2010-10-11 15:12:27

መንበረ ጴጥሮስ፦ አንድ ልብ እና አንድ መንፈስ


ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በመካከለኛው ምሥራቅ ውህደት እና ምስክርነት ኅብረ ባህል ኅብረ ቋንቋ ኅብረ ሃይማኖት የነበራቸው ሁሉ አንድ ማኅበረ አማኞች በመሆን፣ አንድ ልብ እና አንድ መንፈስ ነበራቸው በሚል ርእስ ሥር ትላትና የተጀመረው እ.ኤ.አ. ጥቅምት 24 ቀን 2010 ዓ.ም የሚጠናቀቀው የመካከለኛው ምሥራቅ የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ሂደት በቀጥታ በዳብሊው ዳብሌው ዳብሊው ነጥብ ራዲዮቫቲካና ነጥብ ኦርግ በሚል የድረ ገጽ አድራሻ በኵል ለመከታተል እንደሚቻልም በዚህ አጋጣሚ በማሳወቅ፣ ይህ 185 ብፁዓን ጳጳሳት ያሰባሰበው ሲኖዶስ የመካከለኛው ምሥራቅ ማኅበረ ክርስትያን ሃይማኖታዊ ሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ ጉዳይ የሚዳስስ መሆኑ በቅድስት መሬት የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ርክስትያን ንብረት እና ቅዱሳት ሥፍራ ጠባቂ አባ ፒዛባላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በማብራራት፣ እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ባላት ኵላዊነት ባኅርይ መሠረት በሁሉም አገሮች ባሉት የካቶሊክ አቢያተ ክርስትያን የሚገለጥ ነው ካሉ በኋላ፣ ስለዚህ አነዚህ አቢያተ ክርስትያን ይኸንን ውህደት መርህ በማድረግ አንድነቱን በቃል እና በተግባር የሚመሰክሩ ናቸው። በሊጡርጋዊ ሥርዓት ልዩነት ያለ ቢሆንም ይኽ ልዩነተ ሃብት መሆኑ በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሥር በሚመሰክሩት አንድነት በኵሉ ሃብት መሆኑ ይረጋግጣል።

ሌላው በዚህ ክልል ያለው ማኅበረ ክርስትያን ከሌሎች አቢያተ ክርስትያን ከምስልም እና ከአይሁድ ሃይማኖት ጋር ያለው ግኑኝነት ላይ ያነጣጠረ ሲኖዶስ እንደሚሆን አባ ፒዛባላ በመጥቀስ በዚህ ሥር ከእስራኤል እና ከፍልስጥኤም ጋር ያለው ግኑኝነት ጭምር የሚዳስስ ነው። ይኸንን ሁሉ ግምት የሚሰጥ ሃዋርያዊ ግብረ ኖሎዎ እንዴት መረጋገጥ እንዳለበት የሚያብራራ እና መመሪያ የሚያስቀምጥም ነው ሲሉ፣ የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኒኮላ ኤቶሮቪች፣ ይኽ ሲኖዶስ እንዲካሄድ ለፈቀደው እግዚአብሔር እንዲሁም እቅዱ እግብር ላይ እንዲውል በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ልዩ ክትትል እና መሪነት ቅድመ ዝግጅቱን የመሩትን በማመስገን፣ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መሪ ቃል እና ሀሳብ እንደማይለውም በመግለጥ፣ መካከለኛው ምሥራቅ በተለይ ደግሞ ቅድስት መሬት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምድራዊ ሕይወት ማእከል መሆኑ በማብራራት፣ በዚህ ክልል ተስፋ ፈጽሞ እንዳልጨለመ ሁሉ ዛሬም ነገም በዚህ ክልል ያለው ማኅበረ ክርስትያን ይመሰክረዋል፣ ይህ ለሁሉም አገሮች ክርስትያንም ተስፋ ነው ብለዋል።

