2010-10-13 15:26:48

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ ኣስተምህሮ (13.10.10)


ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ለተለመደው ሳምንታዊ የዕለተ ሮቡዕ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ ኣስተምህሮ መክፈቻ ጸሎት ካሳረጉ በኋላ ከመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 16 ‘ኣምላክ ሆይ! የምታመነው በአንተ ስለሆነ ጠብቀኝ፤ እግዚአብሔርን፡ “ኣንተ ኣምላኔ ነህ፤ ያለኝም መልካም ነገር ሁሉ ከአንተ የተገኘ ነው” እለዋለሁ። በእግዚአብሔር የሚተማመኑ ቅዱሳን እንዴት የተመሰገኑ ናቸው፤ የእኔ ታላቅ ደስታ ከነርሱ ጋር መሆን ነው። ሐሰተኞች አማልክትን የሚከተሉ፤ በርሳቸው ላይ ብዙ ችግር ያመጣሉ፤ እኔ ግን ሐሰተኞች የሆኑትን የእነርሱን አማልክት ኣላገለግልም፤ በሚያቀርቡላቸው መሥዋዕት ኣልተባበርም። እግዚአብሔር ሆይ! አለኝታየ አንተ ነህ፤ አንተ የሚያስፈልገኝን ሁሉ ትሰጠኛለህ፤ ለወደፊትም የሕይወቴ ዋስትና አንተ ነህ።’ የሚለው በተለያዩ ቋንቋዎች ከተነበበ በኋላ በጣልያንኛ ቋንቋ ሰፋ ያለ ትምህርት ኣቅርበው የሚከተለውን ኣጭር ኣስተምህሮ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ኣቅርበዋል። ‘ውድ ወንሞቼና እኅቶቼ፤ ዛሬ በምናቀርበው ትምህርተ ክርስቶስ በመሀከለኛው ክፍለ ዘመን በሰቂለ ኅልናዊ ኣስተንትኖ ባሕታዊት ብፅዕት ኣንጀላ ዘፎሊኞ እንመለከታለን። ብፅዕት ኣንጀላ በ1248 ዓም ፍሊኞ በሚባለው የኡምብርያ ክፍለ ሃገር ከተማ በጣልያን ኣገር ተወለድች። ኣንጀላ ጠንቃቃ ሚስትና እናት ነበረች። ኣንዴ በገዳማዊ ሕይወት የጸና ድህነት የሚከተሉ የሰኣልያንና ዐቃብያን ማሕበርን ታስተናንቀው ነበር፤ ሆኖም ግን በሕይወትዋ ያጋጠምዋት ኣደጋና ሥቃይ በኃጢኣትዋ እንድትጸጸት ምክንያት ሆንዋት፤ በ1285 ዓመተ ምሕረትም ቁርጥ ውሳኔ በመውሰድ ሕይወትዋን ለወጠች። በራእይ የተያት የቅዱስ ፍራንቸስኮስ እርዳታን በመለመን በሳን ፈሊቺኣኖ ኑዛዚዋን ኣደረገች። እናትዋ ባለቤትዋና ልጆችዋ በሞት በተለይዋት ግዜ የነበራትን ንብረት ሁሉ ሽጣ የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ሦስተኛ ማኅበር ኣባል ሆነች፡ በ1309 ደግሞ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።

የብፅዕት ኣንጀላ ዘፎሊኞ መጽሓፍ ስለ መታደስዋ ይተርካል፤ ለእኛም ወደ ጌታ ለመመለስ ኣስፈላጊ መንገዶችን ያስተምረናል፤ መንገዶቹ ደግም ንስሓ ትሕትናና ጸጸት ናቸው። መጽሓፉ ብፅዕት ኣንጀላ ያደርጋቸውን ብዙ ሰቂለ ኅልናዊ ኣስተንትኖዎች እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር የነበራት ውህደት ብርቱ በመኖሩ ለትጽፋቸውና ልትገልጣቸው ያልቻላቸው ራእዮችን ይተርካል፤ የነበራት የኅጢኣትና የቅጣት ፍራቻ በየዕለቱ እያደገ የመጣ የእግዚአብሔር ፍቅር ተወገደላት፤ ይህም በፍኖተ መስቀል ወደ ፍኖተ ፍቅር ኣደረሳት። ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፤ እግዚአብሔር ‘ኣምላኬ ሆይ! ከእርሱ በላይ ሌላ የማይገኘውን ኃይለኛና ሊገለጥ የማይቻል ከፍተኛው ምሥጢር የሆነውን ፍቅርህ ለማወቅ ኣብቃኝ’ የሚለው ጸሎትዋን እንድንካፈል ያድርገን።’ ሲሉ ትምህርታቸው ከጨረሹ በኋላ በተለያዩ ቋንቋዎች ሰላምታና ትምህርት ኣቅርበው ‘ኣቡነ ዘበሰማያትን’ በላቲን ከምእመናኑ ጋር ኣዚመዋል፤ በመጨረሻም ሓዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.