2010-11-03 14:10:08

ርሊጳ በነዲክቶስ ለዒራቅ የሐዘን ተለግራም ላኩ፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ባለፈው ሰንበት በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡ ምእመናን ጋር መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በደገሙበት ግዜ በዒራቅ ባቅዳድ ላይ በሚገኘው አጽናኝ ቅድስቲ ድንግል ማርያም ቤተ ክርስትያን ውስጥ ሥርዓተ ቅድሴ በመከታተል ላይ እንዳሉ በአሸባሪዎች የተገደሉ ምእመናን አስታውሰው የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን መግለጣቸው የማይዘነጋ ነው።

የግድያው ሰለባ ስለሆኑ እንደሚጠልዩ እና ሰላም የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑ ጠቅሰው ዓለም አቀፍ ማሕበረ ሰብ ለመሃከለኛው ምስራቅ ሰላም እንድያፈላልግ መማጸናቸው ይታወሳል።

በዚሁ ዓመጽ ከሐምሳ የሚበልጡ ምእመናን መገደላቸው በርካታ መቁሰላቸው የተገለጠ ሲሆን በዚሁ ዓመጽ የተገደሉ ሁለት ካህናት የአባ ጣሂር ሰዓድ እና የአባ ቡጥሮስ ቃሲም የቀብር ሥርዓት ትናትና መፈጸሙ ተመልክተዋል።

ቅድስነታቸው በበቅዳድ የሲሮ ካቶሊክ ቤተ ክርስትትያን ሊቀ ጳጳስ ለብጹዕ አቡነ እታናሰ ማቲ ሻባ ማቶካ የሐዘን ተለግራም መላካቸው የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለባቅዳድ የላኩት የሐዘን ተለግራም ምእመናን በቤተ እግዚአብሔር ውስጥ እያሉ በግፍ መገደላቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን የሚገልጥ ተለግራሙ እግዚአብሔር በመንግስተ ሰማያት እንዲቀበላቸ ለቤተ ሰቦቻቸው እና ለዒራቅ ቤተክርስያን ጥናቱ እንዲሰጥ እንደሚጠልዩ ያስገነዘበ ተለግራም እንደሆነ መግለጫ አመልክተዋል።

ቅድስነታቸው ባቅዳድ ውስጥ በካቶሊካውያን ምእመናን ላይ በተፈጸመው የግድያ ተግባር በእጅጉ ማዘናቸው መግለጫ ገልጠዋል ።

በመንፈስ ከቤተ ክርስትያኒቱ እና ምእመናኑ አጠገብ መሆናቸው እና የስቃዩ ተሳታፊ እንደሆኑ ቅድስነታቸው በላኩት መልእክት አረጋግጠዋል ያለው የቫቲካን መግለጫ ሁኔታው አሳሳቢ መሆኑ ነው የሚያመለክተው።

አሸባሪዎች የወሰዱት እኩይ ርምጃ የዒራቅ ህዝብ የአብሮ መኖር ለማደናቀፍ እና የርስ በርስ መተማመን ለማጥፋት መሆኑ መግለጫው አክሎ አስገንዝበዋል።

ባቅዳድ ላይ በሚገኘው ካቶሊካዊ ቤተ ክስርትያን የፈሰሰው የንጹኀን ሰላማውያን ሰዎች ደም የዕርቅ እና የፍትሕ መሠረት እንዲሆን ጥላቻ እና አለመተማመን እንድያስወግድ መግለጫው አክሎ ገልጠዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ በዚሁ የግድያ ተግባር ለተገደሉ ሁለት ካህናት ባቅዳድ ውስጥ በሚገኘው የቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ፍትሐተ ጸሎት ያደረጉላቸው በሀገሪቱ የሞሱል ከተማ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ባዚለ ጆርጅስ ካስሙሳ እንደገለጡት፡ ግዜው ለዒራቅ ክርስትያን ማሕበረ ሰብ ሰብአዊ እና እምነታዊ መቅሰፍት የተከሰተበት እና ማሕበረ ሰቡ በካበድ ሐዘን የውደቀበት ግዜ መሆኑ ተናግረዋል።

የዒራቅ ክርስትያን ማሕበ ሰብ ከሊሎች ሃይማኖቶች በተለይ ክእስላሙ ጋር ለመወያየት እና ሀገሪቱ ውስጥ ሰላም ለማስፈን በጋራ ለመስራት በሚንቀሳቀስበት ግዜ ይህ ዓይነቱ ድርጊት ሲፈጸም ቃላት የማይገኝለት አሳዛኝ ድርጊት መሆኑ መግለፃቸውም ተዘግበዋል።

አያይዘውም የዒራቅ መንግስት ለሕብረተ ሰቡ ተገቢ ጥበቃ ባለመስጠቱ ወቅሰው እንዲህ ከሆነ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቀሩ የማሕበረ ሰቡ አባላት የግድያ ሰለባ ከመሆንቸው በፊት ጣልቃ እንድዲባ ያሻል ማለታቸው ተመልክተዋል።

የዒራቅ መንግስት ፕረሲደንት ኑሪ አልማሊቂ ባለፈው ሰንብት የተካሄደ የግድያ ተግባር በክርስትያኖች ላይ ያነጣጠረ ጸረ ሰላም ተግባር መሆኑ ጠቅሰው ተግባሩን ኰንነውታል ተብሎ ተገልጠዋል።

የእህዱ ጥቃት የዒራቅ የሰላም ሂደት ለማደናቀፍ እና የሀገሪቱ ህዝብን ሰላም ለመንሳት የታቀደ መሆኑ በርካታ የዒራቅ የመንግስት እና ሲቪል ባለስልጣናት እንዳመኑበት ተነግረዋል። ይሁን እና ይህ ባለፈው እሁድ ዕለት ባቅዳድ ወስጥ በአንድ ሳጂዳት አል ናዛ በተባለች ካቶሊካዊት በተክርስትያን ውስጥ አክራሪ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር የዋሉ

