2010-10-05 15:58:57

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ


በየትም ሥፍራ ይፈጸምም ማንኛው ዓይነት የወንጀል ተግባር የሞት ፍርድ ምክንያታዊ እና ተቀባይነት አያሰጠውም። የሞት ቅጣት ውሳኔ ፍትኅ ሊሆን አይችልም። በተለያየ መልኩ በቻይናም በኢራን በተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት በህንድ RealAudioMP3 በኢንዶነዢያ በሳዑዲ አረቢያ እና በሌሎች አገሮችም ይሁን የሞት ፍርድ ምክንያታዊ ሊሆን አይችልም። ምክንያታዊ ሊያደርገው የሚችል ወንጀል ጨርሶ አይኖርም። ጸረ ሕይወት የሆነ ተግባር ሁሉም ምክንያት የለውም።

የሞት ፍርድ ለፍትኅ ያለን ጥማት ፈጽሞ አያረካም። ስለዚህ በዓለማችን ለሞት ፍርድ የሚያበቁ ናቸው ተብለው የሚዘረዘሩት የወንጀል ዓይነቶች፣ ሁሉም ባንድላይ ቢጠቃለሉም የሞትን ፍርድ ተቀባይነት የሚያሰጠው ምክንያት ለማቅረብ ብቃት አይኖራቸውም። ሰለዚህ ፍትህ በጸረ ሞት ተግባር የሚረጋገጥ እንዳልሆነ የቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ባቀረቡት ርእሰ አንቀጽ በማብራራት፣ የሰው ልጅ ሕይወት ክብር በማረጋግጥ ብቻ ነው ፍትሕ ለመጨበጥ የሚቻለው፣ የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊን ዋቢ በማድረግ በ ቍ. 2267፣ “ነገር ግን ያለ ደም መፍሰስ የሕዝብ ደኅንነት ከጥቃት መጠበቅ መከላከል ከተቻለ የመንግሥት ባለሥልጣናት ይህን መንገድ ቢከተሉም ደግሞ ለሰብአዊ ክብር ተገቢ የሆነ ዘዴ ነው።” ይላል፣ ሕይወት በፍርደ ሞት መጠበቅ ብሎን ደኅንነትን እና ጸጥታን ዋስትና ማረጋገጥ ፈጽሞ አይቻልም ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.