2010-11-09 14:56:46

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ በእምነት እና በዓለማዊነት ሥነ አስተሳሰብ መካከል ግጭት ሳይሆን ግኑኝነት ማነቃቃት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከትላንትና በስትያን ያጠናቀቁት ቅዳሜ ህዳር 6 ቀን 2010 ዓ.ም. በስፐይን በሳንቲያጎ ደ ኮምፖስተላ እና በባርቸሎና ላካሄዱት 18ኛው ዓለም አቀፍ ሓዋርያዊ ጉብኝት ከመንሳታቸው በፊት ወደ ስፐይን በተነሱበት አይሮፕላን ውስጥ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ቃለ መጠይቅ በሰጡት መልስ፣ በስፐይን ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው የሚከተለው ርእሰ ጉዳይ፣ የሚያቀርበው ምዕዳን እና የጉብኝቱ ዓላማ ጠቅለል ባለ መልኩ በማብራራት፣ በእምነት እና በዓለማዊ አስተሳሰብ መካከል ግጭት ሳይሆን ግኑኝነት ሊነቃቃ እንደሚገባው እና በዚሁ ጉዳይ ሥር የስፐይን ባህል ዓቢይ ሚና እንዳለው ቅዱስነታቸው ጠቅሰው፣ ስፐይን የእምነት ቀዳሜ አገር እንደነበረችም ዘክረው፣ ሆኖም ግን በአገሪቱ የተስፋፋው ዓለማዊነት ጸረ-ውሉደ ክህነት አስተሳሰብ፣ ማመን አለ ማመን በእኵል ደረጃ በማስቀመጥ የእሴቶች ቅደም ተከተል ደረጃቸውን ለሚክድ ባህል፣ ቤተ ክርስትያን ወቅታዊ ምላሽ ለመስጠት በሚል እቅድ መሠረት በሳቸው ውሳኔ አማካኝነት የተቋቋመው አዲሱ የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ጳጳሳዊ ምክር ቤት ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን፣ ጠብ ጫሪው ባህል ቀርቦ በመለየት እና በማጥናት፣ በቅዱስ መጽሓፍ በቲዮሎጊያ ሐሳብ ለማሰብ አስቸጋሪ እይሆነ በመጣበት እና ይኽ ባህል በመስፋፋት ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት ወንጌላዊ እሰይታ ኵላዊነት ባህርዩን ለማረጋገጥ አበክሮ እንደሚንቀሳቀስ አብራርተዋል።

በእምነት እና በምርምር/በአእምሮ መካከል ያለው ግኑኝነት በተደጋጋሚ በተለያየ ወቅት በማስመር ያስተማሩት በማረጋገጥ ማብራሪያ የሰጡበት ብቻ ሳይሆን፣ እውነት የምርምር እና የአእምሮ ዓላማ እና ሕይወት ነው፣ ስለዚህ በዚህ ጉዳና ምርምር ወይም አእምሮ ውበት በመሆን እውነተኛውን ውበት ያብራራል፣ ምክንያቱም እውነት ባለበት ውበት ይወለዳልና፣ በዚህ ውበት ዘንድም ሰብአዊ መሆን በትክልል እና በመልካምነት በውበት እራሱን ያብራራል። ስለዚህ በእምንት እና በሥነ ምርምር መካከል፣ በስነ ጥበብ እና በእምነት መካከል ያለው ግኑኝነት በእምነት ጥልቅ መለያው እና ፍሬ ነገሩ ዘንድ ያለ ነው። እምነት በሥነ ጥበብ ዘንድ ጭምር የሚገለጥም ነው። ለዚህ እንደ አብነት የሥነ ሕንፃ ሊቅ ጋውዲ የነደፈው እና ከ 1882 ዓ.ም. ጀምሮ በመገንባት ላይ ያለው ወደ መጠናቀቅ እያዘገመ ያለው የቅድስት ቤተ ሰብ ቅዱስ ሥፍራ ጠቅሰው፣ የቤተ ሰብ አንገብጋቢው እና መሠረታዊው ጥያቄ ቤተ ሰብ የኅብረተ-ሰብ ማእከል በመሆኑ ይኸንን ማእከላዊነት መሠረት ያደረገ ኅዳሴ ያሻዋል፣ ስለዚህ ለቤተሰብ የሚሰጠው ትርጉም እና አክብሮት እንክብካቤ ለኅብረተ-ሰብ የሚሰጥ ይሆናል። ይህ ደግሞ በእምንነ እና በሕይወት በሃይማኖት እና በኅብረተ-ሰብ መካከል ያለው ውኅደት ያመለክታል። ቤተ-ሰብ መሠረታዊ ርእሰ ጉዳይ ነው፣ ምክንያቱን እግዚአብሔር በአንዲት ቤተ ሰብ ዘንድ በመወለድ ቤተ-ሰብ እንድንገነባ እና ቤተሰብአዊነትን እንድንኖር ጠርቶናል ብለዋል።

በመጨረሻ የሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት፣ መንፈሳዊ ንግደት መልክ እንዳለውም ሲያመለክቱ፣ መንፈሳዊ ንገደት ከራስ ወጥቶ ወደ አንድ ትልቅ ቅዱስ ሥፍራ መሄድ ማለት ብቻ ሳይሆን በኅብረት እና በአንድነት መጓዝ ጭምር ያሰማል፣ የአንድነት ጉዞው ቅዱስ ያዕቆብ የምድረ ስፐይን ሰባኬ፣ መንፈሳዊ ተግባር የኤውሮጳ የጋራው መለያ የሕንጸት ክፍል ነው፣ ስለዚህ መንፈሳዊ ንግደት የእምነት መለያ መግለጫ ብቻ ሳይሆን፣ አንዱ ከሌላው ጋር የሚገናኝበት በመገንኘትም በጽሞና በነጻነት በመታደሰ መንፈስ ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘትን ማለት መሆኑ ማብራራታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.