ክርስትያኖች ሴቶች እና ሕጻናት ጨምሮ ከሐምሳ በላይ መገደላቸው እና ሰባ ስምንት ከባድ እና ቁላል መቁሰልት እንደደረሰባቸው የሚታወስ ሲሆን ፡ድርጊቱ ለሀገሪቱ ቤተክርስትያን እና ምእመናን ብቻ ሳይሆን ሀገራት አቀፍ ማሕበረ ሰብን እጅግ ማሳዘኑ እና ማስደንገጡ እና የሀገሪቱ ክርስትያኖች ምን ያህል ለአደጋ መጋለጣቸው ገሀድ ያደረገ ድርጊት መሆኑንም እየተነገረ ነው።

ዒራቅ ውስጥ ንዑሳን ማሕበረ ሰባት መብት የሚጠብቅ መንግስት አስፈላጊ መሆኑንም ተያይዞ እየተገለጠ ነው ።

ግድያው የፈጸመ አልቃዒዳ የተባለ የእስላም አክራሪ ቡድን መሆኑ ራሱ አምኖ መግለጹም ተመልክተዋል።

ሽብርተኛ ቡድኑ በዒራቅ እና ግብጽ ወህኒ ቤቶች እስርቤት ውስጥ የሚገኙ አባላቱ ነጻ እንዲወጡ ክርስትያኖችን ማገቱም መግለጹ እየተነገረ ነው።

ይህ አልቃዒዳ የተባለ ሽብርተኛ ቡድን ለሰው ሕይወት ደንታ ቢስ ለሃይማኖቶች ክብር የማይሰጥ እኩይ ቡድን መሆኑ በዚሁ ባለፈ ሰንበት የፈጸመው ተግባር ማረጋገጡ እና በዓረብ ዓለም የሚኖሩ ክርስትያኖች የተደቀነባቸው አደጋ ከባድ መሆኑ መታየቱ ተመልክተዋል።





የሳዳም ሑሴን ፈላጭ ቁራጭ መንግስት ከወደቀ ወዲህ አንድ ሚልዮን የዒራቅ ክርስትያኖች ሀገራቸው ጥለው እንዲሰደዱ መገደዳቸው እዚያው የቀሩት በአንድ ሚልዮን ተኩል የሚገመቱም በሰላም ለመኖር እንደማይችሉ እየተረዱ መምጣታቸው እና አሳዛኝ መሆኑ ባቅዳድ ላይ የሚወጡ መግለጫዎች ያመለክታሉ።

በአጠቃላይ ስር ሰደድ የመሃከለኛው ምስራቅ የፖሊቲካ ውዝግብ የእምነት እና ሃይማኖት ነጻነት እንዲከበር የዓለም ሕብረተ ሰብ ቀዳሚ ዓላማው በማድረግ እንዲንቀሳቀስ የሚጠይቅበት ወቅት መሆኑም እየተገለጸ ነው።

ይሁን እና የዒራቅ መንግስት የመከላከያ ሚኒስትር ዓብደል ቃድር ኦቤዲ እንደገለጹት ባለፈው ሰንበት አምስት ሽብርተኞች መገላቸው ጠቅሰው የሀገሪቱን ፖሊስ ማመስገናቸው ተሰምተዋል።

የባቅዳድ አስተዳዳሪ በበኩላቸው ሲገልጡ አሸባሪዎቹ ክርስትያኖች ከሀገሪቱ ለማባረር በማቀድ የወሰዱት እኩይ ተግባር ነው በማለት ድርጊቱንም ማውገዛቸው ተገልጸዋል።

በሌላ በኩል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቀዋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ፍራንሲስ ቻሊካት ባቅዳድ ውስጥ በክርስትያኖች ላይ የተወሰደው አስቃቂ የግድያ ተግባር በማሳሰብ ዓለም አቀፍ ድርጅቱ የእምነት ነጻነት እንድያረጋግጥ አጽንኦት ሰጥተው መጠየቃቸው ከኒውዮርክ የደረሰ ዜና አመልክተዋል።

እንዲህ የባቅዳድ ዓይነቱ የወጣለት የግፍ ተግባር በማውገዝ ብቻ የሚታለፍ ሳይሆን የእምነት ነጻነት ለማረጋገጥ ሁነኛ ርምጃ እንዲወሰድ አጽንኦት ሰጥተው ድርጅቱን መጠየቃቸው አብሮ የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።

ብፁዕ አቡነ ፍራሲስ ቻሊካት በዒራቅ እና ዮርዳኖስ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል በመሆን ለበርካታ ዓመታት የሰሩ መሆናቸው የሚታወስ ነው ።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ የባቅዳድ ፍጻሜ አሳዛኝ እና አሳፋሪ ድርጊት መሆኑ ዓለም አቀፍ የአብያተ ክርስትያናት አንድነት ዋና ጽሐፊ ቄስ ኦላቭ ተቪት ይፋዊ መግለጫ መስጠታቸው ተመልክተዋል።

ይህ በአኅጽሮተ ቃል CEC የሚጠራ የአብያተ ክርስትያናት አንድነት ምክር ቤት ማለት አንገሊካዊት ኦርቶዶክሳዊት እና ፕሮተስታንት 349 አብያተ ክርስትያናት አቀፍ መቀመጫው በስዊትጸርላንድ ጀነቭ ላይ ያደረገ ምክር ቤት 560 ሚልዮን ህዝብ ክርስትያኖች እንደሚያጠቃልል ይታወሳል።








All the contents on this site are copyrighted ©.