2010-11-01 13:16:11

ብፁዕ ኣቡነ ፊሲከላ፦ቃልን እና ተግባርን የሚያጣምር ንቃት


የኅሊና ቀዳሚነት በሚል ርእስ ሥር ለዝክረ ቅዱስ ቶማስ ሞር የተደረሰው መጽሐፍ በኢጣልያ የሕዝብ ተወካዮች ምርክ ቤት የጉባኤ አዳራሽ ለንባብ ለማብቃት በተካሄደው አውደ ጥናት ንግግር በማሰማት የተሳተፉት፣ RealAudioMP3 የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር እ.ኤ.አ. ኅዳር 20 ቀን 2010 ዓ.ም. የካርዲናል ማዕርግ እንዲቀበሉ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 ብቁ ከተባሉት 24 ሊቀ ጳጳሳት ውስጥ አንዱ ብፁዕ ኣቡነ ሪኖ ፊሲከላ፣ ቃል እና ተግባር የሚያጣምር ንቃት የፖለቲካው ዓለም የሚጠይቀው መመዘኛ ነው እንዳሉ ለማወቅ ሲቻል፣ ብፁዕነታቸው ይህ የኅሊና ቀዳሚነት በሁሉም ዘርፍ ወሳኝ መሆኑ በጥልቀት የሚተነትነው መጽሓፍ፣ ቶማስ ሞር ካለ ማመንታት በመኖር የእንግልጣር ንጉሥ በቤተ ክርስትያን ላይ ልዑል ማለት የበላይነት አላቸው የሚለውን ውሳኔ በመቃወሙ ምክንያት ከነበረው አቢይ የፖለቲካ ሥልጣን እንዲወርድ ብቻ ሳይሆን ንጉሥን መካድ በሚለው ክስ መሠረት ለሞት ፍርድ ተላልፎ የመሰከረው እምነት እና የኅሊና ቀዳሚነት ምስክርነት ትላትና ዛሬም ነገም በማንም ሊሻር የማይገባው ውሳኔ ነው ብለዋል።

ቃልን እና ተግባርን የማጣመሩ ንቃት በሁሉም ዘርፍ መኖር የሚገባው የግብረ ገብ እና የሥነ ምግባር መመሪያ፣ በፖለቲካ መድረክ በህዝባውያን ጉዳዮች ዘርፍ ተሰማርቶ ለሚያገለግለው ዋና መመዘኛ ነው። ስለዚህ ሰላም እና መረጋጋት ባለበት ወቅት ብቻ ሳይሆን ችግር ባለበት ጊዜም ይሁም መሥዋዕትነት ቢጠይቅም፣ መኖር የሚገባው ውሳኔ መሆኑ አብራርተዋል። ብፁዕነታቸው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ቅዱስ አባታችን እና የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ በመደጋገም በፖለቲካ ጉዳይ ተሰማርተው የሚያገለግሉት ካቶሊክ ምእመናን እምነት በፈረቃ ከመኖር ምርጫ ተቆጥበው የላቀው ሥነ ምግባር እና ግብረ ገብ የተካነው ሕይወት መስካሪያን መሆን ይገባቸዋል። የፖለቲካ አካላት ብቻ ሳይሆን ሁሉም በተሰማራበት መስክ የዚህ መመሪያ ተከታይ እና እግብር ላይ የሚያውል መሆን ይጠበቅበታል፣ ግዴታም ኃላፊነትም ነው ብለዋል።

ከማንኛው ዓይነት ሃይማኖት ነጻ የሆነ መንግሥት ማለት ጸረ ኅሊና መንግሥት ማለት አይደለም ስለዚህ ፖለቲካ ከሃይማኖት ነጻ ቢሆንም ቅሉ ለኅሊና ድምጽ ተገዥ መሆን አለበት የዚህ ኅያው ምስክር ቅዱስ ቶማስ ሞር ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.