2010-10-20 17:59:09

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት መልእክት ለዘርአ ክህነት ተማሪዎች


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ባለፈው ሰኔ ወር የተጠናቀቀውን የክህነት ዓመት መዝጊያ የጻፉት መልእክት በትላንት ዕለት ይፋ ሆነ።

ቅዱስነታቸው ጥሪ ያላቸውን በዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት የሚገኙትን ተማሪዎችና ለመጪው ካህናት ባስተላለፉት የፍቅርና የማበረታቻ መልእክት በሰብኣዊ ብስለት የተሟላ የንፅሕና ሕይወትና እንዲኖራቸው አደራ ብለዋል፡፡

ርእሰ ሊቃነቀ ጳጳሳት ክህነት እንደ ጥንታዊና ግዜው ያለፈበት ታሪክ ሆኖ መታየት እንደሌለበት በማመልከት የሚመጣው ትውልድም ቢሆን ወደ አምላካችን እግዚአብሔር እንዲቀርቡ የሚመሩ ካህናት ምን ግዜም እንደሚያስፈልጉ ገልፀዋል።

የተከበራችሁ ኣዳሞቻችን መልእክቱን ተርጉሞን ከፋፍለን እናቀርብላችኋለን፡፡

“ውድ የዘርአ ክህነት ተማሪዎች፡

በታሕሣሥ ወር 1944 ዓ.ም. ለወታደራዊ አገልግሎት በተጠራሁበት ግዜ የወታደሩ ሹም እያንዳንዳችን ለወደፊት በምን ሞያ ላይ መሰማራት እንደምንፈልግ ጠየቀን፡ እኔ የካቶሊክ ካህን ለመሆን ነው የምፈልገው ብዬ መልስኩለት፡ እርሱም ሌላ ሥራ መፈለግ ኣለብህ፡ ለአዲሲቷ ጀርመን ካህናት አያስፈልጓትም ኣለኝ፡ ኅሊናው የሳተ-አበድ ኣመራር ባስከተለው ኣሰቃቂ ውድመት ያች የዘመኑ አዲሲትዋ ጀርመን ወደ ውድቀት እያዘነበለች መሆንዋና ያኔ ከምን ግዜም የበለጠ ካህናት እንደሚያስፈልጉ ተረዳሁ፡፡ ዛሬ ግን በኣገሪቱ ያለው ሁኔታ ሙሉ በሙሉ የተለየ ነው፡፡ ቢሆንም ቅሉ ዛሬም ብዙ ሰዎች አንደሚያስቡት፡ ካቶልካዊ ክህነት ግዜው ያለፈበት ለመጪው ሕይወት የማይበጅ ተስፋ የሌለው ሞያ ሆኖ ይታያል፡፡ እናንተ ግን ውድ ወንድሞቼ ይኸንን አስተሳሰብ እና አስተያየት በፍጹም በመቃወም በቤተ ክርስትያን ምሥጢረ ክህነት ጎዳና ለመጓዝ የተነሳችሁ ወደ ዘርአ ክህነት ለመግባት ወስናችኋል። እንዲህ ማድረጋችሁም መልካም ነው። ምንም’ኳ ዘመኑ እደ ጥበብ ተጽኦና ባሳደረበት እና ዓለማዊ ትሥሥር ባንሰራፋበት ዓለም ብንገኝም የሰው ልጅ ዘወትር፡ በኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠው እና ከእርሱ እንድንማር እና በርሱ በኵል እውነተኛ ሕይወት እና ፍሪያማ እና መቼም የማይዘነጋ የእውነተኛ ሰብአዊነት መመዘኛ የሆነውን ለመማር በኵላዊነት ቤተ ክርስትያን ጥላ ሥር የሚያሰባስበው እግዚአብሔር ያስፈልገዋልና፡፡ ሰው እግዚአብሔርን የማይገነዘብበት ሁኔታ ያለው ሕይወት ባዶ ይሆናል። ሁሉም የማይበቃ/ የማያረካ ይሆናል። ስለዚህ ሰው፡ በተለየ ወጣቱ ዘወትር የሚፈታተነው ስካር ወይንም አመጽ ላይ መጠጊያውን ይሻል፡። እግዚአብሔር ግን ኅያው ነው፡ እያንዳንዳችንን ይፈልገናል ሊያውቀንም ይሻል ስለዚህ ሁሉንም። እርሱ ይኽን ያክል ታላቅ ሆኖ እያለ ተናንሽ ለሆኑት ለኛ ጉዳይ ግዜ ኣለው “የራሳችሁ ጠጉሮችም ሳይቀሩ የተቆጠሩ ናቸው’’ ይለናልና፡፡ እግዚኣብሔር ሕያው ነው። ለእርሱ የሚኖሩና እርሱን ወደ ሊሎች የሚያደርሱ ሰዎች ያስፈልጉታል፡ ስለዚህ ካህን መሆን ትርጉም ኣለው። ዓለም እረኞች የሚሆኑ ካህናት ዛሬ ነገ እስከ ፍፃሜዋ ዘወትር ካህናት ያስፈልግዋታል፡፡

