2010-10-18 15:56:40

ካለመታከት መጸለይ እንዳለብን


እግዚአብሔር በሰጣት ጸጋ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትናንትና በመንበረ ሮሜ ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ብቃታቸውን በተኣምር ያስመሰከሩ ስድስት ብፁዓን ቅድስና በታላቅ ክብር ኣወጀች።

ቅዱስነታቸው ዕለቱን የቅድስና በዓል በማለት ገልጠው እግዚአብሔርን ለዚህ ሥጦታ ማመስገን እንዳለብን የቅዱሳኑ ምሳሌ በመከተል ዘወትር መጸለይ እንዳለብን ካለመታከት ዘወትር መጸለይ እንዳለብን ኣሳስበዋል።

ከቅዱሳኑ ኣገሮች የተሰበሰቡ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ም እምናን ነጋዳያን በተሰበሰቡበት ትናንትና ቅዱስነታቸው በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ የቅድስና ሥር ዓት መፈጸመያ ቅዳሴ ኣሳርገዋል።

ቅዱስነታቸው በቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፤ ዛሬ የቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ በቅድስና ጸጋ ታድሰዋል፤ ለዚህ ኣጋጣሚ ከተለያዩ ቦታዎች እስከ እዚህ ድረስ ለመጣችሁ ካርዲናሎች ጳጳሳት በቅዱሳኑ የተቆረቆሩ ተቅዋሞች ኣለቆች በመንግሥቶቻችሁ ተወክላችሁ እዚህ የምትገኙ ባለሥልጣኖች ሳመሰግናችሁ በልቤ ደስ እያለኝ ነው ሲሉ ለሁሉም ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ የዕለቱ ቃለ ወንጌል በመጥቀስ፤ ኣንዳንዴ ለመጸለይ የምንደክምበት ግዜ ሊኖር ይችላል፤ ጸሎት ለሕይወታችን የማይጠቅም ሆኖ የሚሰማን ግዜም ኣይጠፋም፤ ስለዚህ ከመጸለይ ሌላ ሥራ ለመሥራት ለመንቀሳቀስ ፈተና ካለጸሎት በኃይላችንና በእውቀታችን ወደ ፈለግንበት ዓላማ ለመድረስ እንሞክራለን፤ ሆኖም ግን ጌታ በወንጌል ሉቃስ 18 እንዳለው ‘ዐመፀኛው ዳኛ በመጨረሻ ላይ የድኻዋ መበለት ልመና ሲሰማ እግዚአብሔር ታድያ ቀንና ሌሊት እየጮኹ ለሚለምኑት ሳይዘገይ በፍጥነት ይፈርድላቸዋል እላችኋለሁ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር መልካም ነውና’ ሲሉ ሳንታካት እንድንጸልይ ኣደራ ብለዋል።

የሚያስፈልገው ጸሎት ብቻውን እንዳልሆነ ለመግለጥ ቅዱስነታቸው እንዲሁ ብለዋል፤ የጸሎት ኣዝማምያችን መሠረት ያስፈልገዋል ይህም መሠረት እምነት ነው፡ ካለ እምነት በሚገባ ለመጸለይ ኣይቻልም፤ እነኚህ ስድስት ቅዱሳን ይህንን ያስተምሩናል፡ ቅዱሳኑም ቅ.ስታኒስላው ሶልትይ ቅ.ኣንድረ በሰት፣ ቅ.ካንዲዳ ማርያ ደ ኸሱሢፒትሪያ ኢ ባርዮላ፡ ቅ.ማክሎፕ ማርያም ዘመስቀል፤ ቅ.ጁልያ ሳልዛኖ እና ቅ.ባቲስታ ካሚላ ቫራኖ ናቸው። ሲሉ የእያንዳንዳቸው ኣጭር የህይወት ታሪክ በተለያዩ ቋንቋዎች ኣንብበዋል።

