2010-11-06 17:03:11

ርሊጳ ከዚህ ዓለም በሞት ስለተለዩ ካርዲናላት እና ጳጳሳት ሥርዓተ ቅዳሴ አሳርገዋል ፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በትናንትና ዕለት በቅዱስ ጰጥሮስ ካተድራል በዚሁ ዓመት ከዚህ ዓለም ለተለዩ ብፁዓን ካርዲናላት እና ጳጳሳት መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል።

በዚሁ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የተመራ መሥዋዕተ ቅዳሴ በርካታ ካርዲናልት ጳሳት እና ምእመናን ተሳታፊ ሁነዋል ።

ቅድስነታቸው በዚሁ መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከታቸው ላይ ክርስትና ምርጫ መሆኑ ከሄሉ ኩሉ ሉ እግዚአብሔር መሐሪ እንጂ ቀጪ እንዳልሆነ በክርስቶስ ለክርስቶስ ከክርስቶስ መኖር ማማለት ሁሉም ትቶ እሱን መከተል ማለት መሆኑ አመልክተው ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ጠቅሰው ክርስትያኖች የክርስቶስ ትንሳኤ አጋር መሆናቸው አስገንዘበዋል ።

ክርስትያን መሆን እና ክርስትያኖች እዚ ምድር ላይ በሚኖሩበት ግዜ ሁሉ ነገር መተው አለባቸው ማለት ሳይሆን የዓለም ነገራት ሁሉ ዘለዓለማውያን ነገሮች እንደሆኑ በመውሰድ በነሱ ተዘፍቀው መኖር አይገባም ማለት መሆኑ አመልክተዋል።

የሰው ልጅ በመጨረሻ ሕይወቱ ውደ ፈጠረው እግዚኣአብሔር እንደሚመለስ መዘንጋት የለበትም ባደረገው ሐጢአቶች ከልብ ከተጸጸተ እግዚአብሔር መሐሪ ነውና ምሕረቱ ይችርለታል በማለት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በስብከታቸው ላይ ገልጸዋል።

በዚች በምንኖርባት ምድር ሁሉም ሐላፊ ነው የእግዚአብሔር ጸጋ ከተቀዳጀን ግን ሐለፊ እንዳልሆነ ለዘለዓለማዊ ሕይወታችን የሚሸኘን እንደሆነ መሞት በክርስትያናዊ ራእይ ሲታይ ከክርስቶስ ትንሳኤ ጋር የተሳሰረ መሆኑ አስገንዝበዋል።

በዚሁ ዓመት ከዚህ ዓለም ወደ እግዚአብሔር የተመለሱ ስድስት ካርዲናላት ሊቀ ጳጳሳት እና ጳጳሳት በማስታወስ ለክርስቶስ የገቡለትን ቃል አክብረው በመንግስተ ሰማያት እንደሚገኙ ለኛ እንደሚጸልዩልን አመልክተዋል።

ዘለዓለማዊ ሕይወት በእግዚአብሔር ለሰው ልጅ የተሰጠ መለኮታዊ ስጦታ እንደሆነ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስገንዝበዋል።

ዘለዓለማዊ ሕይወት በክርስቶስ ትንሳኤ ሙታን ገሀድ የሆነ የእግዚአብሔር አጋር ማለት መሆኑ እና ወደ እግዚአብሔር መንግስት ለመድረስ ጽኑ እምነት እንደሚያሻ

ቅድስነታቸው በተጨማሪ ገልጸዋል።

እግዚአብሔር በአምሳሉ የፈጠረውን ሰው ስለሚወደው ልጁን ልኮ አድኖታል እሱ እንዳፈቅረን ሁሉ እኛም እሱን መውደድ ይጠበቅብናል፡ እግዚአብሔርን ማሳዘን አየገባንም ለደረገልን ሁል ባለውለታዎች መሆን አለብን ብለውል ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ።

እግዚአብሔር ስውን ምን ያህል እንደሚያፈቅረው በግብር አሳይቶታል ህልውናውን ገሀድ አድርጎለታል ምህረት ሰጥቶታል ምሕረቱ ገደብ የለውም ከሀሌ ኩሉነቱ በምሕረት እንጂ በቅጣት አላሳየም ታድያ የሰው ልጅ ይህንኑ ተረድቶ ምድራዊ ሕይወቱ ማስተካከል እንደሚጠበቅበት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስረድተዋል።በትንሳኤ ክርስቶስ ከክርስቶስ ጋር እንኑር ዱካው እንከተል እሱ እንደሚወደን እኛም በበለጠ እንውደደው መድኀኒ ነው እና ብለዋል ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ።








All the contents on this site are copyrighted ©.