2010-10-19 13:31:22

ቅ..አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የእግዚአብሔር ጥሪ


እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 10 ቀን 2010 ዓ.ም. እዚህ በቫቲካን በመካሄድ ላይ ያለው የመካከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ አበው በክብር እንግድነት የተገኙበት ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ክብር በጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ የሙዚቃ ደራሲ እና አቀነባባሪ ኤኖክ ዙ ጉተንበርግ ከኔውበውኤርን ዘማሪያን ጋር በመሆን በክላን ወርዋልቱንግ የሙዚቀኞች ቡድን የታጀበ RealAudioMP3 የጁሴፐ ቨርዲ ረኵዩም - ጸሎተ ፍትሃት የሙዚቃ ድርሰት መሠረት የተወሃሃደ የሙዚቃ ትርኢት መቅረቡ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ቅዱስ አባታችን የሙዚቃው ትርኢት ፍጻሜ ባሰሙት ንግግር፣ ይህ የጁዜፐ ቨርዲ የጸሎተ ፍትሃት ሙዚቃ፣ የሰው ልጅ መንፈስ ከፍ ከፍ የሚያደርግ ጥልቅ ውበት ያለው መሆኑ በማብራራት፣ የረኵዩም ጸሎተ ፍትሃት ሙዚቃ ደራሲ ቨርዲ እ.ኤ.አ. በ 1873 ዓ.ም. አለሳንድሮ ማንዞኒ ዕረፍት ምክንያት የደረሰው ሙዚቃ መሆኑ ቅዱስነታቸው በማስታወስ፣ ቢሆንም ግን ለማንዞኒ ክብር የቀረበ ብቻ ሳይሆን ማንዞኒ በነበረው የክርስትናው እምነት እና ሰብአዊ ጽናት በቨርዲ ሕይወት እንዲቀሰቀስ ያደረገው ጥልቅ መንፈሳዊነት ጭምር የሚያንጸባርቅ ነው ብለዋል።

ቨርዲ የሰው ልጅ ሟች መሆኑ ይኸ የማይሻረው እውነት በሁሉም የሚደርስ፣ መሆኑ እና እንዲሁም ከነገርነት ባሻገር ስላለው የላቀው እውነት እና ፍጹም የሚዳስስም ነው። ቨርዲ በደረሰው የጸሎተ ፍትሃት ሙዚቃ በላቲን ሥርዓት ያለው የጸሎተ ፍትሃት ሊጡርጊያ ቃላቶችን በመጠቀም የሰውን ልጅ በዚህ እውነት የሆነው በማንም የማይሻረው የሕይወት አንዱ ተጨባጭ ምዕራፍ ፊት በማስቀመጥ፣ እያንዳንዱ በሞት ፊት፣ ሰው ካለው ኢፍጹምነት ባህርይ መሠረት የሚኖረው የሚያንጸባርቀው የሐዘን ስሜት እና ያለው የዘለዓለማዊ ሕይወት ጥማትን የሚያወሳ ነው።

ቨርዲ የጸሎተ ፍትሃት የተሰኘውን ሙዚቃ ከደረሰ በኋላ ለሙዚቃ ድርሰቶች ዋና አዘጋጅ መልእክት ሲጽፍ፦ በመጠኑ የኢ-እግዚአብሔርነት ባህል ተከታይ መሆኑ ሲገለጥ፣ ሆኖም ይህ እርሱ የሚኖረው የኢ-እግዚአብሔርነት እምነት ዘለዓለማዊነትን የሚሻ፣ ሞት በሚያስከትለው ፍርሃት እና በሚያሳድረው ተስፋ መቁረጥ በሰው መሆን ዘንድ ያለው ዘለዓለማዊው ሕይወት የመሻት ባህርይ እና የተስፋ ጭላንጭል እና እግዚአብሄር ሆይ ከዘለዓለማዊው ሞት ነጻ እውጣኝ የሚል ጸጥታ እና ጥልቅ ጸሎት የሚያቀርብ ነው ካሉ በኋላ፣ ይኽ ሰው የሚሻው ዘለዓለዓለማዊ ሕይወት እና ሰላም፣ ከእግዚአብሔር ብቻ እንደሚያገኘው የሚያረጋግጥ ምስክርነት ነው እንዳሉ ከቅድስት መንበር የተላለፈ መግለጫ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.