2010-10-11 15:11:00

የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ


የቅድስት መንበር የዜና እና የማኅተም ጉዳይ ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በትላትናው ዕለት ባቀረቡት የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ፣ ትላትና ቅ. አ. በይፋ ስላስጀመሩት የመካከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ማእከል በማድረግ የሰላም ዘር በሚል ርእስ ሥር፣ የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ የሰላም ዘር መሆኑ በመተንተን፣ ብፁዓን ጳጳሳት በዚህ ለሁለት ሳምንት በሚያደርጉት ጥልቅ ውይይት፣ መካከለኛው ምሥራቅ የክርስትና ኃይማኖት የተወለደበት ሆኖ እያለ በክልሉ ያለው ማኅበረ ክርስትያን በተለያየ ምክንያት አናሳ የክልሉ ክፍለ ኅብረተሰብ ለመሆን ቢገደድም፣ በዓለም አቀፍ መድረክ ማእክል እንድትሆን እንደሚያደርጋት ገልጠዋል።

የክልሉ ማኅበረ ክርስትያን ያለበት ችግር ለሁላችን የሚመለከት ነው፣ ከዚህ በፊት እንደተከናወነው እያንዳንዱ የመከላለኛው ምሥራቅ አገር የእራሱ ውስጣዊ ጉዳይ ላይ በማተኮር ሳይሆን፣ የክልሉ ጠቅላላ አገሮች የክልላቸው ጉዳይ ውኅደት እና ምስክርነት በሚል ርእስ ሥር በጋራ ለመዳሰስ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ የተጠራ ሲኖዶስ መሆኑ አባ ሎምባርዲ ገልጠው፣ የመጀመሪያው ማኅበረ ክርስትያን በአንድ ልብ እና በአንድ መንፈስ በእየሩሳሌም መወለዱንም የሚያስታውስ፣ የክልሉን ጉዳይ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እና በፍቅር በመመልከት ቂም በቀል በማስወገድ ወደ ሰላም በሚመራውን መንገድ ለመራመድ የሚያነቃቃ በመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የምትገኘው ካቶሊክ አቢያ ክርስትያን ያለው ውህደት ትብብር መደጋገፍ የአንድነት መሠረት ከሆነው ከመንበረ ጴጥሮስ ጋር ያላቸውን ውኅደት መሠረት አንድ ድምጽ አንድ የሰላም ምልክት እና ዘር መሆናቸው የሚመሰከርበት ሲኖዶስ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.