህል ጉዳዩ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት አባል የሃንጋሪ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የኤስተርጎም እና ቡዳፔስት ሊቀ ጳጳስ የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ኅብረት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ኤርዶ የባህል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት የመገናኛ ብዙሃን ሥነ ባህል እና አዳዲስ ቋንቋዎች በሚል ርእስ ሥር ባካሄደው ዓውደ ጥናት ንግግር በማሰማት RealAudioMP3 መሳተፋቸው ሲገለጥ፣ ብፁዕነታቸው ከዓውደ ጥናቱ ፍጻሜ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ወንጌል በማስፋፋት ዓላማ ወቅቱ የሚያቀርበው የመገናኛ ብዙኃን ዕደ ጥበባዊ እድገት መጠቀም አስፈላጊ ነው። ቋንቋ የመወለድ የመሻሻል እና የመሞት ባኅርይ ያለው ነው። ስለዚህ የሚሰበከው የወንጌል ቃል፣ የዚህ ቋንቋ ሥነ ሂደታዊ ለውጥ ተጠቃሚ ሊሆን ይገባል፣ የድረ ገጽ፣ የሲነማ ባህል፣ የሙዚቃ በጠቅላላ የስነ ጥበብ ባህል በመጠቀም እና በማስደገፍ የሚቀርብ የታመነበት በቃል እና በሕይወት የሚኖር ወንጌል እና እምነት ማካፈል አስፈላጊ መሆኑ የተሰመረበት ዓውደ ጥናት ነበር በማለት፣ ቤተ ክርስትያን በተለያዩ አገሮች የተለያየ ቋንቋ በመጠቀመ አንድ ብቸኛ እና ልዩ የሆነው መልክእት ታቀርባለች፣ የሥነ ምርምር እድገት ተጠቃሚ መሆን እንደ ጊዜው መለዋወጥ ማለት ሳይሆን ከጊዜ ጋር እኵል በመራመድ አሳማኝ የሆነው ኅያው እምነት ማካፈል አስፈላጊ እና ይኸንን ለማከናወን መከተል የሚያስፈልገው መንገድ የተለየበት ዓውደ ጥናት ጭምር መሆኑ በማብራራት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.