2010-10-08 16:25:37

የምሥራቃውያን ኣብያተ ክርስትያን ሕገ ቀኖና


የምሥራቃውያን ኣብያተ ክርስትያን ሕገ ቀኖና የዛሬ 20 ዓመት ታወጀ፤ ይህንን መነሻ በማድረግ ጳጳሳዊ የሕግ መወሰኛ ጽሑፎች ምክር ቤት ከምሥራቃውያን ኣብያተ ክርስትያን ማኅበርና ከክርስትያን ኣንድነት ጳጳሳዊ ምክር ቤት እንዲሁም ከጳጳሳዊ የምሥራቅ ተቅዋም ጋር በመተባበር የሁለት ቀናት ዓውደ ጥናት ዛሬ ተጀመረ።

የጳጳሳዊ የሕግ መወሰኛ ጽሑፎች ምክር ቤት ሊቀ መንበር የዓውደ ጥናቱ ዓላማ ለመግለጥ ትናንትና በቫቲካን የኅትመትና ዜና ኣደራሽ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ዓውደ ጥናቱ ያለፈውን ታሪክ በመዘርዘር በዓል ለማክበር ሳይሆን ለወደፊት በመመልከት ጥናት ለማካሄድና ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ሲሆን መልካም ኣጋጣሚ ሆኖ ደግሞ የመሀከለኛ ምሥራቅ የጳጳሳት ሲኖዶስ ዋዜማ ላይ ስለሆነ ለዚህም ብዙ ያበርክታል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጠዋል።

መግለጫቸውን በመቀጠል ይህንን ዓውደ ጥናት ለማድረግ በታሰበበት ግዜ ሃሳቡን ተቀብለው እውን እስኪሆን ድረስ ብዙዎች ላሳዪት ትብብር ኣመስግነዋል፤ በተለይም በተለያዪ የቫቲካን ጳጳሳዊ ምክርቤቶችና ማኅበራት የተደረገው መተጋገዝ ግዳዩ የሁላችን መሆኑን ያሳየ ኣመርቂ ተግባር እንደተፈጸመ እንዲሁም የሕገ ቀኖና ሊቃውንት ኣስተማሪዎችና ተማሪዎች ባበረከቱት ከ400 በላይ የሚሆኑ የጥናት ጽሑፎች ጉዳዩን ምን ያህል ትኲረት እንደሰጡት ያመለክታል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ሊቃውንትና የሊሎች ኣብያተ ክርስትያናት ትብብርም የሚመሰገን ነው፤ ሲሉ ባጠቃላይ ለዓውደ ጥናቱ ዝግጅት ያበረከቱትን ሁሉ ኣመስግነዋል።

የምሥራቃውያን ኣብያተ ክርስትያን ሕገ ቀኖና የትኞቹን ኣብያተ ክርስያናት እንደሚመለከት የገለጡ ደግሞ የምክር ቤቱ ጸሓፊ ብጹዕ ኣቡነ ኽዋን ኢግናስዮ ኣርየታ ኦቻኣ ደ ቺንቸትሩ ናቸው፤ ብጹዕነታቸው በመግለጫቸው ሕገ ቀኖናው 23 የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያኖች፡ ክየሰ ሱይ ዩሪስ ማለት በር እሰ ሊቃነ ጳጳስት ሥር በሆነ በፓትርያርክ ወይም በመትሮፖሊታ የሚመሩ በየክልላቸው በሕገ ቀኖናው መሠረት መዋቅሮችና ሥር ዓቶችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ነጻ የሆነ የገዛ ራሳቸው ኣመራር ያላቸው ኣብያተ ክርትያናት እንደሚመለከት ገልጠዋል። እነዚሁ ኣብያተ ክርስትያን በ5ቱ ጥንታውያን መንበሮች ማለት የኣለክሳንድርያ የኣንጾክያ የኣርመን የካልደይ እና የቢዛንቲን ኣብያተ ክርስትያን ክለላ ናቸው፤

በመጨርሻዎቹ ሃያ ዓመታት በጦርነትና በፖሎቲካዊ ችግር ኣንዳንድ ለየት ያሉ ማለት ፓርቲኩላር ግዝያዊ መምርያዎች ማድረግም የግድ ሆኖናል፤ ስለዚህ በዚሁ ዓውደ ጥናት እነዚህ ነገሮች በጥልቀት ይጠናሉ፤ ሌላው ነጥብ ደግሞ የኣብያተ ክርስትያናት ኣንድነትን የሚመልከት ይሆናል፤ ሲሉ በዓውደ ጥናቱ የተለያዩ ሥርዓቶችን የሚያቀናጅ ለሙሉ ቤተ ክርስትያን የኣንድነት መንገድ የሚከፍትና የምሥራቃውያን ኣብያተ ክርስትያን ዕሴቶችን የሚግልጥ እንዲሆን ያላቸውን መልካም ምኞት ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.