2010-11-03 14:58:53

ማላዊ፦ ሁሉም ለጋራ ጥቅም ይነቃ ዘንድ


የማላዊ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የጋራ ጥቅም ማስጠበቂያ መሠረታዊ መመሪያ በእውነት ላይ የጸናው ፍቅር ለድኾች ቅን አሳቢነት መርህ በማድረግ ሁሉም በጋራ ለአገር እና ለዜጋ ጥቅም በሚል ርእስ ሥር ባስተላለፉት አገር አቀፍ መልእክት RealAudioMP3 ባለፈው እሁድ ይፋ መውጣቱ ለማወቅ ሲቻል፣ ወቅታዊው ሁኔታ የሚለውን መልእክት ቀርቦ በጽሞና ማዳመጥ እና በጥልቀ ልብ በማንበብ ቤተ ክርስትያን መንግሥት እና ዜጎች ችላ ሊሉት የማይገባው እርሱም መጪው የማሊ ተስፈኛ ሕይወት ከወዲሁ ተገቢው መንገድ ይከተል ዘንድ፣ ቅንነት የተሞላው ስለ አገር እና ዜጎች ጥቅም ያቀና የውይይት መድረክ መሆኑ ብፁዓን ጳጳሳት በማመልከት፣ በዚህ ሚና ምእመናን ተቀዳሚውን ሥፍራ በመያዝ በቃል እና በሕይወት ምስክርነት የተካነ አስተዋጽኦ እንደሚጠበቅባቸው ያሳስባሉ።

ብፁዓን ጳጳሳት ባስተላለፉት መልእክት ያለው እና ወቅታዊው የአገራቸውን ሁኔታ በመዳሰስ፣ በአሁኑ ወቅት መንግሥት የአገሪቱ ሕዝብ የምግብ ዋስትና ይረጋገጥለት ዘንድ እያረማመደው ያለው ጥረት እና በጠቅላላ የእርሻ ፖለቲካ ጉዳይ በተመለከተ የግብርናው ልማት ለማፋጠን እና ልማቱ የሕዝብ የምግብ ፍላጎት የሚያረካ እንዲሆን የሚለው ውሳኔ ቅድሚያ በመስጠት የአገልግሎት መስጫ መዋቅሮች ማኖር የትርንስፖርት እና የመገናኛ ጉዳይ በሙላት ማረጋገጥ በተሰኘው መርሃ ግብር መሠረት እያከናወነው ያለው አቢይ ጥረት እውቅና በመስጠት እንዲሁም በሕንጸት ዘርፍ አወንታዊ ውጤቶች እየተረጋገጡ መሆናቸው በመጠቅስ፣ የውጭ ድጋፍ እና ትብብር አስፈላጊ ቢሆንም ይህ መንገድ መሠረታዊ የሕዝብ እና የአገር ጥቅም ማረጋገጫ መሆን አይችልን፣ ስለዚህ ራስን የመቻል ምርጫ በሁሉም መስክ ዋናው ዓላማ ይሆን ዘንድ ብፁዓን ጳጳሳት ባስተላለፉት መልእክት አስምረውበታል።

በመጨርሻም የአገሪቱ በፁዓን ጳጳሳት የአገራቸው ወቅታዊው የፖለቲካ ሁኔታ ርእስ በማድረግ፣ በአገሪቱ የዲሞክራሲው ሥርዓት በሙላት ይሰፍን ዘንድ በማሳሰብ በአገር ደረጃ ብቻ ሳይሆን በፖሊቲካ ሰልፎች ውስጥ ዴሞክራሲያዊ አመራር እና አሰራር በአገሪቱ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋስትና መሆኑ በመግለጥ፣ በመጨረሻ የማላዊ የመገናኝ ብዙሃን ፖለቲካ ጉዳይ በመጥቀስ በሕዝብ የግብር ክፍያ አስተዋጽኦ የጸናው የመገናኛ ብዙሃን ሕዝብ በተገባው መንገድ ተገቢ ማስታወቂያ እና ዜና ብሎም ስለ አገሩ አለ ምንም ህቡእ ዓላማ ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖረው ማገዝ ግዴታ እንዳለባቸው አሳስበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.