2010-10-22 13:44:18

የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ቀን በአፍሪቃ


24 ዓመቱ እያስቆጠረው ያለው የአፍሪቃ ኅብረት የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ ቀን እ.ኤ.አ. ጥቅምት 21 ቀን 2010 ዓ.ም. አፍሪቃን ሕዝብዋ እና መሪዎችዋ ስለ ሰብአዊ መብት ጉዳይ እንዲያስተነትኑ እና ውሳኔን በማስታወስ RealAudioMP3 እግብር ላይ እንዲያውሉት “ተቀባይነት ያለው ሰላም በአፍሪቃ ለማረጋገጥ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ ገቢራዊነት ወሳኝ ነው” በሚል ርእስ ሥር አክብሮት መዋሉ ሚስና የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።

ሰብአዊ ማኅበራዊ ኤክኖሚያዊ እድገት ለመጎናጸፍ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ ማረጋገጥ የማያሻማ ምርጫ መሆኑ ቀኑን ምክንያት በማድረግ የአፍሪቃ ኅብረት መግለጫ የጠቀሰ ሚስና የዜና አገልግሎት በማሳወቅ፣ ውሳኔው የአፍሪቃ ኅብረት መሠረተ ድንጋይ የሆኑትን እሴቶች የሚወክል መሆኑ የህብረቱ መግለጫ ያመለክታል። ይህ በኢትዮጵያ ርእሰ ከተማ ዋና መቀመጫው የሆነው የአፍሪቃ ኅብረት ማኅበር ዕለቱ ሰላም እና ደህንነት ላይ ያተኮረ ሆኖ ማክበሩ ለማወቅ ሲቻል። በሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ መረጋገጥ በአፍሪቃ የተጨበጡት ውጤቶች እና መረጋገጥ የሚገባቸው ብዙውን ጊዜ የሚዘነጉት የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ጉዳይ አሁንም በአፍሪቃ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑ ዕለቱን ምክንያት በማድረግ አለ ድንበር የተሰኘው የጋዜጠኞች ማኅበር ካሰራጨው መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.