2010-11-06 13:36:51

የአንቀጸ ሃይማኖት ተነከባካቢ ቅዱስ ማኅበር መግለጫ


እ.ኤ.አ. ጥቅምት 2 ቀን 2010 ዓ.ም የኵላዊት ቤተ ክርስትያን የአንቀጸ ሃይማኖት ጉዳይ የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር የኦፑስ አንጀሎሩም፣ የቅዱሳት መላእክት ተግባር ዓቀጸ ሃይማኖታዊ እና ቀኖናዊ ገጽታውን የሚብራራ ያረቀቀው ዟሪ መልእክት ትላትና ይፋ ሆነ።

ይኸንን ዟሪ መልእክት በማስደገፍ የቅድስት መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍል ተጠሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት፣ ዓቀጸ ሃይማኖት የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅሀር እ.ኤ.አ. በ 1983 ዓ.ም. ይህ የቅዱሳት መላእክት ተግባር ማኅበር ለቅዱሳት መላእክት የሚሰጠው መንፍሳዊ የአክብሮት ሥርዓት ጋብሬለ ተርሊኽ በግልጸት በግል የተቀበልኩት ነው በማለት የሰጡት የቅዱሳት መላእክት አክብሮት ግልጸት እና ከዚህ አንጻር ያቀረቡት የቅዱሳት መላእክት ጉዳይ የሚመለከተው የአክብሮት ሥነ ሓሳብ መሠረት ሳይሆን፣ የካቶሊክ አንቀጸ ሃይማኖት መሥፈርት እና ውሳኔ የሚከተል ከዚህ የመነጨ በሊጡርጊያ ሥርዓት እና የቅዱስ ቁርባን ጉዳይ በተመለከተ ያለው ውሳኔ መሠረት መሆን እንደሚገባው አሳስቦ እንደነበር በማስታወስ፣ ይህ መልእክት እ.ኤ.አ. በ 1992 ዓ.ም. ውሳኔ በማድረግ ዳግም እንዳወጁት ኣባ ሎምባርዲ በማብራራት፣ የካቶሊክ አንቀጸ ሃይማኖት የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ያለፉት ውሳኔዎች ዳግም ሰፋ በማድረግ በማብራራት ውሳኔው በማኅበሩ እግብር ላይ እንዲውል ትእዛዝ በመስጠት እና ማኅበሩን በቅርብ የሚከታተሉ የቅድስት መንበር ልዩ ወኪል በማኅበር እንዲቀመጥ እና የቅድስት መንበር ልዩ ልኡክ በተጨማሪም በዚህ የቅዱሳት መላእክት ተግባር ማህበር እና በቅዱስ መስቀል መደበኛ ቆኖናዊ ማኅበር መካከል ያለው ግኑኝነት የሚከታተል መሆኑ አባ ሎምባርዲ የካቶሊክ ትምህርተ ሃይማኖት ዟሪ መልእክት በመጥቀስ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.