2010-11-03 14:56:32

ትላንትና በላቲን ሥርዓት የሙታን ቀን ተዘክሮ ዋለ


በላቲን ሥርዓት ህዳር 2 ቀን ሁሉም ሙታን የሚዘከሩበት ዕለት ሲሆን፣ ዕለቱ ምክንያት በማድረግ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ሁሉን ሙታን ዘክራ ስትውል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ዕለቱን ምክንያት በማድረግ RealAudioMP3 ከቀትር በኋላ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ልክ 06.00 በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ መሬት ሥር ወደ ሚገኘው የርእሳነ ሊቃነ ጳጳሳት የመቃብር ሥፍራ በመሄድ በግል የኅሊና ጸሎት ማሳረጋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

እ.ኤ.አ. ህዳር 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን የሁሉም ቅዱሳን በዓል ምክንያት ልክ እኵለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግመው እንዳበቁ በሰጡት አስተምህሮ ህዳር 2 ቀን ሁሉም ሙታን የሚዘከሩበት እና ዜጎች ወደ መቃብር ሥፍራ መንፈሳዊ ንግደት በመፈጸም ስለ ሙታን በመጸለይ የተለያዩ መንፈሳዊ ተግባሮች በጋራም ሆነ በግል የሚፈጽሙበት ዕለት መሆኑ በማስታወስ፣ በሞት የሚለየው በሕይወት ላለው የሐዘን ምክንይት ቢሆንም፣ ሐዘናችን በቤተ ክርስትያን ጸሎት የተሸኘ ነው። ከክርስቶስ ጋር ያለን ውህደት በሞት አይረታም በሞት ምክንያት አይቋረጥም ሲሉ እ.ኤ.አ. ህዳር 2 ቀን 2005 ዓ.ም. ባቀረቡት ረቡዓዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የዘመኑ ሰው ዘለዓለማዊ ሕይወት በተስፋ ይጠብቃል ወይስ ዘለዓለማዊ ሕይወት የሥነ ፈጠራ እና የሥነ ተረት ጥናት ክፍል እንደሆነ አድርጎ ነው የሚገልጠው? የሚለውን ጥያቄ በማንሳት፣ ይኽ ጥያቄ የዘመኑ ሰው ምንኛ በምድራዊ ሃብት ተውጦ ታሪክ የሚሠራው እና ሕይወት የሚፈጥረው እግዚአብሔርን ማሰብ የተሳነው መሆኑ ያመለክትልናል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ ጠቅሶታል።

ህዳር 2 ቀን 2008 ዓ.ም. ለዘመኑ ሰው ስለ ሞት እና ዘለዓለማዊ ሕይወት ማእከል ያደረገ አስፍሆተ ወንጌል እንደሚያስፈልገው በማብራራት፣ የክርስትናው እውነት ስለ ሞት እና ሕይወት በተመለከተ ሥነ ተረት ከሚሰጠው አገላለጥ ጋር በማቀላለቅል እና በማመሳሰል ተደናግሮ እንዳይጨልም መጠንቀቅ ያስፈልጋል ሲሉ በሰጡት ረቡዓዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በማብራራት፣ ቅዱስ አጎስጢኖስ ሁሉም የተቀደሰ እና ፍጹም ደስተኛ ሕይወት ይሻል፣ ሆኖም ዘለዓለማዊው የተቀደሰ ሕይወት ምን እንደሚመስል ከወዲሁ ልምዱ እና ግምቱ’ኳ ባይኖረን ወደ ተቀደሰው ሕይወት የተማረክን መሆናችን ግንዛቤው በእኛ ቀልብ ዘንድ አለ። ይህ ደግሞ ኵላዊ ተስፋ ለሁሉም በህሉም ሥፍራ ለሚኖር ሰው የሚመለከት ነው። ዘለዓለማዊ ሕይወት ይኽ ኵላዊ ተስፋ ተብሎ የሚገለጠው ፍጻሜ የሌለው ከተለያዩ የተስፋ ደረጃዎች ውስጥ አንዱ ሳይሆን፣ ዘለዓለማዊ ሕይወት ማለት ፍጹሙ ወሰን አልቦ በሆነው ቅድሚያ የሚቀጥል ፍጻሜ በሚል የጊዜ ገደብ የማይለካ ፍቅር ውስጥ መስመጥ ማለት ነው። ከክርስቶስ ጋር መሆናቸው ላይ የጸና ተስፋ እና የምንጠብቀው የሕይወት ሙላት የደስታ ሙላት ማለት መሆኑ ቅዱስ አጎስጦኖስ እንዳብራራው ቅዱስነታቸው እንዳስታወሱ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ከሞት ተነስቻለሁ አሁን ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ የሚለው ጌታችን እየሱስ ክርቶስ በእጆቹ ይደግፈናል፣ በየትም ሥፍራ ብትወድቅ በእጆቼ ላይ ትገኛለህ፣ በሞት አፋፍ በምትገኝበት ዕለት ማንም ካንተ ጋር ሊሆን በማይችልበት ምንም ነገር እና ማንም ካንተ ጋር ልትወስድበት የማትችልበት ሞትህን ስቶሞት እዛው ካንተ ጋር እሆናለሁ ጨለማውን ወደ ብርኃን ለመለወጥ እዛው እጠብቅሃለሁ በሚለው አገላለጥ ዘለዓለማዊ ሕይወት ምን ማለት መሆኑ ህዳር 2 ቀን 2008 ዓ.ም. ረቡዓዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በሰጡበት ዕለት እንዳብራሩ ይዘከራል።








All the contents on this site are copyrighted ©.