2010-11-12 15:44:52

የቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን “ቨርቡም ዶሚኒ” የጌታ ቃል


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ “የጌታ ቃል በቤተ ክርስትያን ሕይወት እና ተልእኮ በሚል ርእስ ሥር እንዲወያይ የጠሩት የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ፣ 12ኛ ጠቅላይ መደበኛ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 5 ቀን እስከ ጥቅምት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. እዚህ በቫቲካን መካሄዱ የሚዘከር ሲሆን፣ የዚህ ጥልቅ እና ሰፊ ቅዱስ ሲኖዶስ የተወያየባቸው፣ RealAudioMP3 ሀሳብ ለሀሳብ የተለዋወጠባቸው፣ በጠቅላላ ከጉባኤው የፈለቀ የውይይት ህሳብ በቅደም ተከተል የጌታ ቃል በሚል ርእስ ሥር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የደረሱት ድህረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ትላትና ህዳር 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በይፋ ለንባብ መብቃቱ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

የቅዱስ አባታችን ሐዋርያዊ ምዕዳን “በግል ሕይወት እና በቤተ ክርስትያን ሕይወት የቃለ እግዚአብሔር ማእከልነት ዳግም ተገቢ ሥፍራ እንዲያገኝ እና ለመላ የሰው ልጅ ድህነት የማብሠሩ ዓላማ አስቸኳይ እና ያለው ውበት፣ ሞትን አሸንፎ ለተነሣው ጸኑ እና ታማኝ ምስክር ሆኖ መገኘት፣ ይኽ ደግሞ ዘለዓለማዊው ቃል ሥጋ የለበሰው እግዚአብሔር የክርስትና ልዩ መግለጫ እና መለያ ማብሰር በሚለው አጭር እና ጥልቅ ሀሳብ ሥር ለማጠቃለለ የሚቻል ነው።

ይህ ትላንትና በቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ክፍል ይፋ የሆነው 200 ገጽ ያጠቃለለ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የድህረ ሲኖዶስ የደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን፣ ቅዱስነታቸው ለእረኞች ለገዳማውያን ለመናንያን እና ለዓለማውያን ምእመናን የክርስትናው መንፈሳዊነት በቤተ ክርስያን አማካኝነት እና መሪነት በሚበሠረው በምንቀበለው በምናከበረው በቃለ እግዚብሔር ዘንድ ያለ መሆኑ በፍጹም ሳይዘነጋ ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር ዕለት በዕለት እያደገ የሚሄድ ጥልቅ ትውውቅ እንዲኖር የሚል ኃላፊነት የተካነው የጋለጥ ጥሪ የቀረበበት ሐዋርያዊ ምዕዳን ነው።

“አንዲት ሴት ከሕዝቡ መካከል ድምጽዋን ከፍ አድርጋ ‘አንተን ወልዳ ያጠባች እናት እንዴት የተባረከች ናት’ አለችው። … ኢየሱስ ግን “የተባረኩስ የእግዚአብሒሔን ቃል ሰምተው በሥራ ላይ የሚያውሉት ናቸው” አላት። ያች ሴት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የብሥራት ቃል ተማርካ ድምጽዋን ከፍ በማድረግ ያሰማቸው የአድናቆት ቃል፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተባረከው የጌታ ቃል የሚሰማ እና እግብር ላይ የሚያውለው ሰው ነው ሲል የሰጠው መልስ የጌታ ቃል በቤተ ክርስትያን ሕይወት እና ተልእኮ በሚል ርእስ ሥር የተካሄደው የኵላዊነት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የደረሱት ትላትና ይፋ የሆነው የድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን መሠረት፣ በቤተ ክርስትያን ሕይወት ከ20 ዘመናት በፊት በዓለም ለዓለም እንዲመሠከር ለቤተ ክርስትያን የተሰጠ የእግዚአብሔር ቃል፣ ዳግም አቢይ እና ፍጽሙ ብሎም የተስተዋለ ትኵረት እንደሚሰጥበት የሚያሳስብ ነው። ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ፣ ቃለ እግዚአብሔር በሚል ውሳኔው ዘንድ ክስተት ወይንም ግልጸት በሚል ርእስ ሥር በቁጥር ሁለት ስለ ክስተት ወይም ግልጸት ዓላማው እና ይዞታው በሚል ንኡስ ርእስ ሥር ኤፈሶን ምዕራፍ 1 ቁጥር 9 “እግዚኣብሔር በቸርነቱ በክርስቶስ አማካይነት አስቀድሞ ባቀደው መሠረት የፈቃዱን ምሥጢር እንድናውቅ አደረገ” የሚለውን የአዲስ ኪዳን ቃል በመጥቀስ የማይታየው የማይዳሰሰው እግዚብሔር በታላቅ ፍቅሩ ለሰው ልጅ እንደ ወዳጅ ጓደኛው በመናገር እና አብሮ በመሆን ከራሱ ጋር እንዲሆኑ እና በእርሱ አማካኝነትም የመለኮታዊ ባህርይ ተካፋይ ለማድረግ ወሰነ በማለት ግልጸት ወይም ክስተትን ይተነትናል። ይህ የድኅረ ሲንዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ከሁልተኛው የቫቲካን ጉባኤ 45 ዓመት በኋላ ዳግም በተመሳሳይ መልኩ ኅያው የሆነ የጌታ ቃል በማነቃቃት፣ “ዘለአለማዊ እግዚአብሔር፣ ዘለዓለም ካለ ማቋረጥ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በቃሉ ማለቂያ በሌለው ፍጹም ፍቅር አማካኝነት እራሱን ለሰዎች አስተዋወቀ። ይህ ቃል በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረ፣ እግዚአብሔር የሆነ በቅድስት ሥላሴ ማለትም በመለኮታውያን አካላት ዘንድ ያለ የፍቅር ምክክር (ፍቅራዊ ግኑንነት) አማካኝነት፣ እራሱን በመግለጥ የዚህ ፍቅር ተካፋዮች እንድንሆን እንደጠራን የሚያረጋገጥልን ሀሳብ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በደረሱት ድኅረ ሲንዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ዳግም ተብራርቶ ይገኛል።

