2010-11-06 13:30:59

ጳጳሳዊ የፍትህ እና የሰላም ምክር ቤት፦ አስቸኳይ የተሟላ ሕንጸት ለዓለማውያን ምእመናን


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባስተላለፉት መልእክት ሮማ በሚገኘው በላሳል ወንድሞች ማኅበር ዋና ጠቅላይ ሕንጻ ባለው የጉባኤ አዳራሽ ትላትና ጳጳሳዊ የፍትሕ እና የሰላም ምክር ቤት አስቸኳይ የተሟላ ሕንጸት ለዓለማውያን ምእመናን በሚል ርእሰ ሥር ያዘጋጀው ዓመታዊ ጉባኤ በይፋ መጀመሩ ተገለጠ።

ለጉባኤ የቅዱስነታቸው መልእክት ያነበቡት ጳጳሳዊ የፍትህ እና የሰላም ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ኮድዎ አፒያ ቱርክሶን መሆናቸውም ለማወቅ ሲቻል፣ የኤኮኖሚ እና የገንዘብ ሃብት ድርጅቶች እና ተቋሞች አገሮች በጠቅላላም ዓለማችን ሊከተለው የሚገባው በውስጠ ኣስገዳጅ የሚያቀርቡት የፖለቲካ መርሃ ግብር ኵላዊ ማኅበራዊ ጥቅም የሚጻረር እና የሚጎዳ መሆኑ ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት በማብራራት፣ የሰው ልጅ ሕዝቦች እና በጠቅላላ የዓለም ማኅበረሰብ በመታየት ላይ ባለው ኢፍትሃዊነት፣ አድልዎ ምትክ ቀዳሚው የልማት መሠረታዊ መመሪያ የሰውን ልጅ ሥር ሰደድ ከሆኑት የክፋት መንፈስ የሚያድነው ክርስቶስን ከማብሰር የሚነቃቃው የሕይወት ባህል እና የሕይወት ሙላት የሚያንጸባርቁ የተስፋ ቃላቶች ይሻል ካሉ በኋላ አክለውም፣ አስቸኳይ ምላሽ ለሚያስፈልጋቸው አንገብጋቢ ማኅበራዊ ጥያቄዎች መፍትሄ የሚሰጠው መሠረታዊ የሆነው እቅድ ለማመልከት በጥልቀት ግንዛቤ እንዲሰጣቸው ለዚህ የሚያበቃ አመለካከት እንዲኖር ለመደገፍ እንችላለን የኛ ኃላፊነትም ነው እንዳሉም ተገልጠዋል።

በእምነት ብርሃን እና በምርምር ቦግ ያለ ከፍቅር ጋር በተስፋ የተደገፈ ሂደት ለሰው ልጅ የተሟላ ነጻነት እና ኵላዊ ፍትሕ ለማረጋገጥ የሚያስችሉትን እቅዶች ለማረጋገጥ የሚቻል መሆኑ በማብራራት፣ ስለዚህ በዓለማችን የሚታየው ማኅበራዊ ኢፍትሃዊነት እና ማኅበራዊ አድልዎ ካለ ማቋረጥ በጽናት ግምት በመስጠት አሁንም ዓለማዊነት ትሥሥር በተረጋገጠበት ዘመን ጭምር በበለጠ ትኵረት የሚያሻው መሆኑ ጥሪ በማቅረብ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ማህበራዊ ችግሮችን አድልዎ ኢፍትሃዊነት የመሳሰሉት ነቅሎ ለማጥፋት የተስተካከለ ማህብራዊ ኑሮ ለማረጋገጥ የሚከተሉት መንገድ ለይቶ ለማወቅ የሚያደርጉት ጥረት ሥልጣን ማስተካከል የሚል በመሆኑም የሚያካሂዱት ጥረት ብቃት የሌለው ሆኖ እንደሚቀር በጥልቀት አብራርተዋል።

በመጨረሻ ቅዱስነታቸው ዓለማውያን ምእመናን ማኅበራዊ ጥያቄዎች ነጻ እና የኃላፊነት መንፈስ እንደ ሚሰማው ዜጎ ጭምር ማኅበራዊ ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ እንዲያገኙ እና ሥርዓት የጠበቀ ቅን ማኅበርሰብ እንዲጸና የካቶሊክ የማኅበራዊ ትምህርት ጉዳይ ማእከል ያደረገ ልዩ እና የተሟላ ሕንጸት እንዲያገኙ ማድረግ አጣዳፊ እቅድ መሆን አለበት ካሉ በኋላ፣ ይኸንን እቅድ ለማረጋገጥ ድጋፍ የማቅረቡ ብቃት ባላቸው ካህናት እና ብፁዓን ጳጳሳት አማካኝነት ስበአዊ እና መንፈሳዊ ድጋፍ የተሸኘ መሆን አለበት ብለዋል።

