2010-10-07 16:00:19

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ ኣስተምህሮ (06.10.10)


ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ የተለመደውን ሳምንታዊ የዕለተ ሮቡዕ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ ኣስተምህሮ መክፈቻ ጸሎት ካሳረጉ በኋላ ከመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 18 ‘እግዚአብሔር ሆይ! ኃይል የምትሰጠኝ ኣንተ ስለሆንህ፥ እወድሃለሁ። እግዚአብሔር መጠጊያዬና ጠንካራ ምሽጌ ነው፥ ኣምላኬ ጠበቃዬ ስልሆነ፥ ከእርሱ ጋር በድኅንነት እኖራለሁ፤ እርሱ እንደ ጋሻ ይከላከልልኛል፤ ረዳቴም ሆኖ በሰላም ያኖረኛል፤ ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ እርሱም ከጠላቶቼ ያድነኛል። እግዚአብሔር ሕያው ነው፥ መጠጊያ የሆነኝ ኣምላክ ይመስገን፤ ያዳነኝም አምላክ ከፍ ከፍ ይበል። እርሱ ጠላቶቼን ይበቀልልኛል፤ መንግሥታትንም ከበታቼ ኣድርጎ ያስገዛልኛል፤ ከጠላቶቼም ያድነኛል። እግዚኣብሔር ሆይ! በጠላቶቼ ላይ ድልን ታጐነጽፈኛለህ፤ ከግፈኞችም ታድነኛልህ። ስለዚህ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፥ ስምህንም በዝማሬ እወድሳለሁ። መርጦ ልቀባው ንጉሥ፤ ለዳዊትና ለዘሩ፤ እግዚአብሔር ድልን በድል ያጐናጽፈዋል፤ የማያቋርጥ ፍቅሩንም ለዘላለም ያሳየዋል።’ የሚለው በተለያዩ ቋንቋዎች ከተነበበ በኋላ የሚከተለውን ኣስተምህሮ ኣቅርበዋል።

ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፤ ዛሬ ስለእርሷ ለመናገር የምፈልገው ትልቋ ቅድስት ገርትሩድ ባለፈው ሳምንት ስለ ሴት ልጆች ገዳማዊ ሕይወትና ያደረጉት የስነ ጽሑፍ ኣስተዋጽኦ በተናገርንበት ግዜ ወድ ጠቅስነው ወደ ሀልፍታ ገዳም ይወስደናል። በ13ኛው ክፍለ ዘመን በምንኲስናና በሰቂለ ኅሊናዊ ጸሎት ገናና ከነበሩ ትልቋ ገርትሩድ ኣንድዋ ናት፤ ትልቅ ያሰኛት የነበራት ትልቅ የባህልና የወንጌል እውቀት ነው፤ በሕይወትዋና በትምህርትዋ ለክርስትና መንፈውነት ትልቅ ኣበርክቶ ኣደረገች። በልዩ የተፈጥሮ ሥጦታዎችና ችሎታዎች እንዲሁም በልዩ ጸጋ የተሸለመች ጠለቅ ያለ ትሕትናና ለጓደኛ ድኅነት የሚቃጠል ቅናት የነበራ በኣስተንትኖ ግዜ ከእግዚአብሔር ጋር ኃያል ኣንድነት የነበራትና ችግረኛን ለመርዳት ዘወትር ዝግጁ የነበረች ወደር የሌላት ልዩ ሴት ነበረች።

ባለፈው ሮብ ስለእርሷ የተናገርነው ቅድስት ማቲልደ ዘሃከቦርን እና ሌላዋ ትልቅዋ የብህትውናና የምንኩስና ኣብነት ማቲልደ ዘማግደበርግ በእናታዊ ጣፋችና መልካም የመተባበር መንፍስ በእመምኔት ገርትሩድ ሲመራ የሀልፍታ ገዳም ኣብቦ ነበር። እነዚህ ሶስት መነኲሴዎች ለሀልፍታ ገዳም ትልቅ የዕውቀትና የመንፈሳውነት መዝገብ ችረዋል፤ ገዳሙም በእግዚአብሔር በመተማመን መንፈሳዊ ፕሮግራሙን በድንብ አጸና። ገዳሙ የገዳም የምንኲስናን ሕይወት ብቻ ሳይሆን የቅዱስ መጽሓፍ የሥር ዓተ ኣምልኮ የሃይማኖተ ኣበው እና የኣቡነ ብሩክ ሕገ ግዳም በደምብ እንዲጠናና እንዲስፋፋ ታላቅ ኣበርክቶ ኣድርገዋል።

