2010-11-01 13:14:03

የቅዱስ አባታችን መልእክት ለካቶሊክ ተግባር ማኅበር


ከትላንትና በስትያ ከመቶ ሺሕ በላይ የሚገመቱ የካቶሊክ ተግባር ወጣቶች ማኅበር አባላት፣ የማኅበሩ የሕንጸት መሪዎች ምእመናን ካህናት እና ብፁዓን ጳጳሳት የሚገኙበት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከቅዱስ አባታችን ጋር ከቅዱስ አባታችን ጋር በመገናኘት መሪ ቃል መቀበላቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

እነዚህ የካቶሊክ ተግባር ማኅበር አባላት ወጣቶች፣ በመቀጠል RealAudioMP3 ሮማ በሚገኘው በሲየና እና በሕዝባዊ አደባባይ የመንፈሳዊ መዝሙር የምስክርነት የተለያዩ ሃይማኖታዊ መግለጫ መርሃ ግብሮች እንዳከናወኑ ለማወቅ ሲቻል፣ ከሩሲያ ከሮማኒያ ከአርጀንቲና ከብሩንዲ ከቅድስት መሬት ከኢጣሊያ ከተለያዩ ሌሎች አገርች የተወጣጡ የተሳተፉበት በጠቅላላ 100 ሺሕ ወጣት የካቶሊክ ተግባር ማኅበር አባላት፣ 10 ሺሕ አስተማሪዎች 500 ካህናት 50 ብፁዓን ጳጳሳት ተሳታፊ ሆነዋል።

ቅዱስ አባታችን ከካቶሊክ ተግባር ወጣቶች ጋር በመገናኘት ዕለቱ የእምነት በዓል ነው ሲሉ፣ የእምነት ደስታ እና ተሰፋ የሚከበርበት ጭምር መሆኑ ቅዱስነታቸው እየሱስ የሌለበት ሥፍራ እንዳይኖር፣ ዘወትር ብርቱዎች ሁኑ በማለት ያቀረቡት ጥሪ የካቶሊክ ተግባር ማህበር ሊቀ መንበር ፍራንኮ ሚያኖ፣ የቅዱስ አባታችን መልእክት እምነት እንዲኖረን ታማኞች እንድንሆን ችግር በሚያጋጥም ወቅት ተስፋ ለሰው ልጅ የተገባ ክብር ያለው አድማስ መሆን እንደማያቋርጥ ያረጋገጠ መልእክት ነበር ሲሉ፣ የካቶሊክ ተግባር ማኅበር አበ ነፍስ ብፁዕ አቡነ ዶመኒኮ ሲጋሊኒ፣ ወጣቱ በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እንዲህ ባለ መልኵ ተሰባስቦ ስታይ አቢያተ ክርስትያን አለ ወጣት ቀርተዋል የሚለው አነጋገር መሠረት የሌለው እንደሆነ ትረዳለህ ሲሉ፣ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በወጣቶች ጉዳይ በተመለከተ ያላቸው ሚና ላይ ያተኮረ ንግግር ሲያሰሙ፣ ቅዱስ አባታችን ስለ እየሱስ በመናገር የእርሱ እውነተኛው ገጹን በመጠቆም በትክክለኛው የእምነት መንገድ እንድንገኝ ማድረግ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን የሚያሰጠው ደስታ እና በቤተ ክርስትያን መሆናችንን ያለው ተስፋ ያረጋግጥሉናል ብለዋል። የእየሱስ ጓደኞች ለቤተ ክርስትያን እና ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ያላቸው ፍቅር ለመመስከር በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ መሰብሰቡንም አመልክተዋል።

ቅዱስ አባታችን ለታዳጊ ወጣት የካቶልክ ተግባር ማኅበር አባላት ባስተላለፉት መልእክት፣ ወደ ኋላ መለስ ብለው የሕጻንነት የታዳጊ ወጣት ታሪካቸውን በመቃኘት፣ በሕጻናት ላይ ያለው ታላቅነት ለይቶ ያወቀው ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ብቻ መሆኑ ሲያስረዱ፣ በሕፃናት ዘንድ ያለው ትልቅነት አድጊያለሁ በሚለው ጎልማሳው ዘንድ መኖር አለበት፣ ይህ በሕፃን ዘንድ ያለው ትልቅነት፣ የዋህነት ታማኝነት እማኝነት ቅንነት የሚያጎላ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ጠቅሰው፣ እነዚህ የሰብአዊ ጥራት መመዘኛ በሕፃናት ዘንድ ያሉ ናቸው። ስለዚህ ያደገው ሰው ታላቅነት በነዚህ መመዘኛዎች የሚለካ ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት ፍቅር አንዱ የፍጆት ክፍል እየሆነ ሲቸረቸር ለገበያ ሲወርድ ይታያል፣ ፍቅር የሰው ልጅ ከራስ ክብር ማክበር እና ካለው ሰብአዊ ክብር እራሱን በማዋረድ የሚገዛ እና የሚሸጥ እያደረገ እራሱን እና ሌላውን ሲያዋርድ ይታያል። እራስን አለ ማክበር ለሌላው ላለ ማክበር መንገድ ነው፣ ዓለማችን ንጽሕናን እና ድንግልናን መኖር ተስኖት እንዲሁም የማይቻል ሕይወት እንደሆነ በማሰብ እና በመስበክ ከማክበሩ ውሳኔ ተገሎ ይገኛል፣ እንዳሻኝ የሚለው ውሳኔ እውነተኛ ነጻነት እንዳልሆነ ገልጠው፣ በመገናኛ ብዙሃን የሚነዛው ፍቅር፣ ፍቅር ሳይሆን ራስ ወዳድነት፣ ለእኔ ባይነት እኔነትን ማእከል ያደረገ ስስታምነትን የሚያንጸባር በራሱ ውስጥ የተዘጋ ከተጨባጩ ሓቅ የተለየ ቅንነት የሌለው በቕዥት ማዕበል የሚገፋ ሰውን በሳል እንዳይሆን በማገድ ወደ ኋላ የሚጎት ደስታን የሚቀጭ እውነተኛ የልብ ስሜት እና እውነተኛው ግፊት በማፈን በእየሱስ የሚገኘው ፍጽሙ መግለጫው መንፈስ ቅዱስ የሆነው ከአብ የሚሰጠው እውነተኛው እና የተዋበው ፍቅር እንዳይኖር የሚያደርግ መሆኑ አብራርተው፣ አክለውም አስተማሪዎችን በመመልከት፣ አስተማሪ የእውነተኛው የልብ ደስታ በመመስከር ሕይወት ዘወትር መቼም ቢሆን በሁሉም ሥፍራ ውበት እና መልካም መሆኑ የሚያስረዱ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ይህ ማለት ደግሞ ይላሉ ቅዱስነታቸው፣ በእየሱስ የተገለጠው ሕይወት እና መንገድ በመከተል እርሱን ለማፍቀር ከእርሱ የተሰጠው ነጻነት፣ የሕይወት ዘይቤ በአብ ፍቅር ላይ ያለው ፍጹም እምነት መከተል ማለት ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.