የቤተ ክርስትያን ኅዳሴ ከገዛ-ራስ ህዳሴ ይጀምራል

የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትላትና ቅዱስ ካርሎ ቦሮመዮ አክብራ እንደዋለች ለማወቅ ሲቻል፣ ቅዱስ ካሮሎ ቦረመዮ ወንጌላውያን እሴቶች ድኽነት ትህትና ንጽሕና በጠቅላላ ፍጹም የክርስትና ሕይወት የሚጠይቀው ሰቂለ ኅሊና እራስን የማንጻት ጥሪ በሙላት የኖረ መሆኑ ዕለቱን ምክንያት በማድረግ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለሚላኖ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ዲዮኒጂ ተታማንዚ ባስተላለፉት መልእክት አብራርተዋል።

ቅዱስ ካርሎ ቦሮመዮ የሚላኖ ከተማ ጠብቃ ቅዱስ እንደመሆኑም ቅዱስ ኣባታችን ቅዱስ ካርሎ ቦሮመዮ በደማቅ እና ለየት ባለ የበዓል መንፈስ ለምታከብረው ለሚላኖ ከተማ ባስተላለፉት መልእክት፣ ቅዱስ ካሮሎስ ቦሮመዮ እ.ኤ.አ. በ 1538 ዓ.ም. የተወለደ እ.ኤ.አ. በ 1610 ዓ.ም. ቤተ ክርስትያን ቅድስና እንዳወጀችለት በመጥቀስ፣ በቤተ ክርስትያን የአንቀጸ ሃይማኖት አለው እየተባለ ይፈጸመ የነበረው መከፋፈል እና መደናገር የሚያስከትለውም ጉድለት እንዲስተካከለ በመገዘብ ሆኖም ፍርድ ሳያስቀድም ለመተቸት ብሎ ሳይተች የሌላውን ግድፈት ከመቀሰር ይልቅ የግል ክርስትያናዊ ሕይወት ማደስ ከሚለው አቢይ ኃላፊነት መነሳት የሚለው መሠረተ ሀሳብ በመከተል ቤተ ክርስትያን እና የቤተ ክርስትያን ሕይወት እንዲታደስ እንዳደረገ ዘክረው፣ ከመውቀስ እና ከማውገዝ ይልቅ እራስን መለወጥ ለሚለው የሕይወት አብነት መሠረት በማድረግ ለቅድስና የበቃ በመታደስ ቤተ ክርስትያን ለኅዳሴ ያነቃቃ የቤተ ክርስትያን ልጅ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

የቤተ ክርስትያን ተቀዳሚው ዓላማ እያንዳንዱ የቤት ክርስትያን አባል ታዶስ እና ተለውጦ በእግዚአብሔር መንገድ ይገኝ ዘንድ ማነቃቃት እንደሆነም በቃል እና በሕይወት የመሰከረ ቅዱስ መሆኑ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በማስታወስ፣ በአሁኑ ወቅት በጽሞና እዩልኝ ስሙልኝ ሳይሉ ይኸንን ሕይወት የሚኖሩ የቤተ ክርስትያን ልጆች እንዳሉ በመጥቀስ፣ ሁላችን የቤተ ክስትያን ኅዳሴ የምንሻ እራስ ከማደስ ከሚለው ቅዱስ ዓላማ መጀመር አለብን ብለዋል።

ቅዱስ ቁርባን እና ቅዱስ መስቀል ቅዱስ ካሮሎ ቦሮመዮ በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የሚሰዋው ፍቅር ውስጥ እንዲሰምጥ እንዳደረጉት እና ይኽንን ፍቅር ተቀብሎ በመኖር የጸና መሆኑ አብራርተው፣ በቅዱስ ቁርባን ኅላዌነት ከሚያረጋገጠው ከጌታችን እየሱስ ፍቅር የማይመነጭ የቤተ ክርስትያን ተልእኮ የለም፣ ካሉ በኋላ ቅዱስ ቁርባን እና ቅዱስ መስቀል ማእከል በማድረግ የታደሰ ሕይወት ለቤተ ክርስትያን ኅዳሴ መሠረት ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.