2010-10-05 15:57:37

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፣ ሙዚቃ የፍጥረት መልካም ውህደት መግለጫ


የቅዱስ ጴስጥሮስ ባሲሊካ የእድሳት መርሃ ግብር ፍጻሜ ምክንያት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተስኛ የጉባኤ አዳራሽ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ክብር የፍራንዝ ጆሴፍ ሃይድን ቁጥር 94 ውህደ ሙዘቃ RealAudioMP3 ያጠቃለለ የሳንታ ቸቺሊያ ሰማዕትነት ክብር የተደረሰው መዝሙር እንዲሁም የልድዊግ ቫን በትሆቨን ቁጥር 80 የሙዚቃ ድረስት ያካተተ በሳንታ ቸችሊያ የሥነ ሙዚቃ ተቋም መዘምራን እና ኦርኬስትራ በኤስቶኒያ ተወላጅ ኒመ ኻርቪ እና በቺሮ ቪስኮ በተጨመሪም በአንድረያ ሉከሲኒ የተመራ በተከታታይ የሙዚቃ ኮንሰርት መቅረቡ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን የሙዚቃው ኮንሰርት ፍጻሜ ባሰሙት ንግግር፣ የሰው ልጅ በጣዕመ ልሳኑ ፍጥረት ያለውን ኅብረ መልክ እና በውስጡ ያሉትን የተለያየ ኅብረ ሕይወት መካከል ያለው ቅኝታዊ የመልካም እና የውብ ውኅደት መግለጫ ቋንቋ ነው። የፍጥረት ኅብረ ሕይወት ኅያውነቱ መግለጫ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ በመጥቀስ፣ የሙዚቃ ሊቅ አርቮ ፓርት የቅድስት ቸቺሊያ ሮማዊት ሰማዕትነት ክብር የደረሰው መዝሙር፣ ቅድስት ቸቺሊያ በክርስቶስ ላይ ያላት እምነት እና የዚህ እምነት የምስክርነት ልሳን በመሆን የዚህች የሙዚቃ እና የሙዚቀኞች ጠባቂ ቅድስት እምነት እና ሰማዕትነት ጥልቅ መግለጫ ነው ብለዋል።

በሰው ልጅ ዙሪያ እና ውስጥ የሚገኘው የተፈጥሮ የኅያውነት ኃይል፣ ሰው ይኸንን ኅያውነት በጽሞና ጥልቅ መልስ የሚሰጠው፣ በእምነት ነው በማለት፣ ቅዱስ ኢግናዚዮስ ዘ አንጽዮኪያ የተናገረውን በመጥቀስ፣ ከሚጨበጠው እና ከሚታየው ባሻገር ያለው ድምጽ፣ ለማዳመጥ እና ለመታዘዝ የእምነት ቃል እና ጥልቅ ውስጣዊ ጽሞና ያስፈልገዋል።

እምነት ይኸንን ጥልቅ ድምጽ በመከተል በስነ ጥበብ በኵል ብቻ ተገልጦ እና ተነገሮ አይጠቃለለም፣ የላቀ መግለጫው የእውነተኛ ፍቅር ተግባር ነው። እለት በእለት ይኸንን ፍቅር በመኖር፣ ሰማዕትነት የሚጠይቅ ቢሆን የሚሰዋ ፍቅር አድርጎ በማቅረብ፣ ሰማዕትነት በመንግሥተ ሰማይ የሚደረደር የመልካም እና የተወሃሃደ ጣዕመ ሙዚቃ ነው እንዳሉም ከቅድስት መንበር የተላለፈ መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.