2010-10-19 13:32:45

ቅድስት መንበር እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት


ባለፈው ሓሙስ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ፍራንሲስ ቹሊካት በተካሄደው የድርጅቱ 65ኛ ጠቅላይ ጉባኤ ምክንያት በተካሄደው ቅድመ ውይይት ተገኝተው፣ የሕፃናት ወታደሮች እና የወባ በሽታ ለማጥፋት የሚደረገው ጥረት ግቡን እንዲመታ ያሳሰበ ንግግር ማሰማታቸው ሲገለጥ፣ ሕፃናትን ለውትድርናው ዓለም በማጋለጥ የሚደርስባቸው RealAudioMP3 የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ ዘንድ ያለው የሕፃናት ጉዳይ የሚመለከተው መብት እና ፈቃድ ረገጣ በማብራራት፣ ሕፃናት ለውትድርና ዓለም ከተዳረጉ በኋላም ለዘርፈ ብዙ ችግሮችም እንደሚጋለጡ ጠቅሰው፣ በአፍሪቃ በየዓመቱ 1 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ በወባ በሽታ ምክንያት እንዲሁም 250 ሺሕ የሚገመትም በሕፃናት ወታደሮች እጅ ለሞት የሚዳረጉ መሆናቸው ብፁዕ ቹሊካት ገልጠዋል። እነዚህ ሁለት አበይት በተለይ ደግሞ አፍሪቃን በእጅጉ እያሰቃየ ያለው አደጋ ቅድስት መንበር በሁሉም መድረክ አሳሳቢ መሆኑ ከመግለጥ ባሻገራ ችግሩ እንዲቀረፍ በሚደረገው ጥረት ቀዳሚው ሥፍራ ይዛ እንደምገኝም ገልጠዋል።
እ.ኤ.አ. በ 2000 ዓ.ም. የሕፃናት እና የወጣቶች መብት እና ፈቃድ ጥበቃ በሚል መርህ መሠረት ረቆ የጸደቀው ውሳኔ ሕፃናት ከውትድርናው ዓለም ማላቀቅ ብቻ ሳይሆን ቅድስት መንበር ካለ መታከት በምታቀርበው ጥሪ እና በምታደርገው ግፊት በሕግ የተከለከለ ጸረ ሰብአዊ ተግባር መሆኑም ታብራራለች፣ ይህ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸደቀው ውሳኔ በአገር አቀፍ ደረጃ ገና ያላጸደቁት አገሮች ባስቸኳይ እንዲያጸድቁት አደራ ማለታቸውም የቅድስት መንበር መግለጫ በመጠቆም፣ የሕፃናት ሕይወት የአንዲት አገር የነገው ብሩህ ተስፋ እና ቤተሰብ ላደጋ የሚያጋልጥ ጸረ ሰብአዊ ተግባር የሆነው ሕፃናትን ለውትድርናው ዓለም የመዳረጉ ድርጊት ጨርሶ ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ ጥሪ በማቅረብ አክለውም ቅዱስ ኤጂዲዮ የካቶሊክ እንቅስቃሴ እና የተለያዩ የካቶሊክ የተራድኦ ማኅበራትን የሚያቅፈው በካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ስም የሚጠራው የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ርክስትያን የተራድኦ ማኅበር የሕፃናት መብት እና ፈቃድ ጥበቃ እያካሄዱት ያለው ጥረት እጅግ የሚመሠገን ነው ያሉትን ሐሳብ የሕጻናት ወታደሮች ጉዳይ የሚከታተል እና ከዚህ ኢሰብአዊ ተግበር ሕፃናትን ለማላቀቅ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለሚመራው ጽ/ቤት ተጠሪ ራድሂካ ኩማራስዋምይ እንዳስተጋቡት የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.