2010-10-20 18:00:47

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ ኣስተምህሮ (20.10.10)


ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ለተለመደው ሳምንታዊ የዕለተ ሮቡዕ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ ኣስተምህሮ መክፈቻ ጸሎት ካሳረጉ አንደኛይቱ የጳውሎስ መል እክት ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች 13፡1 “በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤  ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል።” የሚለው በተለያዩ ቋንቋዎች ከተነበበ በኋላ በጣልያንኛ ቋንቋ ሰፋ ያለ ትምህርት ኣቅርበው የሚከተለውን ኣጭር ኣስተምህሮ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ኣቅርበዋል። ‘ውድ ወንሞቼና እኅቶቼ፤ ዛሬ በምናቀርበው ትምህርተ ክርስቶስ በመሀከለኛው ክፍለ ዘመን ስለኖረች ቅድስት ኤልሳቤጥ ዘሃንጋሪ እንደ ቅድስት ኤልሳቤጥ ዘቱሪንጅያም የምትጠራ መናገር እወዳለሁ፤ በ13ኛ ክፍለ ዘመን ተወለደች፤ ኣባትዋ የሃንጋሪ ንጉሥ ነበሩ፤ ኤልሳቤጥ ከሕጻንነትዋ ጀምራ ለጸሎት የታመነች ለድሆችም ልዩ ትኲረት በመስጠት የታወቀች ነበር፤ በፖሎቲካ ምክንያት ሉድዊግ ለሚባል መስፍን ብትዳርም እርሷና ባልዋ በእምነትና የጌታን ፍቃድ ለመፈጸም ባላቸው ፍላጎት የተመሠረተ የእርስ በእርስ ፍቅር ኣዳበሩ፤

ኤልሳቤጥ ትሠራበት የነበረችበት ፍርድ ቤት ብዙ ነገሮች ቢጠይቃትም በትዳር ሕይወትዋ እምነትዋን ኣላስተጓጓለችም፤ በማድ ቤት በመስተንግዶ ከትላልቅ ሰዎች ጋር ከመመግብ የታረዙትን መመገብ መረጠች እንዲሁም የሚያሸበ.ርቅ ልብስ ከመልበስ የተራቈቱትን ማልበስ መረጠች፤ እርሷና ባለቤትዋ ሉድቪግ በእግዚአብሔር በነበራቸው ጥልቅ እምነት በእምነት ጉዳዮቻቸው ይረዳዱ ነበር።

ባለቤትዋ በሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ ኤልሳቤጥ ጠቅላላ ግዜዋን ድሆች ለማገልገል ሰዋችው፤ ብዙውን ግዜ ደግሞ የተናቀውንና ብርቱውን ሥራ ትሠራ ነበር።

ኤልሳቤጥ ኣንድ ማኅበር ወይም ገዳም መሠረተች እስከ ዕለተ ሞትዋም መሓላዋን ጠበቀች፤ ከሞትች በኋላ በአራት ዓመት ቅድስት ተባለች የሶስተኛ የቅዱስ ፍራንቸስኮ ማኅበር ጠበቃም ሆነች፤ ለድሆች ኣገልግሎት ያዋለችው ፍቅር እኛም ክርስቶስን በድሆች እንድናፈቅረው ይርዳን፤ ሲሉ ትምህርታቸውን ከደመደሙ በኋላ ባለፈው እሁድ ቅድስናቸውን ላወጁት ቅዱስ ኣንድረ በሰትና ቅድስት መርይ ማክሎፕ የነበርዋንቸውና ባቋቋማቸው ማኅበራት የቅዱስ መስቀል ማኅበር እና የቅዱስ ዮሴፍና ቅዱስ ልብ ደናግል ማኅበር ኣባላትና ተማሪዎች ኣመስግነዋል።

በመጨርሻም ቅዱስነታቸው በዘንድሮ ወደ ካርዲናል ደረጃ ከፍ በማለት ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ እንደሚለው እሳቸውን የሚረዱ ኣዳዲስ ካርዲናላት ለመሰየም እፊታችን ኅዳር 20 ቀን የካርዲናሎች ጉባኤ እንደሚያካሄዱ ኣመልክተው የተሠያሚዎቹ ዝርዝር የስም ዝርዝር ይፋ ኣድርገዋል፤ የተሠያሚዎቹ ብዛት 24 ሲሆን ከመላው ዓለም የምትገኝ እንተላዕለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን የተመረጡ ናቸው።

የስም ዝርዝር ካነበቡ በኋላ ም እመናን ኣዲሶቹን ካርዲናሎች በጸሎት እንዲያስብዋቸው ኣደራ በማለት የዛሬን ትምህርት በሓዋርያዊ ቡራኬ ፈጽመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.