2010-11-06 13:32:52

ቅድስት መንበር፦ የእምነት ነጻነት ጥበቃ 


ከትላትና በስትያን በተባበሩት መንሥታት በተካሄደው ጉባኤ በመሳተፍ ንግግር ያሰሙት በድርጅቱ የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ፍራንሲስ ቹሊካት የተሟላ የሰብአዊ ክብር ጥበቃ የሰው ልጅ ውስጣዊ እና ከነገር ባሻገር የሆነው ወደ ላይ የሚያቀናው መንፈሳዊነት አድምስ ዋስትና መስጠት ጭምር ማለት መሆኑ በማብራራት፣ እ.ኤ.አ. በ 1948 ዓ.ም. የተደነገገው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ እንደሚያረጋግጠውም ከሃይማኖት ነጻነት ጋር የተያያዘው የኅሊና ነጻነት ጥበቃ ጭምር የሚጠይቅ መሆኑ በማስታወስ፣ መንግሥታት ይኽ የላቀው የማይሻረ እና የማይታበል ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ የማክበር እና ዋስትና የማስጠበቅ ግዴታ እንዳለባቸው ብፁዕ አቡነ ቹሊካት በማሳሰብ፣ ከዚህ ጋር በማያያዝ በቅርቡ በኢራቅ ባግዳድ የሶሪያ ሥርዓት በምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ካቴድራል የተጣለው ጥቃት በመጥቀስ በዚያች አገር የሚገኘው ማኅበረ ክርስትያን ለዘርፈ ብዙ ችግር ተጋልጦ እንደሚገኝ በማብራራት፣ ለእነዚህ የኢራቅ ክርስትያን ዜጎች መብት እና ፈቃድ መከበር የዓለም ማኅበረሰብ አቢይ ድጋፍ እና ትብብር አስፈላጊ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ብፁዕ አቡነ ቹሊካት አክለውም፣ ምሥጢረ ተክሊል እና ወላጆች የልጆቻቸው ሕንጸት ጉዳይ በተመለተ ያለባቸው ኃላፊነት ማእከል በማድረግ፣ ምሥጢረ ተክሊክ በአንድ ወንድ እና በአንዲት ሴት መካከል የሚጸና ውህደት መሆኑ በማስረዳት፣ ወላጆች ለልጆቻቸው ሕንጸት ያለባቸው ኃላፊነት እንዲከበር አደራ በማለት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ የሚያሳስበው አንቀጽ ነው ካሉ በኋላ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ ከሰው ልጅ መሆን ውጭ የተገኘ ሳይሆን የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብር ዘንድ ያለ በባህርያዊ ግብረ ገብ የተረጋገጠ በእያንዳንዱ ሰው ልጅ ዘንድ ያለ ኵላዊነት ባህርያ ለበስ መሆኑ በማብራራት ያሰሙትን ንግግር እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.