2010-10-11 16:14:36

የምሥራቃውያን ኣብያተ ክርስትያን


ቅዱስ ኣባታችን የምሥራቃውያን ኣብያተ ክርስትያን ከሮማዊት ቤተ ክርስትያን ጋር በመተባበር ማንነታቸውን እንዲያዳብሩ ጥሪ ኣቅርበዋል።

የምሥራቅ ኣብያተ ክርስትያን ካቶሊካዊና ምሥራቃዊ የሆነ ማንነታቸውን እንዲጠብቁ ኣደራ ያሉት ቅዱስነታቸው የምሥራቃውያን ሕገ ቀኖና ከታወጀ ሃያኛ ዓመቱ ላይ ተሰብስበው ስለ ሉዩ ልዩ ተጨማሪና እስከ ዛሬ የተፈጸሙ ኣንቀጾችን በሚመለከት እንዲሁም ኣጠቃላይ ጥናትና ማሻሻል ለማድረግ የሁለት ቀናት ጉባኤ ላደረጉት ኣበውና ሊቃውንት ቅዳሜ ዕለት ተቀብለው ባነጋገሩዋቸው ወቅት ነበር።

ቅዱስነታቸው በመክፈቻ ንግግራቸው ያስታወሱት ዝክረ ጥዑም ር.ሊ.ጳ ዮሓንስ ጳውሎስን ነው፤ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የምሥራቅ ካቶሊካውያን ኣብያተ ክርስትያናት ከዘመናችን ጋር የሚስማማ ራሱ የቻለ ሕገ ቀኖና እንዲኖራቸው መፈለጋቸውና እውን ማድረጋቸው እጅግ የሚመሰገን ተግባር ፈጽመዋል። የዚህ መምርያ ዋና ዓላማ በ5ቱ ጥንታውያን ምሥራቃውያን ኣብያተ ክርስትያን ማለት ኣለክሳንድርያ ኣንጾክያ ኣርመን ኬልቄዶን እና የቢዛንቲን ኣብያተ ክርስያን ከለላ በመሆን ያደጉና በ23 ቡድኖች የቆሙ ኣብያተ ክርስትያን ከላቲናዊ ሕግ የተለየ የራሳቸው እንዲኖራቸው በዚህም ኣዲስ ሓዋርያዊ ግፊትና ኃይል በማግኘት እንዲዳብሩ መሆኑን ገልጠዋል።

ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን በመቀጠል፤ ‘ኣጋጣሚው በእንዚህ ሃያ ዓመታት ሕገ ቀነናው በዕለታዊ የኣብያተ ክርስትያኑ ሕይወት ምን ያህል እተግባር እንደዋለ፤ ባላቸው ሃብታም ምሥራቃዊ ሥርዓት እምነታቸውን ለመኖር ምእመናኑን ምን ያህል እንዳነቃ ለማወቅ ነው፤ በዚህም የዚሁ ሕገ ቀኖና ምንጭ የሆኑ የጥንትዋ ቤተ ክርስትያን ቅዱሳት ምሥጢራት የምሥራቅ ኣብያተ ክርስትያን ካቶሊካዊና ምሥራቃዊ የሆነ ማንነታቸውን እንዲጠብቁ ይረድዋቸዋል፤ ምሥራቃውያን ኣብያተ ክርስትያን ከሮማዊት ቤተ ክርስትያን ያላቸውን ኅብረት ኣጥብቀው ሲይዙ ባብህላቸው ያላቸው መተማመንን በምንም ዓይነት ኣላጓደሉም፤ ስለዚህ የሁላቸው የምሥራቅ ካቶሊካውያን ኣብያተ ክርስትያን ያላቸውን የጋራ ዕሴትና ውርሻ የሆነ ሥርዓትን በመጠበቅ ከትውልድ ለትውልድ ሲተላለፍ የመጣውን የገዛ ራሳቸው ባህልና ሃብት ለመላዋ ቤተ ክርስትያን እንዲዳረስ ማድረግ ነው።’ በማለት ኣደራ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.