2010-10-13 14:33:33

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ክርስቶስን ዘወትር በየትም ሥፍራ ማበሰር


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባላቸው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሥልጣን እና ኃላፊነት መሠረት ሞቱ ፕሮፕሪዮ - በራስ አነሳሽነት “ቤተ ክርስትያን የትም በሁሉም ሥፍራ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ታበሥር ዘንድ ኃላፊነት RealAudioMP3 እና ግዴታ አለባት የሚል መሠረታዊ ሀሳብ የሰፈረበት ሐዋርያዊ መልእክት በማስደገፍ፣ እዲቋቋም ውሳኔ የሰጡበት የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል የሚያነቃቃ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ተልእኮውን በይፋ ጀምረዋል።

“ኢየሱስ ወደ እነርሱ ቀረበና እንዲህ አላቸው፥ “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል እንግዲህ ወደ ዓለም ሕዝብ ሁሉ ሂዱ በአብና በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው የእኔ ደቀ መዛሙርት አድርጉአቸው፣ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲፈጽሙ አስተምህሩአቸው፣ እነሆ እኔ እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ሁሉጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 28 ከቁጥር 18 እስከ 20 ያለው ለእየሱስ ቃል ቤተ ክርስትያን ታማኝ በመሆን፣ ዓለም በጠቅላላ የወንጌል ውበት እንዲያውቅ ከማድረግ ጥሪ ፈጽማ እታመነታምም፣ እታፈገፍግምም ስለዚህ የአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ ለቤተ ክርስትያን አስፈላጊ እና መተኪያ የሌለው ተልእኮ፣ የማንነትዋ ልዩ መግለጫ እና ትርጉም ነው። አዳዲስ ክስተቶችን እንደየ ባህሉ፣ አካባቢው በማንበብ ታሪካዊ ሁናቴዎችንም ግምት በመስጠት፣ እንዲሁም በአሁኑ ዘመን፣ ለዘመናት በቃለ ወንጌል በተሰበከበት እና በሰረጸበት ማህበርሰብ እና ባህል እየተዛመተ ካለው ከእምነት የመራቁ ምልክት እና ማኅበራዊ ለወጦች ጋር እራስዋን በማነጻጸር እና በማመዛዘን አስፍሆተ ወንጌል ዳግም ለማነቃቃት የጥሪዋ ግዴታ እና ኃላፊነት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አዲሱን የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት እንዲቋቋም ውሳኔ በሰጡበት ሐዋርያዊ መልእክት ዘንድ በማብራራት፣ የዓለም ማኅበረስብ ከወንጌል ለተቀዳጀው ጸጋ እና ከወንጌል ያገኘው ጥቅም የሚያውቀው ቢሆንም ቅሉ ቤተ ክርስትያን በዘመናችን እየተስፋፋ ያለው የቅዱስ ትርጉምን በመዘንጋት እና በማጥፋት ከዚህ በመነሳትም፣ እጥያቄ ውስጥ ፈጽሞ የማይገባው በፈጣሬ ኵሉ ለሁሉም አሳቢ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛ አዳኝ መሆኑ፣ መሠረታውያን የጋራው መወለድ መኖር በቤተሰብ ዘንድ የሚለው ገጠመኝ እና ዋቢ የሆነው ባህርያዊ የግብረ ገብ ህጎች እና እግዚአብሔር ላይ የሚጸናውን እምነት ችላ ማለት ብቻ ሳይሆን፣ ግድ ባለ መስጠት እየተኖረ ያለው ሕይወት ቀርባ በመመልከት እንዲቋቋም ያደረጉት ጳጳሳዊ ምክር ቤት መሆኑ ባስተላለፉት ሐዋርያዊ መልእክት አስገንዝበዋል።

በጠቅላላ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ እንዲሁም ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ እና የእግዚአብሔር አገልጋይ ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በተለያየ መልኵ አሳሲቢ እየሆነ የመጣው የተዛማጅ የግድ የለሽነት የለንገለንጋ እና ኢ - እግዚአብሔርነት ማለት እግዚአብሔር የለም ማለትም የእግዚአብሀር ኅላዌ ብሎ የለም የሚለው ለየት ባለ መልኵ በምዕራቡ አንደኛው በሚል መጠሪያ በሚታወቀው ዓለም እየተስፋፋ ያለው ባህል በመለየት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ አስፍሆተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ፣ ወንጌላዊ ልኡክነት ዳግም ማነቃቃት ብቻ ሳይሆን፣ የተለያዩ ክስተቶችን ቀርቦ በጥልቀት እና በጥንቃቄ ለይቶ በማወቅ መካሄድ እንዳለበት ባስተላለፉት ሐዋርያዊ መልእክት አሳስበዋል።

ስለዚህ ዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ወይንም ዳግመ ስብከተ ወንጌል አንዳዊ ቀመር-ደንብ- መሠረት የሚከናወን ማለት ሳይሆን፣ አስፍሆተ ወንጌል ተጨባጭ ሁኔታዎችን አቢይ ግምት በመስጠት ከእዚአብሔር ጋር ጥልቅ ግኑኝነት እንዲኖር የሚያግዝ ተልእኮ መሆኑ ባስተላለፉት ሐዋርያዊ መልእክት በመግለጥ፣ እንዲቋቋም ውሳኔ የሰጡበት አዲሱ የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ከሌሎች የተለያዩ የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ጳጳሳዊ ምክር ቤቶች እና ቅዱሳት ማህበር ጋር በመተባበር ቤተ ክርስትያን እና ሕዝበ እግዚአብሔርን የሚያገለግል የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ቲዮሎጊያዊ እና በሥነ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ጥልቅ ትርጉም የሚያጠና በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ፍፈቃድ መሠረት ይፋ የሚያደርግ ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.