2010-10-11 16:18:02

ር.ሊ.ጳ ከኣንድ ዓመት በኋላ በካላብርያ (ላመጽያ ተርመ) ሓዋርያዊ ጉብኝት ያደርጋሉ


እ.አ.አ እፊታችን ጥቅምት 9 ቀን 2011 ዓም ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በላመጽያ ተርመ የምትባል የረጅዮ ካላብርያ ከተማ ሓዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የላመጽያ ጳጳስ ብጹዕ ኣቡነ ልዊጂ ኣንቶኒኦ ካንታፎራና በቦታው የሚገኙ መነኮሳን የቸርቶሳ ኣበምኔት ኣባ ጃክወስ ዱፖጝ ኣመልክተዋል።

ቅዱስነታቸው በቦታው ከደረሱ ጥዋት መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚያሳርጉና ማምሻውንም ቸርቶሲኒ ከሚባሉ የሲታውያን መነኮሳት ኣባላት ጋር ዳዊት ዘሰርክ እንደሚደግሙም ለኦዘርቫቶረ ሮማኖ ጋዜጣ በመሰጡት መግለጫ ኣስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.