2010-10-08 16:27:19

ሢመት


የኮር ኡኑም ውሑድ ልብ ሊቀ መንበር ብጹዕ ካርዲናል ፓውል ጆሰፍ ኮርደስ ሕገ ቆኖና እንደሚያመለክተው በዕድሜ ገደብ ምክንያት ኃላፊነታቸውን ለቅዱስ ኣባታችን ማስረክባቸውና ቅዱስ ኣባታችንም እንደተቀበሉት በእርሳቸው ምትክ ደግም የኮናክርይ ጳጳስ የነበሩና በዚሁ ግዜ የስብከተ ወንጌል ማኅበር ጸሓፊ ሆነው በማገልገል ያሉትን ብጹዕ ኣቡነ ሮበርት ሳራህ የኮር ኡኑም ወይም ውሑድ ልብ ሊቀ መንበር እንዲሆኑ ሾመዋል።

ብጹዕ ኣቡነ ሮበርት በ1945 ዓም በጊኒ ተወልደዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የስለ ካህናት የሚያስብ ማኅብር ኃላፊ ብጹዕ ካርዲናል ክላውድዮ ሁመስም ሕገ ቆኖና እንደሚያመለክተው በዕድሜ ገደብ ምክንያት ኃላፊነታቸውን ለቅዱስ ኣባታችን ማስረክባቸውና ቅዱስ ኣባታችንም ጥያቄኣቸውን እንደተቀበሉት በእርሳቸው ምትክ ደግሞ የቪቶርያና ሥዩመ ጳጳስና እስካሁን የማኅበሩ ጸሓፊ ሆነው ያገለገሉትን ብጹዕ ኣቡነ ማውሮ ፕያቸንዛ የማኅበሩ ኃላፊ እንዲሆኑ ሾመዋል።

ብጹዕ ኣቡነ ማውሮ በ1944 ዓም በጀኖቫ ጣልያን ኣገር ተወልደዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.