2010-09-25 14:34:40

ዓለም ከረፍራፊው አደገኛው የኑክሊያር ጦር መሣሪያ ነጻ ማድረግ


ዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ምንጭ ተቆጣጣሪ ድርጅት በቪየና ባካሄደው 54ኛው ክፍለ ጉባኤ ቅድስት መንበርን ወክለው በመሳተፍ ንግግር ያሰሙት የቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ኤቶረ ባለስትረሮ እንዳመለከቱት፣ የምንኖርበት ዓለም ከረፍራፊው የኑክሊያራ ጦር መሣሪያ ነጻ ለማድረግ ዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ተቆጣጣሪ ድርጅት እያረማመደው ያለው መርሃ ግብር አወንታዊ ውጤት የሚያስገኝ ትክክለኛ መንገድ የያዘ ነው ካሉ በኋላ “አቶሚክ የጦር መሳሪያ ጸረ ሕይወት፣ ወቅታዊው እና መጪው ሕይወት ለሥጋት የሚያጋልጥ ጸረ ፍጠረት” መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በ 2010 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት ያሉትን ቃል በመጥቀስ፣ ጸረ የኑክሊያር ጦር መሣሪያ መሥፋፋት በሚል ውሳኔ የተደረሰው የስምምነት ሰነድ ዓለማችን ከአደገኛው ረፍራፊው ጦር መሣሪያ ነጻ እንዲሆን የሚያበቃው ወቅታዊው ብቸኛ መሣሪያ መሆኑ በመግለጥ፣ ይህ የስምምነት ሰነድ በአንዳንድ አገሮች ብቻ ሳይሆን አንድም ሳይቀር በሁሉም አገሮች መንግሥታት ጸድቆ ተቀባይነቱ ዋስትና ያገኝ ዘንድ አሳስበዋል።

በዓለማችን ሰላም ለማረጋገጥ እና የሕዝቦች ጸጥታ እና ደህንነት ዋስትና እዲኖረው ከዓለማችን የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ጨርሶ ማስወገድ ወሳኝ ተግባር ነው ብለዋል።

ቅድስት መንበር የኑክሊየር ኃይል ምንጭ ለመልካም አገልግሎት፣ የሰውን ልጅ የተሟላ እድገት እንዲጎናጸፍ እና በዓለማችን የተጋረጠው ፈተና ለመሻገር የሚያስችል፣ ለዓለም አቀፍ የተሟላ የእድገት ጎዳና መሳካት እንቅፋት የሆነውን ለመዋጋት በሚደረገው ጥረት እና ትብብር መተከያ የሌላት አካል መሆንዋ በማስታወስ፣ ይህ ዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ምንጭ ተቆጣጣሪ ድርጅት ለሰላም ለጤና እና ለብልጽግና የቆመ ተቀባይነት ላለው እድገት እና ይኸንን እድገት ለመጨበጥ ከሚጠይቃቸው ቅድመ መመዘኛዎች አንዱ ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እጅግ አስፈላጊነት ያለው ነው በማለት ይገልጡት የነበረው ሰብአዊነት ሥነ ምኅዳር መሆኑ ከተነተኑ በኋላ፣ በተለይ ደግሞ ረሩም ኖቫሩም አዳዲስ ነገሮች በሚል ርእስ ሥር ር.ሊ.ጳ. ሊዮነ አስራ ሥስተኛ ማህበራዊ ነክ ጉዳዮች ላይ በማስደገፍ እ.ኤ.አ. ግንቦት 15 ቀን 1891 ዓ.ም. የደረስዋት ዓዋዲት መልእክት መቶኛው ዓመት መታሰቢያ ምክንያት እ.ኤ.አ. ግንቦት 1 ቀን 1991 ዓ.ም. መቶኛው ዓመት በሚል ርእስ ሥር የደረስዋት አዋዲት መልእክት፣ ሰብአዊነት ሥነ ምኅዳር በሙላት ይረጋገጥ ዘንድ በማሳሰብ፣ የምንኖርበት አካባቢ ለመንከባከብ የሚደረገው ጥረት አስፈላጊ እና ወሳኝ እንደመሆኑ መጠን ለዚህ መረጋገጥም እውነተኛ የሆነው ሰብአዊት ሥነ ምኅዳር እውን እንዲሆን የሚጠይቀው ግብረ ገባዊ ሁኔታዎች፣ እምብዛም ትኵረት እንደማይሰጥበት በምጥቀስ፣ ስለዚህ ሰብአዊ ሥነ ምኅዳር እጅግ አስፈላጊ ነው ያሉትን ሐሳብ በመጥቀስ ይህ ሰላም እውን ለማድረግ የሚመራ ቃል ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.