2010-11-01 13:17:34

ክርስትያን ምእመናን እና ሙስሊሞች ለኅብረ-ሃይማኖት ውይይት


ፎኮላሪኒ ማለትም አፍቅሮተ ዘ ቤተ የተሰየመው የካቶሊክ እንቅስቃሴ በኢጣሊያ የሙስሊሞች ማኅበረሰብ በመተባበር “በጋራው የወንድማማችነት ጉዞ፦ ሙስሊሞች እና ክርስትያኖች በኢጣሊያ” በሚል መርህ ቃል ትላትና በፊረንዜ RealAudioMP3 ሎፒያኖ ክልል የኅብረ-ሃይማኖት ውይይት ቀን ሙስሊሞች እና ክርስትያን ማኅበረሰብ በጋራ ማክበራቸው ተገለጠ። ይህ ሰላም የተካነው ማኅበራዊ ኑሮ ተቻይ መሆኑ ለመመስከር አልሞ የተከናወነው የሁለቱ ሃይማኖት የጋራው ውይይት በአሁኑ ወቅት በስፋት ለሚታየው ማኅበራዊ ፍርሃት ተገቢ መልስ መሆኑ ማራጋገጥ የሚለው ክብር ያጎላው የጋራው ግኑኝነት በተመለከተ የፎኮላሪኒ ካቶሊክ እንቅስቃሴ በትሬቪዞ የኅብረ ሃይማኖት ውይይት ጉዳይ ተጠሪ ቫለንቲና ማካካሮ እና በኢጣሊያ ቨነቶ ክፍለ ሃገር የሙስሊሞች መንፈሳዊ መሪ ኢማም ካመል ላያኪ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በኢጣሊያ ክርስያን እና ሙስሊሞች ማኅበረሰብ ያነቃቁት የጋራው ውይይት ከሩቅ ዓመታት የተጀመረ ቀጣይነቱ በህሉቱ ሃይማኖቶች ዋስትና ያገኘ ብቻ ሳይሆን፣ እቅዱ ከቨነቶ ክፍለ ሃገር ተነስቶ በጠቅላላ የኢጣሊያ ክፍለ አገሮች ጭምር እየተስፋፋ ብሎም ወደ ብሔራዊ አቀፍ ደረጃ ከፍ እንዳለም በመጥቀስ፣ ዓላማውም ኵላዊ ወድማማችነትን ለማረጋገጥ መሆኑ ቫለንቲና ማካካሮ አስታውቀዋል።

ኢማም ካመል ይህ በየዓመቱ የሚካሄደው የጋራው ውይይት እጹብ ድንቅ ዓላማ፣ ከዓመት ወደ ዓመት የጋራው ውይይት የሚያጎላው ውበት ከሃይማኖት ልዩነት ባሻገር ሁሉንም እየማረከ የእግዚአብሔር ፍጥረት ለማፍቀር በክርስትናው እና በምስልምናው ሃይማኖት ያለው የላቀው እሰይታ የሚያንጸባርቀው የጋራው ክብር የሚያጎላ ነው። ስለዚህ ሁሉም በአንድ የእግዚአብሔር ኅልውና በሚያምኑ ሃይማኖቶች “ወዳጅህን እንደራስህ አፍቅር፣ ላንተ ሊደረግልህ የምትሻው ሁሉ ለሌላው አድርግ፣ ሊደረግብህ የማትሻው አንተም አታድርግ” የሚለው ወርቃማው መመሪያ ማእከል በማድረግ በአንድ እግዚአብሔርነት የሚያምኑ ሃይማኖቶች መካከል መቀራረብ መከባበር እና በሰላም መኖር የሚያሳስብ ብቻ ሳይሆን የሚመሰክር ዕለት ነው ብለዋል።

ማካካሮ ይላሉ ሌላው ካንተ በባህል በቋንቋ እና በሃይማኖትም ጭምር የተለየው ዛቻ እንዳልሆነ ለማስተማር እና የሕይወት ባህል ወድማማችነት እና ወዳጅነትን በማረማመድ በክርስትያን እና በሙስሊሞች መካከል ውይይት የሚቻል ብቻ ሳይሆን ሰላም ለመገንባት ጭምር መሠረት መሆኑ የሚመሰከርበት ዕለት ነው ብለዋል።

ይህ በእዲህ እንዳለ በተለያዩ አቢያተ ክርስትያን ውህደት በተለያዩ ሃይማኖች መካከል ውይይት የሚያነቃቃው የኅብረ ሃይማኖት ዓለማውያን እንቅስቃሴ በአቢያተ ክርስያን መካከል ውህደት እንዲረጋገጥ በዚሁ ጉዳይ ላይ ያነጣጠረ ሕንጸት ውይይት አስተንትኖ እና ጸሎት ያካታተ መርኃ ግብር በሮማ የካማልዶአውያን መናንያን ማኅበር በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ፣ ሰላማዊ የጋራው ኑሮ ዋስትና እንዲኖረው እና በሁሉም ሃይማኖቶች ዘንድ ለጋራው ውይይህ ግንዛቤ እና አስፈላጊነቱንም ለማነቃቃት እና ቅድሚያ እንዲሰጠው በክርስትናው እና በአይሁድ ሃይማኖት መካከል ካለው ግኑኝነት በመነሳት ውህደት እና ግኑንነት ለማነቃቃት ያለመ መሆኑ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.