2010-11-16 14:13:11

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፣ እምነትን ለማካፈል ብቃት ያለው አዳዲስ ቋንቋዎች በመሻት መጠቀም


የመገናኛ ብዙሃን ሥነ ባህል እና አዳዲስ ቋንቋዎች በሚል ርእስ ሥር የባህል ጉዳያ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያዘጋጀው ዓመታዊ ዓውደ ጥናት ባለፈው ቅዳሜ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ተጋባእያኑን በመቀበል በሰጡት መሪ ቃል መጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

በዚህ እ.ኤ.አ. ከህዳር 10 ቀን እስነ ህዳር 13 ቀን 2010 ዓ.ም. የተካሄደው ዓውደ ጥናት RealAudioMP3 የተሳተፉት በባህል ጉድያ በሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ጃንፍራንኮ ራቫዚ ተሸኝተው ከቅዱስ አባታችን ጋር ከተገናኙ በኋላ ብፁዕ አቡነ ራቫዚ ተጋባእያኑን ወክለው ለቅዱስነታቸው የሰላምታ መልእክት ካሰሙ በኋላ፣ በመቀጠል ቤተ ርክስትያን እምነትን ለማካፈል ብቃት ያለው አዳዲስ ቋንቋ አበክራ መሻት እንዳለባት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለተጋባእያኑ ባሰሙት ንግግር በማሳሰብ፣ ሆኖም ግን በመጨረሻ ታማኝ ፍቅር ብቻ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ በመጠቆም፣ ይህ በሮማ ምክር ቤት ሕንጻ በሚገኘው የባህል አዳራሽ የተካሄደወ ዓውደ ጥናት እምነት ለሁሉም ሰው ዘር ለማካፈል በዓለማችን ለአስፍሆተ ወንጌል መሰናክል የሆነውን መለየት በተሰኘው መሠረታዊ ሀሳብ ላይ ያተኮረ ዓውደ ጥናት ከሁሉም ጋር ለመወያየት ያለው ዝግጁነት የሚመሠክር መሆኑ ብፁዕ አቡነ ራቫዚ ባሰሙት መልእክት አስታውቀዋል።

ቅዱስ አባታችን ለተጋባእያኑ ባሰሙት ንግግር፣ እግዚአብሔር በመልካም ፈቃዱ እና ጥበቡ ለእኛ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሊያሳውቀን ፈልገ፣ በማለት ይህ የባህል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት፣ በዚህ በቋንቋዎች መታደስ እና በአዲስ የመገናኛ ብዙሃን ሥልት የሚገለጠው ጥልቅ የባህል ለውጥ በሚታይበት ዓለም፣ የዘመኑን ሰው ቀርቦ በማዳመጥ ለአስፍሆተ ወንጌል የሚበጀው አዳዲስ አጋጣሚዎች በማፈላለግ፣ ወንጌልን ማበሠር ተቀዳሚ ዓላማው መሆኑ በማስታወስ፣ እረኞች እና አማኞች በዚህ አዲሱ ማኅበራዊ ሁኔታ እና በማኅበረ ክርስትያን ጭምር የወንጌል መልእክት እና እምነትን ለማካፈል በሚፈጽሙት አገልግሎት አንዳንድ አሳሳቢ የሆኑትን ችግሮች ቀርበው እንደሚረዱት በማብራራት፣ ባለፈው ሓሙስ ይፋ የሆነው ቨርቡም ዶሚኒ-የጌታ ቃል በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ሓዋርያዊ ምዕዳን በመጥቀስ ክርስትያኖች የወንጌል ተጨባጭ ኃይል ተመክሮ እንዲኖራቸው አሳማኝ የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ሊበሠርላቸው እንደሚፈልጉ ቨርቡም ዶሚኒ ቁጥር 96 ያለው ማብራሪያ በማስታወስ፣ ከዚህ አኳያ የተመለከትን እንደሆነ ቤተ ርክስትያን ከእምነት ተመኩሮ ርቀው የሚገኙትን እና ለእምነት ግድ ለሌላቸውም ጭምር ስትናገር የምታቀርበው የወንጌል መልእክት አጥጋቢ ሳይሆን እና የማያሳትፍ ሆኖ ሲገኝ ተጨማሪ አቢይ ችግር እንደሚሆን አብራርተዋል።

የእምነት ጥልቅ ውበቱ እና ኅያው ትርጉምን ለሌሎች ለማካፈል የምንገለገልበት ቋንቋ አጥጋቢ እና ብቃት የሌለው ከሆነ ወንጌሉ የሚበሠርላቸው በተለይ ደግሞ ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ጋውዲዩም ኤት ስፐስ-ፍሥሓ እና ደስታ በተሰየመው ውሳኔ እንደሚያመለክተው ከእምነት ከቤተ ርክስትያን እንዲርቁ ተጨማሪ ምክንያት ይሆናል፣ ስለዚህ የሚተላለፈው መልእክት የእግዚአብሄር ገር እና ቸር ገጽታውን እና ሃይማኖትን በብቃት የማይገልጥ ወይንም ለመግለጥ ብቃት የሌለው ይሆናል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ በመግለጥ፣ ቤተ ክርስትያን በታደሰ ብቃት እና በሥነ አቃቂር በማጤን አዳዲስ የመገናኛ ብዙሃን ቋንቋዎችን ለየት ባለ መልኵ በመጠቀም ሃብታም እና ጥልቅ የሆነው በሊጡርጊያ የምትጠቀምባቸው ምልክቶች እና ቋንቋዎች ደምቀው የሚያስተላልፉት መልክት እንዲደርስ እና የሰው ልጅ ልብ እና ኅሊናን በእግዚአብሔር እንዲነካ ማድረግ ይጠበቅበታል። የቤተ ክርስትያን ትውፊት እንደሚያረጋገጠውም ቤተ ክርስትያን ከጥንት ጀምራ የምትጠቀምበት ቋንቋ የሥነ ጥበብ ይኽም ውብ የሆነውም መልእክት ለማካፈል ደጋፊ ኃይል በማድረግ ትጠቅምበታለች፣ ስለዚህ የክርስትናው ሕይወት ያለው ውበት የሚያረጋገጥ የወንጌል መልእክት በብቃት እና በይዞታው እንዲሁም ካዘለው መልእከት ጋር የሚጣጣም የሚስተካከል አዲስ ቋንቋ ያስፈልገዋል፣ ካሉ በኋላ በመጨረሻ ግን ይላሉ ለእምነት የተግባው ፍቅር ብቻ ነው ታማኝ ብለዋል። በሙላት የተኖረ ካለ ማነብነብ እና መለፍለፍ በጽሞና የሚናገር በቃል እና በተግባር የተኖረው የቅዱሳት የእምነት ሰማዕት የክርስትናው ሕይወት አብነት ልዩ ብቃት ያለው ማራኪ እና ውብ መሆኑ ያረጋግጥልናል። በሚኖሩት ሕይወት በቃል እና በተግባር የሚናገሩ ወንጌልን በሙላት ለማካፈል የሚችሉ በግልጽነት ከፍቅር በሚመነጨው ደስታ የተካነ ሕይወት የሚያንጸባርቁ አማኞች ያስፈልጉናል በማለት ያሰሙትን መልእክት እንዳጠናቀቁ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.