2010-10-30 15:22:31

ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ፦የሊጡርጊያ ቲዮሎጊያ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ገና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከመመረጣቸው በፊት እ.ኢ.አ. ከሩቅ 1964 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2004 ዓ.ም. ባላቸው የቲዮሎጊያ ሊቅነት መሠረት ስለ ሊጡርጊያ በተመለከተ የሰጡት ቲዮሎጊያዊ ትንተና በተከታታይ ያጠቃለለ አቢይ ድርስት በቫቲካን ታትሞ የወጣው አንደኛው የመጽሓፍ በቫቲካን የኢጣሊያ ልኡከ መንግሥት ሕንፃ የቅድስት RealAudioMP3 መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ የኢጣሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒ. ጃኒ ሌታ ሮማ በሚገኘው ላ ሳፔንዛ መንበረ ጥበብ የወቅታዊ ታሪክ መምህር የታሪክ ሊቅ ሉቼታ ስካራፊያ በራቲስቦና በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ስም ለሚጠራው ተቋም ምክትል አስተዳዳሪ ክሪስቲያን ሻለር በተገኙበተ እና ንግግር ባሰሙበት መድረክ በይፋ ለንባብ መቅረቡ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ይህ የሊጡርጊያ ቲዮሎጊያ በሚል ርእስ ሥር የተጠቃለለው የቅዱስ አባታችን ገና የቅድስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከመመረጣቸው በፊት በመንበረ ጥበብ አስተማሪነት ከዛም የሥርወ እምነት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅይነት እስከ ነበሩበት ዓመት ያጠቃላለ የሊጡርጊያ ቲዮሎጊያ ቤተ ክርስትያንን ከማፍቀር የመነጨ መሆኑ እና ይህ መጽሓፍ በተከታታይ የሚቀርብ መሆኑ ገልጠው፣ የመጀመሪያው ክፍል ለንበብ መብቃቱ ብፁዕነታቸው ለሁሉም አቢያ ጥቅም ያለው ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በሊጡርጊያ ዘንድ ያለው ቲዮሎጊያ እርሱም የእግዚአብሔር ሥም ጎልቶ እንዲታይ እና እንዴት እንደሚገለጥ እና እንደሚብራራ ከሰጠው መሪ ሐሳብ በመነሳት ጸሎት እና ቅዱስ ምልክት ሆኖ እንዴት እንደቀረበ በጥልቀት የሚያብራራ መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ አንደኛው መጽሓፍ ለንባብ ሲቀርብ ባሰሙት ንግግር ሲገለጡ፣ ሮማ በሚገኘው ላ ሳፔንዛ መንበረ ጥበብ የዘመኑ ታሪክ መምህር የታሪክ ሊቅ ሉቸታ ስካራፊያ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ሊጡርጊያ ከእግዚአብሔር ሥም በመነሳት ለሁሉም እግዚአብሕር ግልጽ እንዲሆን ምንም’ኳ የሥርዓት ልዩነት እና የሃይማኖት ልዩነት ቢታይም የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር ያልው ግኑኝነት ቃል እና ምልክት ሆኖ ይኽ ጸሎት በመሆን የሚፈጸም ሥነ ሰብእ ግጽታውንም ጭምር የሚያብራራ ነው። ብሉይ ኪዳን እና አዲስ ኪዳን መካከል ያለው ግኑኝነት ማእከል ያደረገ መሆኑ ገልጠው፣ ኵላዊት ቤተ ክርስትያን ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር ያላት ግኑኝነት ጭምር የሚያብራራ ብቻ ሳይሆን ግኑኝነቱ ምን እንደሚመስል እና እንዴት መሆን እንደሚገባውም ጥልቅ ሀሳብ የሚሰጥ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.