2010-10-25 16:38:43

ወንጌልን መስበክ ዓለምን መገልበጥ ሳይሆን በኢየሱስ ኃይል መለወጡ ነው።


ይህንን ያሉ ትናንትና የመል ኣከ እግዚአብሔር ባሳረጉበት ወቅት ቅዱስ ኣባትችን ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ናቸው። ቅዱስነታቸው ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበት በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ትናንት እኩለ ቀን የመል ኣከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ዕልቱ የስብከተ ወንጌል ዕለት መሆኑ በማሳሰብ ‘የተጠመቁ ሁሉ የድኅነት መልካም ዜናን ለመስበክ የተጠሩ ናቸው’ ብለዋል። የዘንድሮ ዓለም ኣቀፍ የስብከተ ወንጌል ቀን መሪ ቃል፤ ‘የቤተ ክርስትያን ኅብረትን ማነጽ የስብከተ ወንጌል ቁልፍ ነው’ ይላል።

ቅዱስነታቸው ትናንት ጥዋት የመሀከለኛ ምሥራቅ ልዩ የጳጳሳት ሲኖዶስ መዝግያ ቅዳሴ ካሳረጉ በኋላ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ለማሳረግና ኣስተምህሮ ለመስጠት በመኖርያ ቤታቸው መስኮት ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ብቅ በማለት ሰላምታ ኣቅርበው፤ የር.ሊ.ጳ ጳውሎስ 6ኛን ንግግር በማስታወስ ቤተ ክርስትያን ወንጌል ለመስበክ የተላከች ናት፤ ማንነትዋም ይህ ተልእኮ ነው፤ ብለዋል። ይህንን ማንነት እንዲህ ሲሉ ኣብራርተውታል፡ ‘ቤተ ክርስትያን ወንጌል ለመስበክ ትኖራለች፤ ማለትም ለመስበክና ለማስተማር፤ የጸጋ ሥጦታ መስኖ ለመሆን፤ ኃጢኣተኞችን ከእግዚአብሔር ለማስታረቅ፤ የክርስቶስ ሞትና በክብር ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን የሚያስታውስ የክርስቶስ መሥዋዕትን በቅዳሴ ዘወትር እንዲኖር ማድረግ የተጠራች የተፈጠረች ናት፤ ቤተ ክርስትያን በማንኛውም ግዜና በማንኛውም ቦታ ትገኛለች፤ እያንዳንዱን ለመቀበልና በክርስቶስ ሙላት ያለው ሕይወት እንዲያገኝ ትሠራለች፤ እያንዳንዱ ክርስትያን ዘለዓለማዊ ሕይወትን ለብቻው ኣይደለም የሚጠብቀው፤ ወይም ዝም ብሎ ተቀምጦ በመቦዘን ኣይደለም፤ ከክርስቶስ ጋር በመተባበር ከሊሎች ጋር በኅብረት በመኖር ለመላው ዓለም ወንጌልን ያስፋፋል፤ የስብከተ ወንጌል ተል እኮ ዋና ተግባር ዓለምን መገልበጥ ሳይሆን በቃሉን በቅዱስ ቊርባን ማእድ እርሱ ከእኛ ጋር መኖሩን ለማጣጣም የሚጠራንና ጌታ ከሆነው ኣብረን ለመኖር ሁል ግዜ ከሚያስተምረን ከኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል በማግኘት ዓለምን ወደ እርሱ መለወጥ ነው፤ ዛሬ በዘመናችን ያሉ ክርስትያን ከክርስቶስ ጋር በኅበረት መኖር ምን ያህል ኣስደናቂና ልዩ መሆኑን ያሳዩናል፤ ሕይወታቸውን በዚህ ዓለም ከእኛ ጋር ቢያሳልፉም የሰማይ ነዋሪዎች ናቸው፤ የተመደበውን ሕግ ያከብራሉ በኣኗኗራቸው ግን ከዛ በላይ ናቸው፤ ለሞት ተፈርደዋል እሳቸው ግን ከዚህ ሞት ሕይወት ያገኛሉ፤ መልካም ሥራ እየሠሩም ተሰደዋል ግን ከዕለት ወደ ዕለት በቁጥር እየጨመሩና እያደጉ ናቸው። ካሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ተነሥተው በሁሉም የዓለም ክፍሎች እየሰበኩና እየተሰቃዩ ስላሉ ሰባክያነ ወንጌል እንድንጸልይ ኣደራ በማለት የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ኣሳርገዋል፤

ቅዱስነታቸው ከጸሎቱ በኋላ ትናንትና ብፅ ዕናቸው ለታወደ ብፅ ዕት እናቴ ኣልፎንሳ ክለሪቺን ኣስተዋሰው እንዲህ ብለዋል። ‘ትናንትና በቨርቸሊ የሞንዛ የጥቀ ቅዱስ ደም ደናግል ኣባል የነበረች፤ እናቴ ኣልፎንሳ ክለሪቺ ብፅ ዕት ተብላ በመታወጁ ደስ ብሎኛል፤ ላይናተ በሚባል የሚላን ቀበሌ ብ1860 ዓ.ም ተወልዳ በቨርቸሊ በ1930 ዓም ሞተች። ወደ ፍጹም ፍቅር የመራትን እግዚአብሔር እናመስግን፤’ በመጨረሻም በኣደባባዩ ተሰብስበው ለነበሩ በተለያዩ ቋንቋዎች ኣመስግነው ሓዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.