ቅድስት ገርትሩድ ጥር 6 ቀን 1256 ዓም በበዓለ ኣስተር እዮ ተወለደች፤ ስለ ቤተ ሰቦችዋና ስለ ልደት ቦታዋ የሚታወቅ የለም፤ ገርትሩድ በጽሑፍዋ የዚህ ምሥጢር ስትገልጥ ጌታ ራሱ እንደገለጠላት እንዲህ ትላለች፤ በመዝሙረ ዳዊት ማደርያየ እንድትሆን መረጥህዋት ምክንያቱም በእርሷ ያለው ደስ የሚያሰኝ ሁሉ የእኔ ሥራ እንዲሆን እንዳለው እግዚኣብሔር ገርትሩድን ከቤተ ሰቦችዋ ሁሉ ኣራቃት፤ ይህም የሆነበት ምክንያት በሥጋ ዝምድና ማንድ እንዳያፈቅራት በዚህም የሚያንቀሳቅሳት ፍቅር የእግዚኣብሔር ብቻ ይሆናል’ በማለት ትገልጠዋልች።

ያኔ ይደረገ እንደበረው ሁሉ ለመልካም ኣስተዳደግና ለትምህርት በ5 ዓመት ዕድሜዋ በ1261 ዓም በገዳም ገባች። በመዝገበ ዕለት መዘከርዋ እንደዘገበችው የሕይወትዋ ዋና ጉዞ እዚህ ይጀምራል፤ ጌታ በፍቅርና ወደር በሌለው ምሕረቱ እንዴት እንደተንከባከባት ስትገልጽ ‘ጌታ ሆይ ኣንተ ባትረዳኝ ኖሮ፤ በነበረኝ የኣእምሮ ጨለማነት ምንም ሳይረዳኝና ኣለምንም ጸጸት ደስ ያለኝን ነገር ለማሰብ ለመናገር ወይም ለማድረግ ባልተጠራጠርኩም ነበር፤ እንደ ኣረሜን በተመላለስኩ ነበር፤ ሆኖም ኣንተ ከሕጻንነቴ ማለትም ከ5 ዓመት ዕድሜዬ በቅዱስ መቅደስህ እንድኖር በማድረግ ለኣንተ ከተሰጡ የምትወዳቸው ጋር እንድማር ኣደረግሀኝ’ ብላ ጻፈች።

ገርትሩድ ኣስደናቂ ተማሪ ነበረች፤ በኣንደኛና መለስተኛ ደረጃ የተዘጋጀውን ትምህርት በደምብ ተማረች፤ ከየት እንደመጣች ባናውቅም ስለ ወጣትነት ዕድሜዋ ብዙ ጽፋለች፤ ማንበብ ሙዚቃና መዝሙር እንዲሁም ሥነ ጥበብ እንደምትወድ፤ ኃያል ጠባይ እንደነበራት ቆራጥና ችኩል መሆንዋ፤ በመግለጥ ጥፋተኛ መሆንዋና ለጥፋትዋ ምሕረት በመጠየቅ እንድትለወጥ በትሕትና ምክርና ጸሎት ትጠይቅ ነበር፤ ኣንዳንድ ሰዎች እግዚኣብሔር እንዴት ኣድርጎ ይህን ያህል በመጠበቅ መረጣት ብለው እስኪደነቁ ድረስ ኃይለኛ ጠባይዋና ኣንዳንድ ጉድለቶችዋ እስከ መጨረሻ ህይወትዋ ኣልተለይዋትም።

ለ20 ዓመታት ያህል ትምህርትዋን ፈጽማ እስከ መመንኰስዋ ድረስ የሆነ ልዩ ነገር ምንም ኣልነበረም፤ ብቻ ጥናትና ጸሎት ዋና ዕለታዊ ተግባርዋ መኖሩ ይገለጣል፤ ለኣስተማሪዎችዋ ከደናግሉ መሃከል የበለጠች ተማሪ መኖርዋና በተለያዩ የትምህርት መስከች ኣመርቂ ውጤት ያገኘች ጐበዝ ተማሪ ነበረች። ሆኖም ግን በ1280 ዓም በዘመነ ምጽኣት ሁሉ ነገር ያስጠላታል፤ መንፈሳዊ ድርቀት ያድርባታልና ሁሉም ይጨልማታል፤ ከኣንድ ዓመት በኋላ ግን በጥር ወር በእመቤታችን በዓለ ንጽሕ ዋዜማ ላይ ጌታ ጋርዶዋት የነበረ ጨለማን በብርሃን ተካላት፤ የነበራትን መናውጥና ሥቃይ ጌታ በጣዕሙና በፍቅሩ ኣራቀላት፤ ይህንን ፈተና ብርቱ ቢሆንም ቅሉ ገርትሩድ ግን እንደ እግዚአብሔር ስጦታ ተቀበለችው፤ ‘እግዚአብሔር ይህንን የሰጠኝ የነበረኝን የከንቱ ግንብ የመነኲሲት ስምና ልብስ ብለብስም በት ዕቢት ተሳሳቼ ከነበርኩት ሊመልሰኛና ድኅነቱን እንዲያሳየኝ ነው’ በማለት ትገልጠዋለች።

