2010-11-01 13:50:05

መሓሪው የእግዚአብሔር ፍቅር በሃብት ታውሮ የደረቀውን ልብ በማለስለስ ወደ ንስሓ ይመራል፤


 ኣዎ፤ እግዚአብሔር ማንንም ኣይለይም፤ ድሆች ይሁኑ ሃብታሞች በእግዚአብሔር የተመረጡ ናቸው፤እግዚአብሔር እንደኛ በሰብኣዊ ቅድመ ፍርድ ኣይወሰንም፤ በእያንዳንዳችን መዳን ያለባት ነፍስ ያያል።

ቅዱስነታቸው ትናንት ረፋድ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ባስተማሩት የመል አከ እግዚአብሔር ጉባኤ ኣስተምህሮ ላይ የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመጥቀስ፤ ጌታ ዘኬዎስን እንደመረጠ ሁሉ በእያንዳንዳችን የምትድን ነፍስ እንዳለች በመመለክት ዋና ትኲረቱ ኃጢኣተኞችን መዳን መሆኑን ኣስተምረዋል።

በላቲኑ ሥርዓተ ኣምልኮ የትናንትና ቃለ ወንጌል ከሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 19 የተወሰደ ስለ ዘኬዎስ የሚናገር ክፍል ነበር።

ቅዱስነታቸው ቃል ወንጌሉ የኢየሱስ ምሕረት ለማን እንድሚያስፈልግ ልክ በሉቃስ ወንጌል 5፡31/2 ‘ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤  ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም’ እንዳለው ሁሉ በዛሬው ወንጌል ደግሞ ጌታ ኢየሱስ ዘኬዎስን ‘ዘኬዎስ ሆይ፥ ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛልና ፈጥነህ ውረድ’ ብሎ መሓሪ ፍቅሩን ሲገልጥለት እውነትም ኃጢኣተኞችን ወደ ንስሓ ለመጥራት እንደመጣ ያመለክታል በማለት፤ ይህንን ታላቅ የጌታ ምሕረት እንዲህ ሲሉ ገልጠውታል፤ ‘እግዚአብሔር ማንንም ከግምት ውጭ ኣያደርገም፤ ድሆችም ይሁኑ ሃብታሞች፤እግዚአብሔር እንደኛ በሰብኣዊ ቅድመ ፍርዶቻችን ኣይወሰንም፤ በእያንዳንዳችን መዳን ያለባት ነፍስ ያያል በተለይ ደግሞ በኣመለካከታችን እንደጠፉ በሚቆጠሩ ላይ ልዩ ትኲረት ያደርጋል’ ሲሉ የዘኬዎስ ኣብነት ይህንን እንደሚያመልከት ኣብራርተዋል።

የእግዚአብሔር መሓሪ ፍቅር ‘ጻድቃንን ሳይሆን ኃጢኣተኞችን ለመጥራት’ በመጣው ኢየሱስ እንደሚያንጸባርቅ ሲያብራሩም፤ ‘የእግዚአብሔር ምሥጢረ ሥጋዌ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ የዚህ፤ ኃጢኣተኛን ለመዳን እንጂ በኃጢኣት ክብደት ላይ የማይመለከት ወደር የሌለው ምሕረት ዋና ዓላማ ኃጢኣተኛው ተጸጽቶ ንስሓ እንዲገባን እንደገና ኣዲስ ሕይወት ለመጀመር መሆኑን ኣሳይቶናል፤’ ብለዋል።

ዘኬዎስ የዚህ የንስሓ መንገድ ያሳየናል፤ ዘኬዎስ ሃብታም ነበር፤ ብዙዎችም ይጠሉት ነበር፤ ጌታ ‘ዘኬዎስ ሆይ፥ ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛልና ፈጥነህ ውረድ’ ባለው ግዜ ለብዙዎች ዕንቅፋት ሆነዋል። ጌታ ግን የሚያደርገውን ያውቅ ነበር።

