2010-11-09 14:57:32

አባ ሎምባርዲ ከዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ጋር


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሓዋርያዊ ጉብኝት በቅርብ ከሚሸኙት ውስጥ አንዱ፣ የቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ሬድዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ፣ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የስፐይን ሓዋርያዊ ጉብኝት በቅርብ የሚከታተሉት ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ለተላኩት የዓለም ዓቀፍ ጋዜጠኞች፣ የቅዱስ አባታችን በባርቸሎና የሚገኘውን የቅድስት ቤተ ሰብ ቅዱስ ሥፍራ በመጎብኘት እና መሥዋዕተ ቅዳሴ አቅርበው እንዳጠናቀቁ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ቅዱስነታቸው በጋውዲ የሥነ ሕንጻ ጥበብ፣ የቅድስት ቤተ ሰብ ቅዱስ ሥፍራ ንድፍ እና ግንባታው፣ በጠቅላላ የሥነ ጥበብ ውበት እና ጥልቅ ትርጉሙ እጅግ እንደማረካቸው ኣባ ሎምባርዲ ገልጠው የቅድስት ቤተ ሰብ ቅዱስ ሥፍራ ሕንጻ የነደፈው ጋውዲ ጥልቅ መንፈሳዊነት እና የሊጡርጊያ ጥልቅ እውቀት እንዳለው የሚያረጋገጥ መሆኑ ቅዱነታቸው ቀርበው በመመልከት መደነቃቸው ገልጠዋል።

ኣባ ሎምባርዲ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው መጠይቅ ሲመልሱ፣ ቅዱስነታቸው ገና ወደ ስፐይን ለመነሳት በአየሮፕላን እያሉ ማመን አለ ማመን ያው ነው የሚለው እሴቶችን የሚክደው በኤውሮጳ እየተስፋፋ ያለው የአለማዊነት ባህል በተመለከተ ያሉትን እና በዚህ ጥንታዊው ክፍለ ዓለም በሆነው በኤውሮጳ ስላለችው ቤተ ርክስትያን በተመለከተ ካቀርቡት ጥልቅ ትንታኔ ጋር የሚጻረር አይደለም። ስለዚህ የቅዱስነታቸው ትንታኔ ሥነ ታሪክ ገጽታ ያለው ብቻ ሳይሆን በስፐይን በ 1930ዎች ዓመታት የነበረው ጸረ-ቤተ ርክስትያን እና ጸረ-ውሉደ ክህነት ባህል እና ጥሎት ያለፈው ጠባሳ ጭምር ያስታወሰ ነው። ይህ ደግሞ ቤተ ርክስትያን ውይይት ግኑኝነት እንጂ ግጭትን እንደማትሻ የሚያስረዳ ነው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን በናዝራዊት ቅድስት ቤተ ሰብ ቅዱስ ሥፍራ በመገኘት በመጸለይ እና ቅዳሴ በማሳረግ፣ ቤተ ሰብ የኅብረተ-ሰብ ማእከል ቅዱስ ሥፍራ መሆኑ እና የእግዚአብሔር ቅዱስ አላማ የተኖርበት፣ ቤተ-ሰብ በቤተ ክርስትያን አድማስ ላለው ትርጉም መሠረት ብቻ ሳይሆን ኅብረተ-ሰብን ለማነጽ ቤተሰብ ማነጽ ከሚለው አመክንዮ የሚነሳ እቅድ መሆን እንደሚገባው የሚያብራራ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.