ዘርአ ክህነት ለክህነታዊ ኣገልግሎት የሚያራምድ ማኅበር ነው፡ በዚህ ኣባባል ኣስፈላጊ ነገር ብያለሁ። ይህም ወደ መዓርገ ክህነት የሚደረሰው ለብቻ ኣይደለም። የሓዋርያት ማኅበር ያስፈልጋል። ይህም ኩላዊት ቤተ ክርስትይንን በኅብረት ለማገለገል የሚፈልጉ ሰዎች ማኅበር ነው፡፡ በዚህ መልእክት በዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት ላይ ስገኝ ያሳለፍኩትን ሕይወት መለስ ብዬ በመመልከት ካህናት እንድትሆኑ በምታደርጉት የጉዞ ዓመታት የሚጠቅሙ አንዳንድ ኣስፈላጊ ነገሮችን ከናንተ ጋር ለመካፈል እወዳለሁ።

ኛ  ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ጢሞተዎኣስ እንደጻፈው (1ጢሞ 6፡11) ካህን ለመሆን የሚፈልግ ከሁሉ ኣስቀድሞ ‘የእግዚአብሔር ሰው’ መሆን ኣለበት። ለእኛ እግዚአብሔር ሩቅ ያለ ሓሳባዊ ነገር ኣይደለም፤ ከቢግ ባንግ በኋላ የሚገለጥ የማይታወቅ ኃይልም ኣይደለም። በኢየሱስ ክርስቶስ ገጽታ የእግዚአብሔር ፊት እናያለን። በኢየሱስ ቃላታም እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሲናገር እናዳምጠዋለን። ስለዚህ ለክህነት በምንዘጋጅበት ግዜም ይሁን በመላው የክህነት ዘመናችን ዋናው ኣስፈላጊ ነገር በኢየሱስ ክርስቶስ ኣማካኝነት ከእግዚአብሔር የምናደርገው የግል ግኑኝነት ነው። ካህን ኣባላቱን ለመጠበቅና ቁጥራቸውን ለመጨመር የሚታገል የማንኛውም ድርጅት ኣስተዳዳሪ ኣያደለም። ካህን በሕዝብ መካከል የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነው። ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር ለማድረስ ይታገላል፤ በዚህም በሰዎቹ መካከል ያለው እውነተኛ ኅብረትን ለማሳደግ ይጥራል። ስለዚህ፤ ውድ ወንድሞቼ ከእግዚአብሔር ጋር በማያቋርጥ ግኑኝነት እንድትኖሩ መማር እጅግ ኣስፈላጊ ነው።

እርግጥ ነው ጌታ ሁል ግዜ ጸልዩ ሲል የጸሎት ቃላት መላልሰን እንድንደግም ኣይደለም የሚጠይቀን፤ ሆኖም ግን እያንዳንዱ ቀን በጸሎት መጀመር በጸሎትም መፈጸም ኣለበት። ቅዱስ መጽሓፍ በማንበብ ጌታን ማዳማጥ ኣለብን፤ ፍላጎታችንና ተስፋችንና እንዲሁም ደስታችን ሥቃያችን ስሕተቶቻችን ልንገልጥለጥ ያስፈልጋል፤ ለተደረገልን መልካም ነገርም ምስጋናችን ማቅረብ ኣለብን፤ በዚህም እግዚአብሔርን የሕይወታችን ማእከል በማድረግ ዘወትር እፍታችን ይሆናል። እንዲህ ያደረግን እንደሆነ ስህተቶቻችንን ልናውቅና እንድንሻሻል ለመሥራት እንችላለን፤ በየዕለቱ ለምናገኛቸው በጎ ነገሮችንም ልናስተውል እንችላለን፤ ለዚህም ምስጋናችን ያድጋል፤ በምስጋና ደግሞ እግዚአብሔር ቅርባችን መሆኑንና ልናገለግለው እንደምንችል እንረዳለን።








All the contents on this site are copyrighted ©.