2010-10-05 16:00:17

ዓለም አቀፍ ቀውስ በሚታይበት ዘመን በጋራ መኖር


በቅዱስ ኤጂዲዮ የሚጠራው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ማኅበር ሁለ በየዓመቱ የሚያዘጋጀው ዓለም አቀፍ የሰላም ጉባኤ መርሃ ግብር መሠረት የዘንድሮው በስፐይን ባርቸሎና ከተማ እያካሄደ መሆኑ ለማወቅ ሲቻል፣ ቅዱስ አባታችን የቅድስት RealAudioMP3 መንበር ዋና ጸሓፊ በብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነን በኩል ለጉባኤው ባስተላለፉት መልእክት፣ በዚህ ዘርፈ ብዙ ግጭት እና ቀውስ በሚታይበት ዘመን ሁሉም ሃይማኖቶች ሰላምን ለማገልገል እና ሰላማዊ የማኅበራዊ ኑሮ ለማረጋገጥ የተጠሩ መሆናቸው እና ይኸንን ጥሪያቸው እግብር ላይ እንዲያውሉ መሆናዊ ኃላፊነት እና ግዴታ አለባቸው በማለት ቅዱስ አባታችን ለተጋባእያኑ ሰላምታን በማቅረብ፣ የእያንዳንዱ ሰው በማንም የማይሻረው ሰብአዊ ክብሩ በሙላት እንዲረጋግጥ ሁሉም ሃይማኖቶች መላውን ማኅበረሰብ ለዚህ ዓላማ መነቃቃት ግዴታ አለባቸው ጥሪያቸውም ነው ብለዋል።

የሰው ልጅ እውነተኛውን ዓለም አቀፍ የወንድማማችነት መንፈስ በመከተል በመከባበር እና በመቀራረብ እንዲኖር ለዚህ እሴት መሠረት ወደ ሆነው መንፈሳዊ እና ስነ ምግባር ማተኮር እና መከተል እንደሚኖርበት ቅዱስነታቸው በማሳሰብ፣ ሁሉም አማኞች ሰላምን በማገልገል ዓላማ እንዲጠመዱ እና ሰላምን ቅድሚያ እንዲሰጡ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን ይኸንን ዓላማ የጸሎት ሐሳብ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። በጸሎት እና ከጸሎት ብቻ ነው እግዚአብሔርን በሰውል ልብ ውስጥ የዘራው የሰላም የመከባበር መንፈስ ቋንቋ አድርጎ እግብር ላይ ለማዋል የሚቻለው። ከጸሎት ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያበቃው ኃይል ይገኛል፣ ስለዚህ ይኸንን ኃይል በመሻት በክፋት እና በጥላቻ ሳንረታ የውይይት መንገድ እንከተል፣ እውነተኛ ውይይት ጥላቻን በማግለል ማኅበርሰብ እንደ የአንድ ቤተ ሰብ አባላቶች-ወንድማማቾች ሆኖ እንዲገነባ ያደርጋል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

ይህ ሁሌ በያመቱ የቅዱስ ኤጂዲዮ የካቶሊክ ማኅበር የሚያዘጋጀው ዓለም አቀፍ የሰላም ጉባኤ እ.ኤ.አ. በ 1987 ዓ.ም. መጀመሩ የማኅበሩ ሊቀ መንበር ማርኮ ኢምፓሊያዞ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውሰዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.