የቤተ ክርስትያን አናሥር፣ የክልሉ መንፈሳዊ ኅብረ ሃብት፣ ኅብረ ሊጡርጊያ፣ የሚገለጥበት ብቻ ሳይሆን እነዚህ የመካከለኛው ምሥራቅ ካቶሊክ አቢያተ ክርስትያን በመካከላቸው በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አማካኝነት የሚጸናው አንድነት በጋራ ለመመስከር መጠራታቸው እና እስካሁን ድረስ እንዳከናወኑትም እግብር ላይ ለማዋል ሊከተሉት የሚገባው አዲስ ሓዋርያዊ ግብረ ኖሎው ለመወጠን የሚያግዘው መመሪያ፣ ከሌሎች አቢያተ ክርስትያን እና ሃይማኖቶች ጋር ያላቸው ግኑኝነት በመካከለኛው ምሥራቅ ያለው ማኅበረ ክርስትያን ኅላዌ ውጤታማ እና ንቁ በማድረግ እንዲረጋገጥ የሚመራ ሲኖዶስ ነው ብለዋል።

የእየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ርክስትያን ፓትሪያርክ ረዳት ብፁዕ አቡነ ዊሊያም ሾማሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ የመካከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ መንፈሳዊ እና የተስፋ ሁነት ነው በማለት ሲገለጡት፣ በ 16 አገሮች የሚኖር 5.5 ሚሊዮን ካቶሊክ ምእመናንን የሚወክሉ 185 የሲኖዶስ አበው ያሰባሰበ መሆኑ በማብራራት፣ ስለ ሲኖዶስ ሃሳብ በሁሉም ምእመናን እና አቢያተ ክርስትያን እንዲጸለይ የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲመራው እና እውነት የሚያበሥር እንዲሆን ተጋባእያን ብፁዓን አበው በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ የሚመሩ እውነትን በፍቅር የሚናገሩ እና የሚያበሥሩ ናቸው የሁላችን ጸሎት ያስፈልጋቸዋል።

በመካከለኛው ምሥራቅ ያለው ማኅበረ ክርስትያን ለተለያዩ ዘርፈ ብዙ ችግሮች መጋለጡ መናገር እና የሚደርስበት ስደት መከራ እና አድልዎ ገሃድ ማውጣት ተገቢ ነው። እውነት መናገር መፍራት የለብንም፣ ሆኖም ግን እውነት በፍቅር እና በጥበብ የሚሸኝ መሆን አለበት በፍቅር የሚምራ እውነት እና የሚመሰከር እውነት ለአደጋ ቢያጋልጥም ነጻ ያወጣል።

የሲኖዶሱ ግብ መንፈሳዊነት፣ እርሱም በእግዚአብሔር ቃል ጸንቶ የክልሉ አቢያተ ክርስትያን በመካከላቸው እና ከመንበረ ጴጥሮስ ጋር ያላቸውን ውህደት መኖር እና መመስከር የሚል ነው ብለዋል። ስለዚህ የሲኖዶስ ጠቅላይ ርእስ የሲኖዶስ ግብ ምን መሆኑ በውስጠ ታዋቂነት ይገለጠዋል ሲሉ፣ በእስራኤል የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ብፁዕ እለቡነ አንቶኒዮ ፍራንኮ በበኩላቸውም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ አማኞች ነን ስለዚህ በተስፋ እና በመጠባበቅ የምኖር ነን፣ ተስፋ በሰዎች በሁኔታዎች አማካኝነት በእግዚአብሔር ተግባር ዘንድ ያለ ነው። ስለዚህ የድኅነት ተስፋ ነው፣ ይህ ደግሞ ለሁሉም ሰው ዘር የተሰጥ ጸጋ ነው። ጸጋውን በአንድነት እና በውህደት መመስክር እንዳለበት በተለያዩ ርእሶች ሥር የሚያሳስብ ሲኖዶስ እንደሚሆን አልጠራጠርም ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.