2010-09-29 18:03:16

ብፅዕት ክያራ ንጹሕ ልብ ያላት


በዲቪን ኣሞረ መካነ ንግደት ትናንትና ማምሻውን የክያራ ባዳኖ የብፅዕና ሥርዓትን የፈጸሙ ብጹዕ ኣቡነ ኣንጀሎ ኣማቶ በብጽዕናው ሥርዓት ባሰሙት ስብከት ይህች ልጅ እንደክሪስታል ንጹሕ ልብ ኣላት እንደ ውቅያኖስ የሚሰፋ ፍቅርም ኣላት ሲሉ ኣመጒሰዋል። የቅዱሳን ጉዳይ የሚከታተል ማኅበር ዋና ሓላፊ ብጹ ዕ ኣቡነ ኣንጀሎ ኣማቶ በ19 ዓመት ዕድሜዋ የሞተችው ይህች ብፅ ዕት የክርስቶስ መል እክተኛ የወንጌል ሓዋርያ ናት፤ የእምነት ኃልንና ንጽሕናን እንድናገኝ ጥሪ ታቀርበናለች፤ ክያራ ባዳኖ የመጀመርያ ቊርባንን በተቀበለች ግዜ ያደርገችው ውሳኔም ‘ለኢየሱስ ብዙ የፍቅር ሥራዎች ማበርከት ኣለብኝ’ የሚል ነበር፤ ይህ ውሳኔ ዕድሜዋ ኣጭር ቢሆም እስከ ሕይወትዋ መጨረሻ በእምነት ጠበቀችው፡ ብጹዕነታቸው ይህን ሲያብራሩ ‘ከሕጻንነትዋ ልዩ የሆነ ፍቅር ስለነበራት ይህንን ፍቅር በቃላትና በተግባር ኣሳይታ ኣለፈች፤ ክያራ በኣንደኛ ደረጃ ትማር በነበረችበት ግዜ ላንድ ድኃ የክፍልዋ ተማሪ ምግብዋን ትሰጥ ነበር፤ እናትዋ ይህን ባወቀች ግዜ ለሁለት የሚሆን ምግብ ኣዘጋጅታ ትሰጣት ነበር፤ ክያራ ግን ሁሉንም ለድሆች ትሰጥ ነበር፤ ምክንያቱም በድሆች ኢየሱስ ታይ ነበርና’ ሲሉ የነበራት የጋለ ፍቅር ከገለጡ በኋላ ባለፈው ዝግጅታችን ያቀረብነውን የሕይወት ታሪክዋን ዘርዝረዋል።

ክያራ ለሃይማኖትዋ ትልቅ ቅናት የነበራት፤ ሁል ግዜም ማንነትዋን የምትገልጥ ተግባርዋ ቃልዋ የማይነጣጠል ጽኑ ክርስትያን እንደነበረችም ኣብራርተዋል።

ለብጽ ዕና ያበቃትም ይህ ጽናትና እርግጠኝነት በመኖሩ በብርቱ ሕመምና ሥቃይ በተፈተነችበት ግዜም እስከ መጨረሻ ታጋሽና ታማኝ በመሆን ነው።

በመጨረሻ መላው ሰውነትዋ በሕመም ተማቆ ሳለ ልቤ ጤነኛ በመሆነ የሚያስፈልገኝ ሌላ የለም በዚህ ልብ ሁሉን ለማፍቀር እችላለሁ ብላ ነበር፤ ፍቅርዋና ለጋስነትዋ ወደር ስላልነበረበት ከኣካላትዋ ሁሉ ጤናማ የነበሩት የዓይን ብሌኖች ስለነበሩ እነሱንም ለተቸገሩ በመለገስዋ ዛሬ ሁለት ሰዎች ብርሃን ሊያዩ ችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.