2010-10-30 15:20:46

ሥነ ምርምር፣ በሰው እና በፈጣሪው መካከል ላለው ውይይት እና ግኑኝነት ሥፍራ ነው


ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ፣ እዚህ በቫቲካን ጳጳሳዊ የስነ ምርምር ተቋም ባዘጋጀው ዓመታዊ ጉባኤ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት ተጋባእያን ትላንትና ተቀብለው መሪ ቃል መለገሳቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ቅዱስነታቸው በሰጡት መሪ ቃል፣ በእምነት እና በስነ ምርምር መካከል RealAudioMP3 ያለው ግኑኝነት ሲያብራሩ፣ ቤተ ክርስትያን ስነ ምርምር በትክክል ለሰው ልጅ እርባና እንዲውል የሚያጎናጽፈው እድገት ታበረታታ ዘንድ አደራ ካሉ በኋላ፣ የዚህ ጳጳሳዊ የስነ ምርምር ተቋም ሊቀ መንበር በመሆን ያገለገሉት በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የስነ ባህርያዊ ሊቅ ኒኮላ ካቢቦን በማስታወስ፣ እኚህ ምሁር የሰጡት አስተዋጽኦ የሚደነቅ ነው ብለዋል።

ስነ ምርምር የሁሉም ፈውስ አድርጎ ወይንም በፍራት ስሜት መመልከት የሚሉትን ሁለት እነርሱም ስነ ምርምር ፍጹም በማድረ ወይንም ጸረ ስነ ምርምር መንገድ መከተል ከሚፈጥረው ከሚታዩት ሁለቱ ዓይነት የፅንፈኝነት መንገዶች መጠንቀቅ ይገባል። የስነ ምርምር ሚና በትዕግሥት እና በጋለ ስሜት ስለ ተፈጥሮ እና ስለ ሰው መሆን እውነትን መፈለግ እንደሆነም በማብራራት፣ ስነ ምርምር የተጎናጸፋቸው እድገቶች የጨበጣቸው የምርምር ውጤቶች ግልጽ ነው፣ ሆኖም የተጎናጸፈው እና በምርምሩ ሂደት ያሳየው ውድቀት ጭምር በማብራራት፣ ውጤት ሲያስገኝ ፍጹም አድርጎ መመልከት እና ውድቀት ሲያጋጥመው ጸረ ምርምር የሆነ አመለካከት ማረማመድ ኢምክንያታዊ ነው ብለዋል።

ቤተ ክርስትያን ለስነ ምርምር ሊቃውንት ያላት አክብሮት በመጥቀስ የሚያደርጉት ጥረት በማድነቅ፣ በሥራቸው እንዲበረቱ በመደገፍ የስነ ምርምር ሊቃውንት የመሠረተ ፍጥረት ስነ እውነት እና ሥነ አመክንዮ ገጽታው እና ሂደቱን ለመለየት በሚከተሉት የምርምር ሥልት ለፍልስፍና ያላቸው ፍላጎት የሚመሰክር መሆኑ ቅዱስነታቸው በማብራራት፣ ይህ ምርጫ ምክንያታዊ የሚያደርገውም ሥነ ምርምር የሚያስገኘው ውጤት ቤተ ክርስትያን ጭምር ተጠቃሚ መሆኗ ጠቅሰው፣ ሆኖም ምርምር የሰው ልጅ መንፈሳዊ እና ሰብአዊ ብሎም የፍጥረት ፍጻሜ በተመለከት ላለው ጥያቄ እና ትርጉም ለመሻት ለሚያደርገው አስተንትኖ ክፍት ሲሆን ነው ስለዚህ በምርምር እና በእምነት መጽናት ያለበት ግኑኝነት ተገቢ እና ወሳኝ ነው ብለዋል።

የሥነ ምርምር ሊቃውንት ዓለምን/ፍጥረትን አይፈጥሩም ሆኖም በተፈጥሮ ዘንድ ያለው ባህርያዊ ሕግ በመሻት እና በማጥናት የሆነውን ነገር ጠልቆ ለመረዳት እና ለመተንተን ጥረት ያደርጋሉ፣ ስለዚህ የስነ ምርምር ሊቃውንት እንደ ማንኛው ሰው ባህርያዊ ሕግ እና ምክንያቱንም ይሻሉ። ይኽ እንዲሆን የሚያደርገውም ከነገር ባሻገር ያለውን ፍጹም አካል እንዳለ መረዳት ሲጀምሩ፣ በስነ ምርምር እና በሃይማኖት መካከል ውይይት እንዲኖር ይገፋፋል በማለት በስነ ምርምር የሚጨበጡት ውጤቶች በሰው ዘንድ ያለው ተፈጥሮን የማድነቅ ስሜት ከፍ ከፍ ያደርጋል፣ የሚጨበጠው ውጤት በራሱ የሚዘጋ እና ሁሉን ወደ እራሱ የሚስብ ሳይሆን ከራሱ ውጭ ወደ ሆነው ተደናቂው ፍጹም ያሸጋግራል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.