2010-11-09 14:58:39

አይቨርይ ኮስት፣ የአፍሪካ እና የኤውሮጳ አቢያተ ክርስትያን በጋራ


አስፍሆተ ወንጌል በጋራ ኃላፊነት ለሰብአዊ ሕንጸት በሚል እቅድ መሠረት በአፍሪቃ እና በኤውሮጳ አቢያተ ክርስትያን መካከል፣ አድ ጀንተስ ወደ ሕዝብ የሚለው የሁለተኛው የቫካን ጉባኤ ውሳኔ፣ ስለ ቤተ ክርስትያን ሓዋርያዊ ተግባር ወይም ተልእኮ በተመለከተ የተብራራው ዓላማ እና መመሪያ መሠረት በማድረግ በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እቅድ ለመተባበር የሚያነቃቃ የመላ አፍሪካ እና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እና የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በአይቨርይ ኮስት ርእሰ ከተማ አቢጃን እ.ኤ.አ. ከህዳር 10 ቀን እስከ ህዳር 14 ቀን 2010 ዓ.ም. የጋራ ውይይት መርሃ ግብር እንደሚረጋገጥ ተገለጠ።

ይህ በሐዋርያዊ ተልእኮ ዘንድ ካህናት በመለዋወጥ የሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልጋዮች እና ሕንጸት በተመለከተ የቤተ ክርስትያን አገልግሎት የአፍሪካ እና የኤውሮጳ አቢያተ ክርስትያን በመተባበር አስፍሆተ ወንጌል እንዲያከናውኑ የሚያነቃቃ እና የሚያበረታታ መድረክ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል። በዚህ የውይይት መድረክ ከአፍሪካ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ከኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳታ ምክር ቤት፣ ከቅድስት መንበር ከተለያዩ የካቶሊክ የግብረ ሰናይ ማኅበራት የተወጣጡ በጠቅላላ 40 ተባእያን እንደሚሳተፉም ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.