ጠቅለል ባለ አገላለጥ፣ ሥነ ማርያማዊ የግልጸት ወይንም የክስተት ገጽታው ከሚል ቲዮሎግያዊ ሥነ ሐሳብ በመንደርደር ግልጸት ያለው ነገረ ሥላሴአዊ እና ሥነ ክርስቶሳዊ ገጽታው እርሱም የዮሐንስ ወንጌል መቅደም እና የቅዱስ ጳውሎስ መልእክቶች መሠረት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ቃለ እግዚአብሔር በሚለው ውሳኔ ዘንድ ያሰፈረው ሐሳብ በመከተል፣ ለመወያየት ወይንም ለመመካከር የሚጠራው የግልጸት ክርስትያናዊ ይዞታው የሚያብራራ፣ የእግዚአብሔር ቃል ዘለዓለማዊ የሚፈጥር የሚገናኝ መሆኑ የሚገልጥ ነው።

የቅዱስ መጽሓፍ ሥነ መንፈሳዊ ገጽታው፣ ይኽ ደግሞ ቅዱስ መጽሓፍ በትክክል በቤተ ክርስትያን የዚህ ቃል ማኅደር በመሆንዋ አማካኝነት በእርሷ መሪነት ሥር፣ ትክክለኛ ትርጉሙ እና አገላለጡ ወይንም ትንተናውን በመከተል የሚጎላው እምነት እና የሚኖረው መንፈሳዊነት የሚተነትን እና መጽሓፍ ቅዱስ ማእከል በማድረግ የሚደረገው ሥነ ምርምራዊ ጥናት እና ቲዮሎጊያ ገጽታው የሚፈጠረው ተመሣሳይ-የማይገናኝ ክሌአዊ መንገድ ያለው ውህደትና ተሟይነታቸውን የሚያሥረዳ ነው።

በጥልቀት መጤን የሚገባቸው ጥያቄዎች ማለትም የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ የፍጻሜ ሰነድ ያሰፈራቸው ሃምሳ አምስት የሐሳብ መስተዋድዶች ላይ በማተኮር፣ ቲዮሎጊያ ለመጽሓፍ ቅዱስ ትንተና እና ትክክለኛ አገላለጥ ብሎ የሚያቀርበባቸው ሁለት ሐሳቦች፣ እርሱም ቤተ ክርስትያን ቅዱስ መጽሓፍ እውነተ እና አስተንፍሶ የሚሉትን ሁለት ቃላት ማእከል በማድረግ የምትጠቀምባቸው የቅዱስ መጽሐፍ ሥነ ትንተናዊ ሥልት የሚያጎላ ሲሆን፣ ሆኖም ግን በመካሄድ ላይ ያለው ጥልቅ እና የማያቋርጥ ጥናት ግምት የሚሰጥ ቃለ እግዚአብሔር በሊጡርጊያ እና ከተለያዩ ጥሪዎች ጋር ያለው ኃላፊነት የተካነው ግኑኝነት የሚያብራራ ነው። ቅዱሳት መጻሕፍት አንድ መጽሐፍ፣ የክርስቶስ መጽሐፍ ስለ ክርስቶስ የሚናገር መጽሐፍ በክርስቶስ ዘንድ የተሟላ ፍጻሜ ያለው መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በደረሱት ሐዋያዊ ምዕዳን አማካኝነት በጥልቀት ያስረዳሉ።

ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የዛሬ 45 ዓመት በፊት ካጸደቃቸው ውሳኔዎች ውስጥ ደይ ቨሩቡም ማለትም ቃለ እግዚአብሔር የተሰየመው ውሳኔ አንዱ ሲሆን፣ ያንን ውሳኔ በጥልቀት ካለ መረዳት ቀስ በቀስ ያስከተለው በስሜት ላይ ብቻ የሚገለጥ መንፈሳዊነት ወይንም ቅዱስ መጻሕፍት የሥነ ምርምር ማእከል በማድረግ መንፈሳዊ ገጽታው ችላ የሚለው ደረቅ ሥነ ምርምር ተገቢ ምላሽ የሚሰጥ ሐዋርያዊ ምዕዳን መሆኑ የባህል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ራቫዚ ትላትና ሐዋርያዊ ምዕዳኑን ለንባብ ለማቅረብ በተካሄደው መድረክ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ሲያብራሩ፣ የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ኮየለት በሕዝበ እግዚአብሔር ዘንድ በመታየት ላይ ያለው መንፈሳዊ ግሽበት በማስወገድ የሚያድስ ሐዋርያዊ ምዕዳን መሆኑ በበኵላቸው ባሰሙት ንግግር አስታውቀዋል።

ቅዱስ መጽሐፍ የእምነት መጽሐፍ፣ ከሕዝብ እግዚአብሔር እምነት የተወለደ በመሆኑ በእምነት አማካኝነት ብቻ ጥልቅ ምሥጢሩ ለመረዳት እንደሚቻል እና ይህ እምነት እያደገ መሄድ እንዳለበት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን እንዳሳሰቡ የቅድስት መንበር የዜና እና የማህተም ጉዳይ ተጠሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ገልጠዋል።

የክርስትናው መሠረት ብሉይ ኪዳን መሆኑ ቅዱስ አባታችን በደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን በማብራራት፣ ይኽ ደግሞ በክርስትናው እና በአይሁድ ሃይማኖት መካከል ለሚደረገው ውይይት መሠረት መሆኑ በመጥቀስ፣ የክርስትና እምነት እና የአይሁድ እምነት የሚያገናኝ ድልድይ መሆኑና በጠቅላላ በተለያዩ አቢያተ ክርስትያን መካከል ለሚደረገው ውይይት የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት ማእከል መሆን እንዳለበት ቅዱስነታችው ገልጠዋል።

ቃለ እግዚአብሔር እና ሊጡርጊያ፣ መጽሓፍ ቅዱሳዊ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የተሰኙትን ርእሶች በማብራራት፣ ቃለ እግዚአብሔር ያወቀ ሁሉ የማብሠር ኃላፊነት እንዳለው እና የተቀበልነው ጸጋ ለሌሎች ማሳወቅ ቃሉ እንደለወጠን በመመስከር ሌሎች በቃሉ እንዲማረኩ ብቻ ሳይሆን እንዲለወጡ በቃሉ መሠረት አብነት ሆኖ መገኘት የሚያነቃቃ ሐዋርያዊ ምዕዳን ሲሆን፣ በሌላው ረገድ የምንኖርበት ዓለም ቅን እንዲሆን ኢፍትሃዊነት፣ አድልዎ የመሳሰሉትን ሁሉ ካለ ማወላወል የሚቃወም ቃለ እግዚአብሔር የሚያነቃቃው መቀራረብ መተሳሰብ እኩልነት ወዘተ የመሳሰሉት እሴቶች በቃሉ አማካኝነት በቃል እና በሕይወት በመመስከር፣ ዘመናችን በአዲስ መንፈስ ቃል እግዚአብሔር እንዲያዳምጥ እንዲሁም ዳግመ አስፍሆተ ወንጌል አስፈላጊ መሆኑ ቅዱስ አባታችን በደረሱት በሐዋርያዊ ምዕዳን በማሳሰብ፣ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልን ለሁሉም ፍጥረት አብስሩ በሚለውን ቃለ ወንጌል ጥቅስ ሥር አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.