2010-10-01 14:22:34

የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያንና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ኮሚሽን በቭየና


እ.አ.አ ከመስከረም 20 ቀን እስከ 27 2010 ስለ ኣብያተ ክርስትያን ኣንድነድ ለመወያየት በቭየና ሲካሄድ የሰነበተው ከካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያንና ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን የተውጣጡ ተወካዮች ኮሚሽን ጉባኤ በወንድማማችነት መንፈስና የመተባበር መተማመን በሰፈነበት ጥሩ ሁኔታ እንደተጠናቀቀ ከቦታው የደረሰ ዜና ያመልክታል።

በጉባኤው መርኃ ግብር መሠረት ተወካዮቹ የተወያዩበት ዋና ነጥብ ‘በኣንደኛው ሺ ክፍለ ዘመን የመንበረ ጴጥሮስ ጳጳስ ለቤተ ክርስትያን ኣንድነት ያበረከተው’ የሚል ር እስ ነበር። በጉባኤው ከካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን 23 ተወካዮች ሲሳተፉ በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን በኩል ከቡልጋርያ ፓርትያርክ በቀር ሌሎች ሁሉ ተሳትፈዋል። ስብሰባውን የመሩት በጳጳሳዊ የክርስትያን ኣንድነት ምክር ቤት ፕረሲደንት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ኣቡነ ኩርት ኮች እና የፐርጋሞ መትሮፖሊታ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ኣቡነ ዮሃኒስ እንደነበሩም በስብሰባው ፍጻሜ ላይ በእንግሊዝኛ ቋንቋ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተመልክተዋል።

ኮሚሽኑ በስብሰባው ፍጻሜ ጉዳዪን ካጠኑ በኋላ መንበረ ጴጥሮስ ከሲኖዶሶች ጋር በነበረው ግኑኝነት ያካሂደው የነበረ የመሪነት ቦታ ንባበ መለኮታዊና ቤተ ክርስትያናዊ ጥናት እንዲያካሄድ ኣንድ ንኡስ ኮሚቴ ኣቋቊመዋል።

ስብሰባው ቭየና ላይ እንዲሆን የተመረጠበትን ምክንያት ሲገልጡም የምሥራቅና የም ዕራብ መገናኛ በመሆንዋ ለኣንድነት ይረዳል በሚል እንደ ት እምርት መወሰዱንም ከዚህ ጋር ተያይዞ የመጣ ዜና ያመለክታል።

ስብሰባው ስኬታም እንዲሆን ቅዱስ ኣባታችን መስከረም 22ቀን ባስካሄዱት ሳምንታዊ የዕለተ ሮቡዕ ኣጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ ላይ ሁላቸው ም እመናን እንዲጸልዩ ኣደራ ብለው ነበር፤ እንዲሁም የኅብረት ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ኣቡነ በርጠለሜዎስም መል እክት ለተሰብሳቢዎቹ መል እክት እንደጻፉም ተመልክተዋል።

ስብሰባው በተፈጸመ ቅዳሜ ዕለት የቪየና ከተማ ከንቲባ ሚካኤል ህዩፓል ተቀብሎ እንዳነጋገራቸው እንዲሁም በቭየና ቅዱስ እስጢፋኖስ ካተድራል ብጹዕ ካርዲናል ክርስቶፍ ሾንቦርን ካቶሊኮችና ኦርቶዶክሶች የተሳተፉበት መሥዋዕተ ቅዳሴ እንዳሳረጉና የመንበረ ጴጥሮስ ቅድምያ እንዳብራሩ ተመልክተዋል።

እሁድ መስከረም 26 ቀን ደግሞ በቪየና ቅድስት ሥላሴ ካተድራል ከሁለቱም ወገን በተሳተፉበት የፐርጋሞ መትሮፖሊታ ፓርትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ዮሃኒስ መሥዋዕተ ቅዳሴ ኣሳርገዋል። በስብሰባው ግዜ የክርስትያን ኣንድነት ጳጳሳዊ ምክር ቤት ኃላፊ ለነበሩ ብጹዕ ካርዲናል ቫልተር ካስፐር የምስጋና መል እክት እንደተጻፉ የመል እክቱ ይዘትም ብጹዕነታቸው ለክርስትያን ኣንድነት ያደረጉት ኣስተዋጽዖ የሚያመስግን ነበር። የቀድሞ ምተመርተዋል።

በመጨረሻም ተሰብሳቢዎቹ የድርገቱ ሁለትኛ ጸሓፊ ለነበሩትና በዛው ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት ኣቡነ ኤለውተሪኦ ፎርቲኖን በጸሎት በማሰብ ሥራዎቻቸው ስኬታም እንዲሆን ምእመናን በጸሎት እንዲረድዋቸው ኣደራ በማለት ስብሰባው እንድተፈጸመ ከቦታው የደረሰን ዜና ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.