2010-10-15 15:04:31

ምያንማር፣ ፍትሕ ነጻነት ሰላም እና ብልጽግና


የያንጎን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቻርለስ ማኡንግ ቦ እ.ኤ.አ. ህዳር 7 ቀን 2010 ዓ.ም. በምያንማር የሚካሄደው ሕዝባዊ ምርጫ መሠረት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት በምያንማር ፍትሕ ነጻነት ሰላም እና ብልጽግና ለማረጋገጥ RealAudioMP3 የሚያስችለው መንገድ እንዲፈጠር ሁሉም ዜጋ እንዲጸልይ ጥሪ እንዳቀረቡ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ብፁዕ አቡነ ማኡንግ ቦ ሕዝባዊ ምርጫ የእንያንዳንዱ የመምረጥ መብት ያለው ዜጋ ያጠቃለለ የአገር ጥቅም እንዲቀድም የሚያሳስብ ነው፣ ስለዚህ የመምረጥ መብት ያለው በምርጫው መሳተፍ ግዴታ አለበት፣ እያንዳንዱ በሚሰጠው ድምጽ አማካኝነት ለሰላም ለፍትህ ለነጻነት እና ለእድገት በሚደረገው ጥረት ተሳታፊነቱን ያረጋገጣል፣ በዚህ በሚካሄደው ምርጫ የምያንማር ካቶሊክ ምእመናን በአገሪቱ እየታየ ያለው ለዲሞክራሲው ሥርዓት ምሥረታ የሚበጀውን ለውጥ በመደገፍ እና በማበረታታት ጎዳና እንደሚገኝም ባስተላለፉት መልእክት በመጥቀስ፣ ሰላም አለ እድገት እድገትም አለ ሰላም ሰላምም ይሁን እድገትም አለ ፍትህ አይጨበጥም፣ ሁሉም እንደየ ሃይማኖቱ ሊካሄድ ተወስኖ ስላለው ሕዝባዊ ምርጫ አወንታዊ ውጤት እንዲኖረው እንዲጸልይ ምህረት ይቅር መባባል መከባበር እና መቀባበል ይዘራም ዘንድ አደራ እንዳሉም ፊደስ የዜና አገልግልቶ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.