2010-10-19 13:36:59

የኢጣሊያ የካቶሊክ ምእመናን ማኅበራዊ ሳምንት


እ.ኤ.አ. ከባለፈው ጥቅምት 14 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለሶስት ቀናት የተካሄደው የኢጣሊያ የካቶሊክ ምእመናን ማኅበራዊ ሳምንት ትላንትና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 ለጉባኤው ያስተላለፉት መልእክት ተነቦ መጠናቀቁ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ይህ “ለመጪው አገር ተስፈኛ ዝክረ ነገር” በሚል ርእስ ሥር ተመርቶ የተካሄደው RealAudioMP3 የካቶሊክ ማኅበራዊ ሳምንት፣ በኢጣሊያ ማኅበራዊ ፖለቲካዊ እና ኤክኖሚያዊ ተጨባጭ ጉዳይ የዳሰሰ እና ዕለታዊ እንቅስቃሴ እና ውሳኔ፣ መጪው የአገር ተስፋ የሚነበብበት የሚገለጥበት የአገር ጥቅም የሚያስቀድም ይሆን ዘንድ ያሳሰበ እንደነበር ሲገለጥ፣ ትላትና ለማኅበራዊ ሳምንት መዝጊያ የቀረበው መሥዕተ ቅዳሴ የመሩት ስብሰባው ላስተናገደው በኢጣሊያ ረጆ ካላብሪያ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሞንደሎ መሆናቸው ሲገለጥ፣ ብፁዕነታቸው ባሰሙት ስብከት፣ ኢፍትሃዊነትን ሕገ ውጥነትን በመቅጫ ሕግ ብቻ የሚፈታ ሳይሆን ሕጋዊነት እና መልካም አብነት ሰላም እና የአገር ጥቅም ሕይወትን የሚያቀድም ባህል በማራመድ ጭምር ነው፣ እንዳሉ ለማወቅ ተችለዋል።

ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኤኮኖሚ ቀውስ ኤክኖሚያዊ ጉዳይ መሠረት ያለው ብቻ ሳይሆን ባህላዊ እና ስነ ማኅበራዊ ቀውስ የሴቶች መብት እና ፈቃድ በትክክል እና በተገቢ ካለ ማሳካት፣ በማኅበረ-ሰብ መሠረት የሆነውን ቤተ ሰብ ለመደገፍ የሚደረገው ጥረት መንግሥታት እና ተቋሞች ያሳዩት ዝለት፣ አልቦ ፍቃደኝነት የአገር እና የሕዝብ ጥቅም ማስቀደም የሚለው አወንታዊ ተግባር የሚሽር ራስ ወዳድነትን የሚያረማምደው ባህል መስፋፋት መሆኑ በማብራራት፣ ይኽ አርቆ ለማይመለከተው ዛሬ ብቻ ለሚል ጠባብ አስተሳሰብ እና ባህል፣ ከሚያጋልጠው ምርጫ ለመላቀቅ የዜጎች ሁኔታን የመተንተን ብቃቱ እንዲያሰለጥኑ በመደገፍ በማኅበራዊ ጉዳይ ተሳታፊነታቸውን በማክበር ንቁ የኅብረትሰብ አባል የሕይወት ባህል የሚያከብር እንዲሆን ማገዝ ወሳኝ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

ቅዱስ አባታችን በዚህ በምንኖርበት ዘመን በፖለቲካው እና በባህል ጉዳይ በትህትና የሚሳተፍ የታደሰ ካቶሊካዊ ትውልድ ይፈልቅ ዘንድ ጥሪ በማቅረብ፣ በፖለቲካው እና በባህል ጉዳይ የካቶሊክ ምእመን የተሳትፎ ተግባር እግዚአብሄር ሰው እና ዓለም ከሚመለከቱ ሓቆች በመንደርደር አእምሮ ግብረ ገብ መሠረት ከሚያደርግ የሕንጸት ሂደት ፈጽሞ መለየት የለበትም ብለዋል።

በመጨረሻም የስደተኞች እና ተፈናቃዮች ጉዳይ በመጥቀስ ስደተኛ በተስተናገደበት አገር ተዋህዶ ለመኖር የሚያግዘው መድረክ እንዲፈጠርለት በማሳሰብ ቤተ ክርስትያን የእዚአብሔር የማዳን እቅድ መርህ ያደረገ በትክልል የድሰተኛ እና የተፈናቃዮች ጉዳይ የሚመለከት ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በመወጠን የምትሰጠው አገልግሎት የሰው ልጅ ለስደት የሚዳርጉት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመቀረፍ የሚያግዝ፣ ከሰው ልጅ ምድራዊ ተግባር ባሻገር የሚመለከት መሆኑ ገልጠው፣ ታሪክ በእዚአብሔር ቸርነት የሚመራ መሆኑ ጸንቶ ማመን እና ይኽ እምነት የሚስጨብጠው ተስፋ በእየሱስ ክርስቶስ ኅላዌ የተገለጠ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.