2010-10-22 13:45:56

ሕጻናት እና ወጣቶች የተጋረጠባቸው ድኽነት መዋጋት


የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት ጉዳይ የሚንከባከበው ድርጅት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ሕጻናት እና ወጣቶች ተጋርጦባቸው ላለው ሰብኣዊ ኤኮኖሚያዊ ድኽነት ለመቅረፍ ምን መደረግ አለበት የሚለውን ጥያቄ ማእከል RealAudioMP3 በማድረግ እና መልስ ለመለየት ያቀደ ጉባኤ ድርጅቱ እና የኢጣሊያ የሥራ እና የማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢጣሊያ የከተማ ነዋሪዎች ማኅበራት፣ የማኅበራዊ ጉዳይ የሚንከባከቡት ማኅበራት የተለያዩ የመጻእተኞች እና የተፈናቃዮች ተነከባካቢ ማኅበራት በጋራ ያዘጋጁት የሁለት ቀን ስብሰባ ትላትና እዚህ በሮማ መጀመሩ ለማወቅ ሲቻል፣ 2010 ዓ.ም. የኤውሮጳ የጸረ ድኽነት ዓመት ተብሎ የሚታሰብ ሲሆን፣ ጸረ ድኽነት የሆኑት የልማት የድጋፍ እቅዶች በመለየት ጸረ ድኽነት ዘመቻ የሚፋጠንበት ዓመት መሆኑ ግምት የሰጠ ስብሰባ ነበር።

በበለጸጉት አግሮች የሚታየው ድኽነት ስውር በመሆኑ በድኽነት የተጠቃው ግለ ሰብ ከህብረተሰብ የሚነጥል ነው። ይህ ከኅብረተሰብ መነጠልን የሚያስከትለው ድኽነት ሰብአዊ ግኑኝነትን የሚነካ የከፋ ድኽነትህን ገሃድ ለማውጣት እና እርዳታ ለመጠየቅ አሳፋሪ እንደሆነ ለብቻህ በተዘጋ ሕይወት የሚነጥል የተዛማጅ ባህል ተጽእኖ ያለበት አሰቃቂ ድኽነት ነው። በዚህ ዓይነት ድኽነት በስፋት የሚጠቃው የህብረተሰብ ክፍል ቀርቦ ለመደገፍ ምን መደረግ እንዳለበት በማለት ለሚሰጠው መልስ ማስተግበሪያ ሥልት ለመቀየስ የሚረዳ አስተያየት ያሰባሰበ ስብስባ እንደነበርም ተገልጠዋል፣።








All the contents on this site are copyrighted ©.