2010-10-15 15:02:26

የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ መሠረት ባህርያዊ የግብረ ገብ ሕግ


በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ፍራንሲስ ቹሊካት ከትላንትና በስትያ ድርጅቱ ባካሄደው 65ኛው ጠቅላይ ጉባኤ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፣ የሕግ ሉአላዊነት የሕዝቦች እና የአገሮች ልማት ሰላም እና ደኅንነት መሠረት መሆኑ በማብራራት፣ የሰው ልጅ ብልህነት እና የማስተዋል ችሎታ እና የተፈጥሮ እና የታሪክ ብሩህነት ተነባቢነት አለ ምንም ቅድመ ሁኔት የሰው ልጅ ክብር መጠበቅ እና ማክበር የተሰኙት መሠረታውያን ሃሳቦች ለሰው ልጅ የጋራ ጥቅም የሚበጅ፣ የሚያገለግል፣ የሚንከባከብ፣ RealAudioMP3 ቅን ሕግ ተደንግጎ እንዲጸና የሚመመሩ ናቸው። ስለዚህ የኅብረተሰብ ማስተዳደሪያ ደንብ ይሁን የሚባል የተራ ደንብ ውጤት አይደለም፣ እንዲህ በመሆኑም ባህርያዊ የግብረ ገብ ሕግ መሠረት በማድረግ የሚለው ሃሳብ እና ተግባር ያካተተ መሆን አለበት ብለዋል። ከዚህ አኳያ በዓለም አቀፍም ይሁን በአገር አቀፍ ደረጃም የሕግ አካላት የሕግ ማስፈጸሚያ እና የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ይኸንን ኵላዊው እውነት ግምት የሚሰጡ መሆን ይጠበቅባቸዋል ግዴታም ነው ብለዋል።

የሕግ አካላት፤ የሕግ ማስፈጸሚያ እና የሕግ መወሰኛ መዋቅሮች ለሥራቸው እና ለአገልግሎታቸው መሠረት የሆነውን በመዘንጋት በቀላሉ በሰብአዊ ተመክሮአዊ ጉዳይ ላይ ብቻ ግንዛቤ በማኖር እና በዚህ ላይ ብቻ በመጠመድ ይኸንንም መሠረት በማድረግ የችሎት ሂደት እና ሕጎችን ተፈጻሚነት እና እግባብነት ላይ ያተኵራሉ። ስለዚህ ይህ በሚታዩት ክስተቶች እና አወንታዊ ተጨባጭ ላይ የሚመረኮዘው የፍልስፍና አድማስ የሚከተል እና ፋይዳአዊነት ላይ ያተኮረ ለግል ጥቅም እና ፍላጎት የሚንከባከብ ከማኅበራዊ ኃላፊነት ጉዳይ ጋር የሚጋጭ ሕግ እንዲደነገግም ቦታ እና ዕድል ይፈጥራል። ስለዚህ ይኽ ደግሞ የሕግ ሉኣላዊነት ሳይሆን ፍትህ እና ቅንነት ሕጋዊነት በሕግ እና ለሕግ እንዲሆን ያስገድዳል።

በዓለም አቀፍ ደረጃም ይሁን በአገሮ አቀፍ ደረጃም የሚደነገጉት የሠራተኛ፤ የስደተኛ እና የተፈናቃዮች መብት ፈቃድ ግዴታ፣ ሕግ አድርጎ ለማቅረብ የሚደረገው ጥረት፣ ዓለም አቀፍ ትሥሥር የሚመለከቱ ሕጎችን የዓለም አቀፍ ባንክ ቤት ሕግ፣ ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ መረጋጋት የሚከታተል ማኅበር፣ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ሃብት ድርጅት ሕጎች የሁሉም አገሮች የተሳትፎ እኵልነት የሚያረጋግጥ እንዲሆን ቅድስት መንበር በዚህ ዓለም አቀፍ መድረክ የምትሰጠው አስተዋጽኦ በማስታወስም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እያሳየው ያለው ግስጋሴ አርኪ ነው ብለዋል።

በመጨረሻም በብሔራዊ አቅፍ ደረጃ እያንሰራፋ ያለው ሙስና ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ አለ መረጋጋት እና የተፈጥሮ ሃብት እጥረት ብዙ አገሮች በኤክኖሚው ረግድ ብቻ ሳይሆን የሕግ ሉኣላዊነት ለማረጋገጥ ለሚያደረገው ጥረት ጭምር እንቅፋት መሆኑ በማብራራት፣ በብሔራዊ አቀፍ ደረጃ ዓለም አቀፍ የሆኑት ሕጎች ካግባብነት ውጭ እየሆኑ እግብር ላይ እንዳይውሉ የሚፈጠሩት ፖለቲካዊ የመሳሰሉት መሰናክሎች እንዲቀረፉ የሁሉም ጥረት ይጠይቃል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.