2010-10-11 15:10:01

ቅ.አ. ር.ሊ.ጳ. የሬፓብሊክ ክሮአዚያ ርእሰ ብሔር ተቀብለው አነጋገሩ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከትላትና በስትያን የረፓብሊካዊት ክሮአዚያ ርእሰ ብሐር ኢቮን ጆሲፖቪችን ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ። ወቅታዊው የክሮአዚያ እና በቦዝኒያን እና ኤርዘጎቪና የክርአዚያ ዜጎች በተመለከተ ርእሰ ጉዳይ ሃሳብ ለሃሳብ መለዋወጣቸው ሲገለጥ፣ የቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ክፍል እንዳመለከተውም፣ በክሮአዚያ የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን አስተዋጽኦ በባህላዊ እድገት እና በመንፈሳዊው ረገድ በተጨማሪም ክሮአዚያ በኤውሮጳ ኅብረት ለተሟላ ውህደት በምታደርገው ጉዞ ለዚህ ውህደት ክርስትያናዊ መለያዋ መሠረት መሆኑ እንድትገነዘብም ይኽ መለያ እንዲጎላ ቤተ ክርስትያን አቢይ ድጋፍ እንደምትሰጥ የተካሄደው ግኑኝነት እንዳሰመረበት ለማወቅ ተችለዋል።

ርእሰ ብሔር ኢቮን ጆሲፖቪች ከቅዱስ ኣባታችን ተሰናብተው በቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማንበርት በተሸኙት ከቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ጋር መገናኘታቸው የቅድስት መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍል ካሰራጨዋ የዜና ምንጭ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.