ገርትሩድ በተሰጣት ራእይ ኣንድ ወጣት ነፍስዋን ጋርዶ ከነበረ እሾህ እንድትወጣ በእጅዋ ይዞ መራት፤ መርጦ ከመከራው ስላውጣት እጅ ስትናገርም ‘በዛይ እጅ ጠላቶቻችን በመክሰስ የቸነክሩት ምልክት ኣየሁ’ በማለት በመስቀል ላይ በመዋል በደሙ ያደነነ የጌታ እጅ መሆኑን እንዳወቀችው ትገልጣለች።

ገርትሩድ ከዚህ ራእይ በኋላ ሕይወትዋ ባጠቃላይ ተለውጦ ከጌታ የነበራት ኣንድነት ኣሳደገችው፤ በተለይ በተለያዩ የሥር ዓተ ኣምልኮ ወቅቶች፤ ዘመነ ምጽ ኣት ልደት ጾመ ኣርባ ትንሣኤና በእመቤታችን ድንግል ማርያም በዓላት በሕመም ተማቃ እንዳትዘምር በተከለከለችበትም ግዜ ሳይቀር በብርቱ መንፈሳውነት ትሳተፍ ነበር፤ እንደ ቅድስት ማቲልደ ሥር ዓተ ኣምልኮን የመንፈሳዊ ሕይወትዋ ምንጭ በማድረግ ገር በሆነ መንገድ ታጣጥመው ነበር።

የሕይወትዋ ታሪክ ሁለት ዓይነት የሕይወትዋ ኣቅጣጫ ለውጦች ያመለክታል፤ ኣንደኛው በትምህርት ዘመንዋ ከዓለማዊ የሳይንስና የፍስፍና ትምህርት ወደ ንባበ መልኮት ትምህርትና ገዳማዊ ሕይወት ያደረገችው ለውጥ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እርስዋ እንደምትገልጠው ከግድ የለሽ ኑሮ ወደ ልዩ የተልእኮ ቅናት ያለበት ጠለቅ ያለ የጸሎት የኣስተንትኖና የሰቂለ ኅሊና ሕይወት መለወጥ ነው። ከእናትዋ ማኅጸንና ገና ሕጻን ሳለች የመረጣት ጌታ በገዳሙ ማእድ እንድትካፈል በማድረግ፤ በጸጋው ከኣፍ ኣዊ ሕይወት ወደ ውሳጣዊ ሕይወት የዚህ ዓለም ነገሮች ከማሰብ መንፈሳዊ ነገሮችን ለማፍቀር ጠራት።’ ገርትሩድ ቅዱስ ኣጎስጢኖስ እንደሚለው ከጌታ እጅግ ርቃ እንደነበረች በምድረበዳ ትኖር እንደነበረች እውነትን በትምህርትና ጥናት ለማግኘት በሳይንስና ፍልስፍና ያካሄደችው ኣሰሳ መንፈሳዊ ጥናቶችን ቸል ማለትዋን ኣሁን ባለችበት የኣስተንትኖ መንፈሳዊ ተራራ ስትመለከተው ‘ኣሮጌውን ሰው ጥየ ኣዲሱን ሰው ለበስኩ’ ስትል ነበረች፤ ከሰዋስው ትምህርት የንባበ መለኮት ትምህርትን መረጠች በዚህ ግዜ ቅዱስ መጽሓንና ሌሎች መንፈሳውያን ጽሑፎችን ጠንቅቃ ኣጠናች፤ ልብዋን ምርጥ በሆኑ ጣፋጭና ጠቃሚ የቅዱስ መጽሓፍ ጥቅሶች ትሞላ ነበር፤ ስለዚህም ሁል ግዜ ምክርዋን ለመጠየቅ ለሚመጡት ሁሉ የሚሆን የምያንጽና ብቃት ያለው የቅዱስ መጽሓፍ ጥቅስ ትነግራቸው ነበር፤ እንዲሁም እምነትን በሚመለከት ለሚከራከርዋት በቂ የቅዱስ መጽሓፍ ጥቅሶች በመስጠት ኣፋቸውን ታስይዛቸው ነበር።

