2010-10-22 13:42:55

ብፁዕ ካርዲናል ቱርክሶን፦ ክርስትና ለእውነተኛው እድገት ወሳኝ ነው


ትላትና ጳጳሳዊ የረጂና አፖስቶሎሩም መንበረ ጥበብ የትምህርት ዓመት መክፈቻ ምክንያት የቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት መሠረት እርሱም የማኅበራዊ ትምህርት ዋቢ ያደረገ መለኮታው ንባብ ያሰሙት ጳጳሳዊ የፍትሕ እና የሰላም ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ኮድዎ አፒያ ቱርክሶን በማኅበራዊ መሠረተ ገጽታ የበለጸጉት አገሮች እና RealAudioMP3 ያለበለጸጉት የሚለው የልዩነተ አጥር በተለይ ደግሞ በዓለማዊነት የትሥሥር ሂደት ምክንያት የተደናገረ ትርጉም በመላበስ ሰሜን እና ደቡብ በሚል አጠራር ሃብታም እና ድኻ በሚል ቃል እንዲገለጥ ያስገደደው ተጨባጭ የባህል ልዩነት ችላ የሚል ማኅበራዊ ክስተት ለስደት ምክንያት መሆኑ በማብራራት፣ ቤተ ክርስትያን በወንጌል ብርሃን ተመርታ ይኸንን ማኅበራዊ ክስተት የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳይ ትምህርት ጋር በማያያዝ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 ፍቅር በሐቅ በሚል ርእስ ሥር በጻፉዋት አዋዲት መልእክት ሥር በማንበብ ሲያስረዱ ምዕራቡ ዓለም በተዛማጁ ባህል እጅግ እየተጠቃ የእምነት መቃወስ ተከናንቦት እንደሚገኝ እና የዚህ ኅብረተሰብ መጪው ዕድል ከጥንት ሲወርድ ሲዋረድ በመጣው ክርስትያን እሴቶች ላይ በመቆም ብቻ የሚቀረፍ ሳይሆን፣ ቤተ ክስትያን እነዚህ እሴቶች በፋይዳዊነት ሥነ ሃሳብ ብቻ እንዳይታጠር፣ ለተሟላ እድገት ወሳኝ መሆናቸው የማስተማሩ ኃላፊነት አላት። ለሰው ልጅ የተሟላ እድገት እግዚአብሔር አስፈላጊ መሆኑ ፍቅር በሐቅ የተሰኘቸው ዓዋዲት መልእክት ዋቢ በማድረግ ካብራሩ በኋላ፣ በእምነት እና በምርምር መካከል ያለው ግኑንኘት በቤተ ክርስትያን የማህበራዊ ጉዳይ ትምህር መሠረት በመመልከት፣ ለልማት የምንከተለው መንገድ በዚህ የቤተ ክርስትያን ማኅበራዊ ጉዳይ መንጻት ይኖርበታል ብለዋል።

በመጨረሻ ሰብኣዊ እውቅት ሉኣላዊ ብቃት የሌለው እና ለብቻውም ለሰው ልጅ የተሟላ እድገት አያጎናጽፍም፣ ስለዚህ በውስጡ ከራሱ ውጭ እንዲመለከት የሚገፋፋው ወደ ላይ ቀና እንዲል የሚያደርገው መንፍሳዊ ባህርይ አለው፣ ይኸንን ባህርይ ተቀብሎ ሰሚ ጀሮ እንዲሰጥበትም ፍቅር በሓቅ ያስፈልገዋል በማለት የሰጡትን መለኮታዊ ትምህርተ ንባብ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.