2010-11-03 14:57:44

ከክርስቶስ ጋር ያለን ውህደት


የኢጣሊያ ስሜናዊ ክልል ጥቅላይ የቲዮሎጊያ መንበረ ጥበብ ምክትል ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ፔራንጀሎ ሰኵየሪ በላቲን ሥርዓት ትላንትና ታስቦ ስለ ዋለው ዕለተ ሙታን በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ቅዱስ አባታችን RealAudioMP3 ር.ሊ.ጳ. ቀኑን ምክንያት በማድረግ በሰጡት አስተምህሮ ሞትም ቢሆን ከክርስቶስ ጋር ያለንን ውህደት አያጠፋም፣ በዚህ ክርትያናዊ እውነት ከኛ የተለዩት ወድሞቻችን እህቶቻችን በጠቅላላ ከዚህ ዓለም በሞት ቀድመውን ተለይተው ያሉት፣ ለኛ ቅርብ መሆናቸው ክርስቶሳዊ ሓቅ ያረጋግጥልናል። ምክንያቱም በሞት ምክንያት ከዚህ ዓለም የሚለይ ሰው በበለጠ ለእግዚአብሔር ቅርብ ወደ ሚሆንበት ደረጃ ስለ ሚሸጋገር በበለጠ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ በበለጠ ለኛም ቅርብ ይሆናል። ለእግዚአብሔር እጅግ ቅርብ በመሆን በሚለገሰው ዓይነት ሕይወት አማካኝነት ወደ እግዚአብሔር ያቀረበው ቅርበት ከኛ የተለየው ወደ እኛ እንዲቀርብ ይገፋፋዋል።

ዕለታዊ ሕይወታችን በዘልማድ በመሰልቸት እና በተስፋ ቢስነት እንዳንኖር መጠንቀቅ የእኛ ኃላፊነት ነው። እያንዳንዱ ዕለት የማይደጋገም አዲስ ዕለት ነው። ዛሬ የዘራነውን ስለምናጭድ የምንዘራው ሁሉ በንኖ እንዳይቀር፣ ዕለታዊ ኑሮአችንን በሚገባ እንኑር እንምራ፣ ሕይወት ጸጋ መሆኑ ለመመስከር የሚያስችለውን መንገድ እንድንከተል የሚያሳስበን ዕለት ነው ብለዋል።

ወደ መቃብር ሥፍራ በመሄድ ለኅሊና ጸሎት መንፈሳዊ ንግደት መፈጸም የሚለው አቢይ ትርጉም ያለው ክርስትያናዊ ባህል መታቀብ የሚገባው ነው። ሆኖም ወደ መቃብር ሥፍራ በመሄድ የአበባ ጉንጉን ማኖር ለብቻው በቂ አይደለም፣ ስለዚህ ይህ መንፈስ በቅዱስ ቁርባን ለመሳተፍ የሚያነቃቃን ሊሆን ይገባዋል። ከኛ ከተለዩት ጋር የሚኖረን መንፈሳዊ ቅርበት ለመጠበቅ ቤተ ርክስትያን የምታቀርብልን ቅዱሳት ሚሥጥራት አሉን እነርሱን እንጠብቅ እንኑር በማለት የሰጡን ቃል ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.