‘ጌታ ኣደገኛ የሆነውን ሙከራ ለማድረግ ፈለገ፤ አሸነፈም፤ ዘኬዎስ በኢየሱስ ተግባር እጅግ ስለተነካ ሕይወቱን ለመለወጥ ይወስናል፤ “ጌታ ሆይ፥ ካለኝ ሁሉ እኵሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ፤ ማንንም በሐሰት ከስሼ እንደ ሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ” ብሎም ቃል ይገባል፤ ኢየሱስም ‘ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል፤’ በማለት ስለተፈጸመው ጉዳይ ኣብራርቶ እግረ መንገዱ ‘የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአል’ ሲል ተል ዕኮውን ይፋ ያደርጋል።

ቅዱስነታቸው በዛሬው ወንጌል ስላለው ሌላ መል እክት ሲያብራሩም ጌታ በወንጌለ ማቴዎስ 19፡23 ላይ ‘እውነት እላችኋለሁ፥ ለባለጠጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ጭንቅ ነው።’ ያለው በዘኬዎስ ጉዳይ የማይቻል የሚመስለው በጌታ ኃይል እንደሚቻል ማመልከቱን እንዲህ ሲሉ ገልጠዋ፤ ቅዱስ ጅሮም እንዳለው ዘኬዎስ ወዲያውኑ የዚህን ዓለም ሃብት ጥሎ በሰማያዊ ሃብት እንደተካው ይገልጣል፤ ቅድሱ ማሲሞ ዘቶሪኖም ሃብት ለሞኞች የጥፋት መሣርያ ሲሆን ለጥበበኞች ግን ሰማያዊ ሃብት ለማካበት ደጋፍ ነው፤ ለእነዚህ የድኅነት ዕድል ሲሰጥ ለሞኞች ግን ወደ ጥፋት የሚጠልፍ ይሆናል’ ያሉት በመጥቀስ የሃብት ጥቅምና ኣደጋኛነት ካብራሩ በኋላ በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ በነበሩ ም እመናንና ነጋድያ መለስ ብለው፤ ‘ውድ ጓደኞቼ፤ ኢየሱስ በመጀመርያ በተቀበለው መሠረት ዘኬዎስ ኢየሱስን ተቀበለ፤ ተለወጠም፤ ኢየሱስ ወደ ለዘኬዎስ ድኅነት ወደ እርሱ ሂዶ ተገናኘው እንጂ በሩቁ ኣልኰነነውም፤ ከኢየሱስ ጋር የፍጹም ኣንድነት ኣብነት ለሆነችው ድንግል ማርያም እኛም የእግዚአብሔር ልጅ ጉብኝት ጣዕምን እንድናገኝና በፍቅሩ በመታደስ ምሕረቱን ለሌሎች እንድናስተላልፍ ትረዳን ዘንድ እንለምናት፤ በማለት ትምህርታቸውን ፈጽመው የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ኣሳርገዋል።

ቅዱስነታቸው ከመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት በኋላ ከትናንትና ወዲያ ቅዳሜ ዕለት በኦራደያ ካተድራል በሩማንያ የጳጳስና ሰማዕት ኣቡነ እሲላርድ ቦግዳንፉ ሥር ዓተ ብፅ ዕና መታወጁን ኣስታውሰዋል፤ ኣቡነ እሲላርድ በ1949 ዓም የ38 ዓመት ዕድሜ በነበራቸው ወቅት ጳጳስ ተሠይመው ወዲያውኑ በሩማንያ ኮሚኒስት እስር ቤት ተወስደው ለኣራት ዓመታት ያህል ተሰቃይተው ተዋርደው በእስር ቤት የሞቱ ጳጳስና ሰማዕት ነበሩ።

በግ ዐ እግዚአብሔር የሆነ ኢየሱስን እስከ መጨረሻ ሕይወቱ የተከተለ ጀግና እርኛ ስለሰጠን እግዚኣብሔርን እናመስግነው፤ ምስክርነቱ ዛሬም በጌታ ወንጌል ምክንያት ለሚሰደዱ ያጽናና’ ካሉ በኋላ በተለያዩ ቋንቋዎች ኣመስግነው ሓዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.