ቅድስት ገርትሩድ ሁሉን ነገር ወደ ሓዋርያዊ ግብረ ተል እኮ ለወጠችው፤ ለቤተ ክርስትያን በመተማማንና እርሷን በማፍቀር የእምነት እውነት ጥራት ባለበት ቀለል ባለ መንገድ በጸጋና በሚማርክ መንፈስ ለሁሉም እንዲዳደረስ ሌት ተቀን መጻፍ ጀመረች፤ ጽሑፎችዋም የንባበ መለኮት ኣስተማሪዎች ሳይቀር የሚጠቀሙት ለሁም የሚያገልግል ሆነ፤ የሀልፍታ ገዳም ከዘመናት በኋላ በደረሰው መውደም ከጽሑፎችዋ ጥቂት ብቻ ቀርተዋል።

ቅድስት ገርትሩድ በቃልዋና በኣብነትዋ ለሌች ብዙ ኣስተማረች፤ ለገዳማዊ ሕይወት የማትነቃነቅ ምሶሶ ሆና እንደምትኖር የሕይወት ታሪክዋን የጻፉ ይገልጣሉ፤ ለጸሎት ለንስሓ ለተጋድሎ እና ለሕገ ገዳም የነበራት ኣክብሮት ልዩ ነበር፤ እግዚኣብሔር ወደ እርሱ ጠርቶ በብዙ ጸጋ እንደሸለማት ብትገልጥም በትሕትና የማይገባኝ ሳለሁ እግዚአብሔር በጸጋው መረጠኝ ብላ ትጽፍ ነበር። ሁኔታዋን በማወቅም ለእግዚኣብሔር ፍቃድ በልበ ሙሉነት ሁለንትናዋን ሰጠች።

ከተቀበለቻቸው ጸጋዎች ለእርሷ ልዩ የሆኑ ሁለት ነገሮችን በጽሑፍዋ ትገልጣለች፤ በልብዋ ያተማቸው የጌታ ቊስሎች ጥልቅ የሆኑ የፍቅሩ ምልክቶች፤ ሁለተኛው ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያምን እንደ ጠበቃዋና እንደ እናትዋ መስጠቱ በተለያዩ ግዜ ለእርሷ ሲያማጥናት ያሳያት ፍቅር ናቸው። በእንዲህ ያለ ሁኔታ ከጌታ ጋር ኣንድ በመሆን በፍቅሩ ተውጣ ሳለች የዚህ ዓለም ሕይወትዋን ኅዳር 17 ቀን 1301 ዓም በ46 ዓመት ዕድሜዋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።

የቅድስት ገርትሩድ ሕይወት እንደ ማንኛውም ታሪክ ስላለፉ ነገሮች ማውራት ሳይሆን ለዘወትር የምሆኑ ለክርስትያናዊ ሕይወት ትልቅ ትምህርት ቤት ነው፤ ቅድስት ገርትሩድ ትክክለኛ ሕይወትና መንገድ ታሳያናለች፤ ይህም ከጌታ ኢየሱስ የሚፈጥር ጓደኝነት ነው፤ ይህ ጓደኝነት ቅዱስ መጽሓፍን በማፍቀር ሥር ዓተ ኣምልኮን በማፍቀር ጥልቅ እምነት በመኖር እና በእመቤታችን ፍቅር ልንማረው እንችላለን፤ በዚህ መንገድ ጌታን በእውነት እናውቃለን እውቀቱም እውነተኛ ደስታን ይሰጠናል፤ ይህን ደስታ የኑሮ ዘመናችን ግማሽ ክፍልን ሊይዝ ይችላል፤

በማለት ትምህርታቸውን በማመስገን ከደመደሙ በኋላ ትናንትና የተዘከረው የመቊጠርያ በዓል ኣስታውሰው፤ የጥቅምት ወር ለማርያም የተሰጠ የመቊጠርያ ጸሎት ወር ነው፤ ስለዚህ ሕዝበ ክርስትያን በመላው የዚህን ጸሎት ክብርና ጥቅም በመረዳት ጸሎተ መቊጠርያ እንዲያዘወትሩ ኣደራ በማለት በሰላምታና በቡራኬ ትምህርታቸውን ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.