ቅዱስ ስታኒስላው በመስከረም 27 ቀን 1433 ዓ.ም በፖላንድ ተወልደው እንዳደጉ፤ ገዳማዊ እንደነበሩ ለቅዱስ ቊርባን ልዩ እንደነበራቸው እንዲሁም ቅዱስ ቁርባን የእግዚአብሔርና የጓደኛ ፍቅርን እተግባር ላይ ለመዋል ምንጭና ምልክት መሆኑን እንዳስተማረ ኣመልክተዋል።

በካንዳ በ1845 የተወለደው የቅዱስ መስቀል ግዳም ኣባል ቅዱስ ኣንድረ በሰት ደግሞ ሥቃይንና ድህነትን በት ዕግሥት ያሳለፈ እምነትን የእግዚአብሔር ፍቃድ ለመፈጸም በነጻነት ሁሉንም በእርሱ እጅ መተው መሆኑን ኣስተምረዋል።

እመምኔት ካንዲዳ ማርያ ደ ኸሱስ ሲፒትርያ ኢ ባርዮላም በ1845 በእስፓኛ የተወለዱ ቅድስት ሆነው መንፈሳውያን ኣባቶችዋ የነበሩ ኢየሱሳውያን ለኢየሱስ ብቻ መኖር እንዳለባት ባስተማርዋት መሠረት እስከ ዕለተ ሞትዋ እኔ የእግዚኣብሔር ብቻ ነኝ ስትል በመኖር የዘለዓለም ሕይወት ኣገኘች።

በችግርና በረሃብ ከተሰደዱ የእስኮትላንድ ዜጋዎች ጥር 15 ቀን በ1942 ዓም በመልበርን ኣውስትራልያ የተወለዱ ቅድስት መርይ ማክሎፕ በጽናትዋ በቅዱስ ቅናትዋ በት ዕግሥትዋና በጸሎትዋ ኣብነት የሆኑ ድሆችን ለማስተማር የከፈለችው መሥዋዕትና በት ዕግሥት ያሸነፈችው በሕመም የደረሳት ፈተናና ከሌሎች የተጫናት መስቀል ወደ ቅድስና ኣደረሳት።

በደቡብ ኢጣልያ የኣንደኛ ደረጃ ትምህርት ኣስተማሪ የነበረች ቅድስት ጁልያ ሳልዛኖ ጥቅምት 13 ቀን 1846 ዓም ከባለጠጋዎች ብትወለድም በ4 ዓመት ዕድሜዋ ኣባትዋ ስለሞቱ በገዳም ነው ያደገችው፤ መምህር ሆና ስትሠራ እግዚኣብሔርን ለሁሉም ለማሳወቅ ኣበርትታ ሠርታለች፤ የቅዱስ ልብ የትምህርተ ክርስቶስ ኣስተማሪዎች ደናግል ማኅበርም መሠረተች።

በመጨረጻም ከ1458 እስከ 1524 ዓም የኖረች የክላሪሰ ደናግል ኣባል ቅ.ባቲስታ ካሚላ ቫራኖ እስከ ዕለተ ሞትዋ የሕይወት ወንጌላዊ ትርጉም በተለይ በጸሎት የመሰከረች ቅድስት ናት፤ የክርስቶስ ኣካል የሆነችው ቤተ ክርስትያን ወለቅ ዘለቅ ስትል እርሷ ግን የተጋድሎ የንስሓና የጸሎት መንገድ በመከተል ስለቤተ ክርስትያን መታደስ ብዙ የጸለየችና የታገለች ቅድስት ናት፤ ሲሉ ከእያንዳንዱ ቅዱስ ለእኛ ይሆናል ያሉትን ትምህርት ቀንጨብ ቀንጨብ እያደረጉ ኣስተምረዋል።

በመጨረሻም በተለያዩ ቋንቋዎች በማመስገን የእነዚህ ቅዱሳን ኣብነት በመከተል እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን የሚያቀርብልንን የዘለኣለም ሕይወት ጥሪ እንቀበል ሲሉ ስብከታቸውን ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.