2010-10-15 14:10:40

ሲኖዶስ ጳጳሳት መሃከለኛ ምስራቅ፡


ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ እዚህ ቫቲካን ውስጥ የተጀመረው የመካከለኛው ምስራቅ ጳጳሳት ሲኖዶስ እየቀጠለ ነው ፡ ዘካቶሊካውያን ኢትዮጵያ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሱራፊኤል ፡ እና በኤርትራ የባረንቱ ኤጳርቅና ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቶምስ ዖስማን በዚሁ ሲኖዶስ ተሳታፊ ናቸው ።

ይህ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጳጳሳት ሲኖዶስ ሕብረት እና ምስክርነት የተሰየመ መሪ ቃል ይዞ እየተካሄደ መሆኑ የሚታወስ ነው ፡

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክትሶ በዚሁ ጥዋት እና ከቅትር በኃላ እየተካሄደ ያለውን ሲኖዶስ ተሳታፊ መሆናቸው አይዘነጋም ።

ይሁን እና ትናትና ከቀትር በኃላ ሀገራት አቀፍ የአይሁድ ኮሜቴ ወኪል ራቢን ደቪድ ሮዝን ለሲኖዶሱ ንግግር አድርገዋል ።

ራቢን ደቪድ ሮዝን በአሁኑ ወቅት በካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እና የእስራኤል ህዝብ ግንኙነት በመልካም ሁኔታ እንደሚገኝ ጠቅሰው፡ ለግንኘቱ መልካምነት ሲገልጡ ፡ ከአስር ዓመታት በፊት የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እስራኤል ጉብኝት እና በርካታ ክርስትያኖች ወደ እስራኤል መግባታቸው እና ከአይሁድ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት በማድረግ የርስ በርስ ሰብአዊ ትውውቅ መካሄዱ በክልሉ የሚገኙ ካቶሊካውያን ተቋሞች መልካም ሙያ የመሳሰሉ መሆናቸው አስገንዝበዋል።

ውስብስብ ያለውን የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ሁኔታ ቅድስት መንበርን እንደሚያሳስባት ያመለከቱ ደቪድ ሮዝን እስራኤል በኢዝሁ ክልል ጸጥታ የመጠበቅ ሐላፍነት እና ግዴታ እንዳላት ጠቅሰው ሆኖም ግን በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የሚካሄደው ውይይት ለሰላም ጠቀሜታ እንዳለው አስገንዝበዋል።

ሶውስቱ ሃይማኖቶች ማለት ይሁዲ ክርስትና እና ኢስላም ተቻችለው በሰላም ለመኖር አንዱ የሌላውን ህልውና መቀበል እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል።ሲኖዶሱ ዛሬም ቀጥሎ ውለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.