2010-09-29 18:04:48

የቤተ ክርስትያንንና የኅብረተሰብ መታደስ ከምሕረት ይወለዳል


ቅዱስ ኣባታቸን በቪሲታ ኣድ ሊሚና እዚህ ሮም ለሚገኙ የብራዚል ጳጳሳትን ኣግኝተው ባነጋገሩበት ወቅት ራሳችንና ኅብረተሰባችን ለማሳደስ ምህረት ያስፈልገናል ብለዋል።

ኣያይዘውም ቤተ ክርስትያን በዘመናችን ለውጣት ትውልድ ልዩ ትኲረት መስጠት እንዳላትም ገልጠዋል። ለዘመናችን መንፈሳዊ ቀውስ ዋና ምክንያት የምሕረት ፀጋን በደንብ ኣለማወቅና ኣለማሳወቅ ነው፤ የምሕረት ጸጋ እንደ እውነተኛ ችሎታ እንዳለው ያልታወቀ እንደሆነ የሰው ልጅ ከበደል ነጻ የሆነ ይመስለዋል፤

እንደ እውነቱ ከሆነ ግን የሰው ልጆች በኅሊናቸው ይህ ዓይነተ ነጻነት እውነተኛ እንዳልሆነ፤ኃጢኣት መኖሩና እኛም ኃጢኣተኞች መሆናችን ይረዳቸዋል፤ ኣንዳኣንድ የሥነ ልቦና ሊቃውንት የበደል ስሜትን ከኅሊና ለማራቅ ይሞክራሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ኢየሱስ በደልን ሊያጠፋና ነጻነት እንዲያለብሰን እንደመጣ እናውቃለን፤ እንደ እውነቱ ከሆነ ሁላችን ጌታ ያስፈልገናል፤ የእጁ ሥራ በመሆናችን ጌታ እንደ ኣንድ ጠቢብ የእጅ ሥራውን በደንብ በመከታተል የሚያስተካክለውና የሚያጸዳው ጌታም እኛን ከኃጢኣትና ከሌላ በደል ሊያነጻን ይችላል፤

የእውነተኛ ተሓድሶ መሠረት የሆነው ምሕረት ያስፈልገናል፤ እንደ ቅዱሳን ሁሉ ወደ ጌታ ለመመለስና ለመታደስ የእርሱ ምሕረት ያስፈልገናል፡ እንደ ቅዱስ ጳውሎስም ‘የምኖረው እኔ ኣይደለሁም ጌታ ኢየሱስ ነው በኔ የሚኖረው’ እስከማለት በምሕረቱ መታጠብ ኣለብን፤ ቤተ ክርስትያን ከዚሁ የእያንዳንዳችን የግል መታደስ በመነሳት ነው ልትወለድ የምትችለው፤ከዚህ መንጻት የሚፈልቀው ደስታ ትልቅነት ዓለምን ሊነካ ስለሚችል የመላው ዓለም እንደገና በመወለድ ወደ ወጣትነት ሊመልሰው ይችላል፤ በእንዲህ መንገድ በታደሰው ዓለምና ቤተ ክርስትያን የክርስትስ ገጽታ ይንጸባረቃል፤ ትሑትና ጥበበኛ የእውነትና የፍቅር ነቢይ የሆነው ክርስቶስ ኣዲሱ ትውልድ ጓደኛ ነው፤ ሲሉ በምሕረትና በወጣቶች ያተኮረ ንግግር ኣድርገዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.